የኢትዮጵያ ልማት በዓለም አቀፍ ሚዲያ

(ስንታየሁ ግርማ)

“የኢቫንካ ትራምፕ ጫማዎች ከቻይና ሥሪት ወደ ኢትዮጵያ ሥሪት እየተቀየሩ ነው ” – ኳርትዝ የተባለ ድረ-ገፅ፡፡

ኢቫንካ ትራምፕ የአሜሪካው ዕጩ ፕሬዚዳንት ተወዳዳሪ የዶናልድ ትራምፕ ልጅ ናት፡፡ ኢቫንካ በቻይና የተሠሩ ጫማዎች መሸጫ መደብር አሏት፡፡ ይሁንና የኢቫንካ ጫማ አቅራቢ ድርጅት የሆነው የቻይናው ሁጃን ፋብሪካ በዚህ ሣምንት ፋብሪካው መሠረቱን ከቻይና ጉልበት ርካሽ ወደ ሆነበት ኢትዮጵያ ለማድረግ መወሰኑን የፋብሪካው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጠቅሶ ኳርትዝ እ.ኤ.አ. ኦክቶበር  8, 2016 “ivankaTrump’s Shoe collection may be moving  from made in China to “ made in Ethiopia”  በሚል ርዕስ አንቀፅ አስነብቧል፡፡

የሑጃን ግሩፕ ሥራ አስፈፃሚ እንደሚሉት ግባቸው በኢትዮጵያ 30,000 የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር እ.ኤ.አ. በ2ዐ2ዐ ከውጭ ንግድ የሚገኘው ገቢ ከ1 እስከ 1.5 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ማድረስ እንደሆነ ለአጀንስ ፍራንስ ፕሬስ ገልፀዋል፡፡ ዛንግ በቀላል ኢንዱስትሪ ከተማ ሁሉም የምርት ግብአቶች በተሟሉበት መኖሪያ ቤቶች ባሉበት እና ሆስፒታል በአ/አ በመገንባት የዓለም የሴቶች ጫማዎች ማምረቻ ማዕከል የማድረግ ዕቅድ እንዳላቸው አስታውቀዋል፡፡

ይሁንና ይህ ክስተት ለኢቫንካ እና ለትራምፕ አሉታዊ እንደምታ እንዳለው ኳርትዝ ያስቀምጣል፡፡ ምክንያት ደግሞ ትራምፓ በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት የአሜሪካን ማንፋክቸሪነግን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ኃሳብ እንዳላቸው መግለፃቸው ነው፡፡ ይሁንና የልጃቸው ኢቫንካ የጫማ መደብር የሚሸጣቸው ምርቶች ከውጭ የገቡ ናቸው፡፡ እንደ ሁጃን አባባል ከሆነ ፓሪስ ለሚገኘው የኢቫንካ የጫማ መደብር 100,000 ሺህ ጫማዎችን ሸጦላታል፡፡ ሮበርት ላውረስን የተባሉት የሀርቫርድ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ፕሮፌሰር የኢቫንካን መደብር እና ማስታወቂያ ካጠኑ በኋላ እሳቸው እንደሚሉት ከኢቫንካ የሽያጭ ምርቶች መካከል ከ838 ውስጥ 600 ከውጭ የገቡ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ከቻይና የገቡ ናቸዉ፡፡

ኳርትዝ በመቀጠል ኢትዩጵያ የአፍሪካ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ማዕከል እየሆነች ነው ይላል፡፡ እንደ ኤች.ኤንድ.ኤም እና ፕሪማርክ የተባሉት ካምፓኒዎች መሠረታቸውን ኢትዮጵያ እያደረጉ ነው፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ርካሽ ጉልበት እና መንግሥት በኢንዱስትሪ ፓርኮች እያደረገ ያለው መሠረተ ሠፊ እና ግዙፍ ኢንቨስትመንት ነው፡፡ H and M የሚባለው ድርጅት የሲዊድን ድንበር ተሻጋሪ የሆነ ፋሽን የሚከተል ልብሶችን የሚቸረችር ድርጅት ነው፡፡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በ62 ሀገሮች የሚንቀሳቀስ ሲሆን እ.ኤ.አ. በ2015 ለ132,000 ሰዎች የሥራ ዕድል ሲፈጥር ፕሪማርክ ደግሞ የአይሪሾች ሲሆን በአውሮፓ ልብሶችን በማቅረብ ይታወቃል፡፡

ኳርትዝ እንደሚለው በባለፈው ዓመት ሚክኪንሴይ የተባለው በዓለም ላይ በሥራ አመራር ምክር የተሠማራ ድርጅት ኢትዮጵያን ለመጀመሪያ ጊዜ ከዋነኛ መዳረሻዎች ዝርዝር ውስጥ አስገብታል፡፡ የድርጅቱ ከፍተኛ የሥራ አስፈፃሚዎች በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ውስጥ የኩባንያው ዋነኛ የምርት ምንጮች ሊሆን የሚችሉት ባንግላዴሽ – 48% ፤ ቬትናም – 33% ፤ ኢትዮጵያ – 13% መሆኗን ገልጻ 71ኛው የኩባንያው ምርቶች መዳረሻ እንደምትሆን አስቀምጧል፡፡

የኢቫንካ ጫማዎች ከውጭ የገቡ መሆን ከአባቷ የምርጫ ቅስቀሳ ኃሳብ ጋር ይጋጫል፡፡ ትራምፕ እንደሚሉት ከቻይና በሚገቡ ምርቶች ላይ የ45% ቀረጥ እንደሚጥሉ አስታውቀዋል፡፡ በአግዎ (AGOA) ስምምነት መሠረት ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ የሚገቡ ሸቀጦች ከቀረጥ ነፃ ተደርገዋል ፡፡

ኳርትዝ ብቻ ሳይሆን የሩፐርት ሜርዶክ ንብረት የሆነው ታዋቂው ዋል እስቴርት ጆርናልም “Why made in Ethiopia could be the next made in China” በሚል ርዕስ አንቀፅ ሜይ 15, 2014 ባወጣው ፁሑፍ ፋብሪካዎች ከቻይና በጉልበት መወደድ ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚፈልሱ መዝገቡ ይታወሳል ፡፡

Photo – The 756 km Ethiopia – Djibouti railway was inaugurated on October 5 [Credit: Railway Gazette]

ሌላው በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ትኩረት የሳበው የኢትዮጵያ  ስኬት የኢትዮጵያ ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት መጠናቀቅ ነው ፡፡ ግሎባል ታይምስ በ26/10/2016 “Ethiopian Djibouti Railway signals new era of China’s infrastructure construction” በሚል ርዕስ ባወጣው መጣጠፍ  የባቡር መሥመሩ በአፍሪካና በቻይና መካከል ያለው ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እንደተሸጋገረ የሚያሳይ ነው ብሏል ፡፡ ግሎባል ታይምስ አያይዞም የባቡር ትራንስፖርት “ማርሽ ቀያሪ” እና ወደ መካከለኛ ገቢ ለሚደረገው ጉዞ ቁልፍ እንደሆነ የኢትዮጵያመንግስት ያምናል ብሏል፡፡

ግሎባል ታይምስ አክሎም የኢትዮጵያ የውጭ /የገቢ/ ንግድ 90 በመቶ በጅቡቲ ወደብ ላይ የተመሠረተ ሲሆን ባቡሩ በዓለም በፍጥነት በማድረግ ላይ ካሉት አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ እና የቻይና ግንኙነት እየተጠናከረ መምጣቱን ያሳያል ብሏል፡፡ ባቡሩ በሰዓት 12ዐ ኪሎ ሜትር የሚጓዝ ሲሆን በኢትዮጵያ እና በጅቡቲ መካከል አሁን ያለው የ7 ቀናት ጉዞ ወደ 1ዐ ሰዓታት ዝቅ በማድረግ የሸቀጦችን ዋጋ  በከፍተኛ ዋጋ በመቀነስ የኢትዮጵያን ዕድገት የበለጠ ያፋጥናል፡፡ ግሎባል ታይምስ እንደሚለው መላውን የቻይና የባቡር ኢንዱስትሪ ሠንሠለት ወደ ሌላ ሀገር ኤክስፖርት በማድረግ የመጀመሪያው ልምድ ነው ብሏል፡፡

የአፍሪካ ኤክስፖነት “Ethiopian Djibouti Real way Project African’s first made in electric way” በሚል ርዕስ አንቀፅ ባወጣው ፁሑፍ ኢትዮጵያ ደረጃውን የጠበቀ የባቡር መሥመር እንደዘረጋች እና ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ቀጣይነት ላለው ዕድገት የኢትዮጵያን ፈለግ መከተል እንዳለባቸው አሳስቧል፡፡ ድኀረ ገፁ ባቡሩ የኢትዮጵያንና የአፍሪካን እስትንፋስ የዘራ እና ደስታን ያበሰረ ፤ በትራንስፖርት ዋጋን ባቡሩ በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነስ ከአውሮፓ ጋር በባህር ላይ የምታደርገውን የንግድ ልውውጥ በከፍተኛ ሁኔታ በማቀላጠፍ ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ የኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ብሏል፡፡  ድኀረ ገፁ አክሎም በአንድ ወቅት በድርቅና በርሃብ የምትታወቀው ኢትዮጵያ አሁን በንግድ አጋርነቷ ለአፍታ እንኳን መዘንጋት የሌለባት ሀገር እየሆነች ነው ብሏል፡፡

በተጨማሪም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በኢትዮጵያ ሠላምን እያመጣ እንደሆነ የኢንቨስተሮችን ተስፋ እያለመለመ መሆኑንና መንግሥት ለባለ ሀብቶቹ ከለላ እንደሚሰጥ ዘ ጋርዲያን ዴይሊኔሽን እና ሌሎችም ዘግበዋል፡፡

*********

* ስንታየሁ ግርማ – በኢፌዲሪ ኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ፅ/ቤት፣ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር፡፡ ኢ-ሜይል  Sintayehugirma 76@gmail.com

Guest Author

Guest Author

Recent Posts

ኪዳነ ኣመነ – እንደህዝብ አንድ ሆነናል ያስቸገረን የህወሓት አስተሳሰብ ነው

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 2 - ለውጥ…

5 years ago

ኪዳነ አመነ – ለትግራይ ታላቅነት ሼምለስ ሆነን እንሰራለን

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 1 - ለትግራይ…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ትዴት ኢትዮጲያዊ ማንነት ብቻ እንዳለ ነው የሚያምነው (video)

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ (ክፍል 2)- ስለትዴት…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ኢሳት የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ ነው የሰራው (Video)u

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ (ክፍል 1) -…

5 years ago

የበረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ መታሰር -ሕጋዊ ወይስ ፖለቲካዊ እርምጃ?

(የማነ ካሣ) እንደሚታወቀው አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከጥረት ኮርፖሬሽን ጋር በተያያዘ…

5 years ago

ኣስተያየት በ’ኣብራክ’ ልብወለድ ድርሰት ላይ

(መርስዔ ኪዳን - ሚኔሶታ) ኣብራክ የተባለውን የሙሉጌታ ኣረጋዊ መጽሓፍ ኣነበብኩት። ኣገራችን ከሊቅ አስከደቂቅ በዘውጌ ብሄርተኝነት…

5 years ago