[Audio] ሚ/ር ጌታቸው ረዳ:- በተቃውሞና በሁከት የተሳተፉ ሁሉ በውጭ ሀይሎች ተገፍተው የገቡ ናቸው ማለት አይቻልም።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ ዛሬ ከሰዓት በኋላ የሰጡት ፕሬስ ኮንፈረንስ የድምጽ ቅጂ አትመናል፡፡

በፕሬስ ኮንፍረንሱ ወቅት በሰሞኑ በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሸዋ እና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞኖች እንዲሁም በአማራ ክልል አካባቢ ስላለው ሁኔታ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፤ በኦሮሚያ ክልል ያለውን ሁኔታ አስመልክቶ ከተናገሯቸው ነጥቦች ጥቂቱን እነሆ፡-

*በተቃውሞና ተከትሎ በመጣው ሁከት የተሳተፉ ሁሉ በውጭ ሀይሎች ተገፍተው የገቡ ናቸው ማለት አይቻልም።

*በአብዛኛው ለፌዴራል ስርአቱ የሚጨነቅ ተገቢ ጥያቄዎች ያሉት የህብረተሰብ ክፍል ሲሆን በማስተር ፕላኑ ላይ በቂ ማብራሪያ ካለመሰጠቱ ጋር ተያይዞ የተሰራጩ ወሬዎች በፈጠሩት ብዥታ ተቃውሞን ለማሰማት የሞከረ ነው።

*ሌላው አካል እነኝህን ተገቢ ጥያቄዎች ጠልፎ ተቃውሞውን ወደ ለየለት ሁከት ለመውሰድ የሚሞክር ሀይል ነው።

*በሁከቱና ሰላም ለማስፈን በተወሰዱ እርምጃዎች ቀላል የማይባል ሰው ሞቷል። የቁጥር እንካሰላንታ ውስጥ መግባት አላስፈላጊ ነው። Originally ከተነሳበት genuine የመልካም አስተዳደርና ማስተር ፕላን ጥያቄዎች አንፃር አንድም ሰው ቢሆን መሞቱ አሳዛኝ ነው።

*አሁን ሁኔታው መጀመሪያ ከነበረው ባህሪው ተቀይሯል። በደቡብ እና ደቡብ ምእራብ ሸዋ አንዳንድ ከተሞች ላይ ያለው እንቅስቃሴ ከማስተር ፕላኑም ከመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ጋር የማይገናኝ የለየለት ብጥብጥን ለመፍጠር የሚደረግ ነው። አሁን እንደ መጀመሪያው ወጣቶች ስሜታቸውን የሚገልፁበት ሁኔታ አይደለም ያለው፤ የታጠቁ armed gangs ከአካባቢያቸው ውጪ እየተንቀሳቀሱ የሚያውኩበት ሁኔታ ነው ያለው።

*እነኚህን ያሰማሯቸው ሀይሎች መልሰው መቆጣጠር መቻላቸውንም እርግጠኛ መሆን አይቻልም።

*ትክክለኛ ጥያቄ ያቀረበው የህብረተሰብ ክፍል አንዳንድ ሀይሎች ወደ ስርአት አልበኝነት በመውሰዳቸው ምክንያት ተገቢ ጥያቄዎቹ ሊደፈቁበት አይገባም፤ በሚካሄዱ ሪፎርሞች ሊመለስለት ይገባል።

*አብዛኛው ህዝብ የፌዴራል ስርአቱን የመጠበቅ እንጂ የማፍረስ አላማ ስለሌለው ነው ከጥፋት የዳንነው።

*ምንም እንኩዋን ተቃውሞው በነበረባቸው አካባቢዎች ተቃዋሚዎች የተሻለ ድምፅ ያገኙባቸው ቢሆንም፣ ህዝቡ ኢህአዴግን የመረጠው ከነቅሬታዎቹ ነው።

*የመንግስት እምነት የመልካም አስተዳደር እና የሰብአዊ መብት ጥያቄዎችን መመለስ ካልቻልን ለውጭ ሀይሎች ተጋላጭ እንሆናለን vulnerability እንፈጥራለን የሚል ነው።

*********** 

ሙሉውን ከድምጽ ቅጂው ያዳምጡ።

Fetsum Berhane

Fetsum Berhane is an Ethiopian resident, economist researcher and a blogger on HornAffairs.

Recent Posts

ኪዳነ ኣመነ – እንደህዝብ አንድ ሆነናል ያስቸገረን የህወሓት አስተሳሰብ ነው

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 2 - ለውጥ…

5 years ago

ኪዳነ አመነ – ለትግራይ ታላቅነት ሼምለስ ሆነን እንሰራለን

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 1 - ለትግራይ…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ትዴት ኢትዮጲያዊ ማንነት ብቻ እንዳለ ነው የሚያምነው (video)

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ (ክፍል 2)- ስለትዴት…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ኢሳት የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ ነው የሰራው (Video)u

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ (ክፍል 1) -…

5 years ago

የበረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ መታሰር -ሕጋዊ ወይስ ፖለቲካዊ እርምጃ?

(የማነ ካሣ) እንደሚታወቀው አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከጥረት ኮርፖሬሽን ጋር በተያያዘ…

5 years ago

ኣስተያየት በ’ኣብራክ’ ልብወለድ ድርሰት ላይ

(መርስዔ ኪዳን - ሚኔሶታ) ኣብራክ የተባለውን የሙሉጌታ ኣረጋዊ መጽሓፍ ኣነበብኩት። ኣገራችን ከሊቅ አስከደቂቅ በዘውጌ ብሄርተኝነት…

5 years ago