የኢህአዴግ 10ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ የአቋም መግለጫ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር/ኢህአዴግ /10ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ የተካሄደው አምስተኛው ጠቅላላ ምርጫ በማንኛውም መስፈርት ሲለካ እጅግ ዴሞክራሲያዊ፣ፍትሐዊ፣ግልጽ እና በመላው የሀገራችን ህዝቦች ዙሪያ መለስ ተሳትፎ የተፈፀመ ከመሆኑም በላይ የምልአተ ህዝቡን ንቁ ተሳትፎና ተአማኒነት ያተረፈ ሆኖ በተጠናቀቀበት ማግስት እንዲሁም ህዝቡ ለድርጅታችን ስኬታማ ስራዎች እውቅና በመስጠት እና ድክመቶቻችንን እንደምናርም በማመን አርቆ አሳቢነትና አስተዋይነት በተሞላበት አኳኋን ታላቅና ከባድ ሀላፊነት በሰጠበት ፤የመጀመሪያውን ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አንፀባራቂ ድሎች በማስመዝገብ በማያቋርጥ የለውጥና የህዝብ ተጠቃሚነት አቅጣጫ መጓዝ በቻልንበትና ለህዳሴያችን መሰረት ያስቀመጥንበት 14ኛው ዓመት ታሪካዊ የተሀድሶ ጉዞ ላይ በምንገኝበት ፤ከዚህም ባሻገር የሁለተኛውን የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ የህዝቡን ተሳትፎ ባረጋገጠ መልኩ ነድፈን ወደ ተግባር ለመግባት የተሟላ ዝግጅት ባደረግንበት ህሊናዊና ነባራዊ ሁኔታ ላይ ሆነን ያካሄድነው በመሆኑ ታሪካዊ ጉባዔ ነው፡፡

የዛሬ 14 ዓመት የተጀመረው የሀገራችን የህዳሴ ጉዞ በኢህአዴግ መሪነት እንዲሁም በህዝቡ የተደራጀ እንቅስቃሴ በመላ ሀገራችን ፈጣን ፣ ተከታታይ ህዝቡን በየደረጃው ተጠቃሚ ያደረገ እድገት በማረጋገጥ በምግብ ሰብል እራሳችን የቻልን ሲሆን የቁልቁለት ጉዟችንን ገትተን ከጥልቁ የድህነት ጉድጓድ መውጣት ጀምረናል፡፡ በሁሉም ዘርፎች ተስፋ ሰጪና አኩሪ ድሎች መመዝገብ ጀምረዋል፡፡ 10ኛው ድርጅታዊ ጉባኤያችንም በእነዚህ አንጸባራቂ ድሎች እና ታላቅ ህዝባዊ ሀላፊነትና አደራን ከምን ጊዜውም በላይ መወጣት በሚገባን ወሳኝ ጊዜና ድባብ ታጅቦ የተካሄደ ሲሆን በመጀመሪያው አምስት ዓመታት የተቀመጡ ግቦች እንዲሁም በ9ኛው ድርጅታዊ ጉባዔያችን የመጀመሪያው መርሀ ግብር የሁለት ዓመት ተኩል አፈፃፀም ግምገማ በመነሳት በፖለቲካዊና ርዕዮተ ዓለማዊ ጥራት ፣ በመልካም አስተዳደርና ዴሞክራሲ ፣ በኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት ግቦች የተቀመጡ አቅጣጫዎች እና በአምስተኛው አገራዊ ምርጫ ወቅት ህዝቡ ያነሳቸው አንገብጋቢ ጥያቄዎችን መሰረት ኣድርጐ ጉባዔያችን በአጽንኦት ገምግሟል፡፡

በተለይም በመልካም አስተዳደር አፈፃፀም ረገድ የሚታዩ ችግሮችን በጥልቀት በመገምገም የሞት ሽረት ትግል በማድረግ ችግሮችን በብቃት ለመፍታት የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል፡፡ በመጀመሪያው እድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈፃፀም በጥንካሬም ሆነ በድክመት የምንወስዳቸውን ተሞክሮዎች በመለየት በሁለተኛው የዕቅድ ዘመን በሁሉም ዘርፎች የላቀ ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ መሰረታዊ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል፡፡

በመሆኑም “ህዝባዊ አደራን በላቀ እድገትና ትራንስፎርሜሽን” በሚል መሪ ቃል በሰሜናዊቷ ኮከብ መቀሌ ከተማ በሚገኘው ለሰላም፣ለልማት እና ለዴሞክራሲ መረጋገጥ እና የዛሬው ቀን ይመጣ ዘንድ ለተሰዉ ሰማዕታት መታሰቢያ በተገነባው አዳራሽ ከነሀሴ 22-25/2007 ዓ.ም የተካሄደው 10ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔተኞች የሚከተለዉን ባለ 9 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተናል፡፡

  1. በድርጅታችን ኢህአዴግ ተሀድሶ ጠርቶ በመጣው የልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መስመራችን በግልፅ እንደተቀመጠው የኪራይ ሰብሰቢነት ፖለቲካል ኢኮኖሚ በልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ፖለቲካል ኢኮኖሚ የመቀየር ጉዳይ የህዳሴ ጉዟችን ዋነኛ አቅጣጫ በማድረግ ባለፉት ዓመታት በተካሄደው ርብርብ በገጠር የልማታዊ ፖለቲካል ኢኮኖሚ የበላይነት እየያዘ የመጣ ቢሆንም በከተሞች አሁንም የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብ የበላይነት እንደያዘ እንደሚገኝ ጉባኤያችን ገምግሟል፡፡ የብዙዎቹ ችግሮቻችን ዋነኛ መንስኤና ምንጭ ከኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር ጋር የተያያዘ መሆኑን የተመለከተው ጉባኤያችን በቀጣይ ዓመታት የኪራይ ሰብሳቢነት ምንጮች ሆነው የተለዩትን የመሬት ፣ የግብር ኣሰባሰብ የመንግስት ግዥና ኮንትራት አስተዳደር ላይ የሚታዩ ችግሮችን ስር ነቀል በሆነ ሁኔታ ለመፍታት ከፍተኛ ርብርብ መደረግ እንዳለበት አስምሮበታል፡፡ በመሆኑም እኛ የ10ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ ተሳታፊዎች የልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ተግባራት እንዲጎለብቱ የፀረ-ኪራይ ሰብሳቢነት ትግሉ በላቀ ደረጃ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከምንጊዜውም በላቀ ሁኔታ ለመረባረብ ቃል እንገባለን፡፡

  2. በአገራችን እየተመዘገበ ባለው ፈጣን ዕድገትና ለውጥም ሆነ በሂደቱ እየተስተዋሉ ላሉት ድክመቶች ወሳኙ የድርጅታችን ጥንካሬ መሆኑን በመገንዘብ እና የሁሉም ችግሮቻችን መፍቻ ቁልፍ የውስጠ ድርጅት ስራችን ብቃት የሚወስን መሆኑን በመገምገም ከፊታችን ከሚጠብቀን ውስብስብ መድረክ በአመራሩና በአባላት የሚታይ የአድርባይነትን፤ፀረ-ዴሞክራሲ ዝንባሌዎች እንዲሁ ፤ የቁርጠኝነትና የህዝባዊ ወገንተኝነት የመላላት ችግሮችን ለማስወገድ እንዲቻል የውስጠ ድርጅት ዴሞክራሲን በማጠናከር የአመራሩና የአባላቱ ፖለቲካዊና ርዕዮተ-አለማዊ ብቃት በማጎልበት የርድጅታችን የመሪነት ሚና ወደ ላቀ ደረጃ ለማሻጋገር ከምን ጊዜውም በላይ በትጋት እንረባረባለን፡፡

  3. በ9ኛው ድርጅታዊ ጉባኤያችን ባስቀመጥነው አቅጣጫ መሰረት በተፈጥሮ ሀብት እና አካባቢ ጥበቃ ስራዎች በመጀመሪያ ደረጃ የሚታይ የሰራዊት ግንባታ በማረጋገጣችን እንዲሁም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በሰራነው ስራ በምግብ ሰብል ራሳችንን ያስቻለ ስኬት መመዝገቡንም ጉባዔው ያረጋገጠ ሲሆን በእንሰሳት ሀብት ፣ በመስኖ ልማት ስራዎች እንዲሁም በከተማ ልማት ዘርፍ የሰራዊት ግንባታው በሚፈለገው ደረጃ ያልተፈፀመ መሆኑን ገምግሟዋል፡፡ በመሆኑም በገጠርም ሆነ በከተማ የተጀመረው የልማት ሰራዊት ግንባታ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሰራዊት ግንባታ እጥረት በታየባቸው መስኮች ብቃት ያለው ሰራዊት በመገንባት ሁሉንም የልማት አቅሞች በብቃት በመገንባትና የማስፋት ስትራቴጂያችንን በማጠናከር በሁሉም ዘርፎች የሚታዩ መልካም ልምዶችን በማስፋት ለመዋቅራዊ ለውጥና ትራንስፎርሜሽን ከመቼውም ጊዜ በላቀ ፍጥነት ለማሳካት እንረባረባለን፡፡

  4. እኛ የጉባኤው ተሳታፊዎች በልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መስመራችን እየተመራን ባለፉት 12 ዓመታት ባለ ሁለት አኃዝ የኢኮኖሚ ዕድገት በማስመዝገብ በኣለም ደረጃ በፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ብሆንም አገራችን አሁንም ከድህነት ያልተላቀቀችና በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ያልቻለች በመሆኑ በቀጣይ ፈጣን ፣ ተከታታይና ፍትሃዊ ኢኮኖሚ ዕድገት በላቀ ደረጃ አጠናክሮ በማስቀጠል በ2ኛ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር ለማረጋግጥ የሚያስችሉ የማክሮ ኢኮኖሚ ጉዳዮች በተለይም በቁጠባ ፣ ኢንቨስትመንት እና ኢኮኖሚ የሚያመነጨውን ገቢ አሟጦ በመሰብሰብ ረገድ የተመዘገቡ ስኬቶችን የበለጠ ለማጎልበት ፣ በሌላ በኩል አሳሳቢ ደረጃ ላይ ለሚገኘው የወጪ ንግድ ሚዛን ክፍተት እና ፤ የማንፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚታዩ ችግሮችን በወሳኝነት በመፍታት ወደ ኢንዱስትሪ የሚደረገዉን ሽግግር ለማፍጠን ቃል እንገባለን፡፡

  5. በማህበራዊ ልማት ረገድ በተለይም በጤናና በትምህርት ዘርፎች ባለፉት ዓመታት በርካታ አንፀባራቂ ድሎች የተመዘገቡ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ አሁንም ለዘርፎቹ በተደራሸነት እና በጥራት ረገድ የሚታዩ ችግሮች ላይ ስር ነቀል ለውጥ በማምጣት የህብረተሰቡን እርካታ ለማረጋገጥ ያላሰለሰ ጥረት እናደርጋለን፡፡

  6. በድርጅታችን መሪነት የተጀመረውን ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ቀጣይነት ተወዳዳሪነት ለማጎልበት የተጀመሩትን ሰፋፊ መሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎች በማከናወን ረገድ አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸው እንዳለ ሆኖ በዘርፉ የሚስተዋሉትን የተደራሽነትና የአገልግሎት ጥራት ችግሮች በብቃት በመፍታት ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገቱን ለማስቀጠል እንዲሁም ፍትሃዊ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት እንረባረባለን፡፡

  7. ባለፉት ዓመታት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታን ለማፋጠንና ለማጎልበት የተለያዩ ተግባራት መከናወናቸውን ጉባኤያችን ገምግሟል፡፡ በዚህ ረገድ በየደረጃው የሚገኙ ምክር ቤቶች ተልዕኳቸውን እንዲወጡ በተለይም አስፈፃሚውን አካል የመከታተልና የመቆጣጠር ኃላፊነታቸውን በብቃት መወጣት እንዲችሉ ፣ የብዙሃንና የሙያ ማህበራት በሀገራችን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ እና በነቃ ተሳትፎ ፣ የትምክህት የጠባብነትና የአክራሪነት ዝንባሌዎችን ለመታገል በመቻቻልና በመከባበር ላይ የተመስረተው አንድነታችን ፀንቶ እንዲኖር የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ፣የመድበለ ፓርቲ ስርዓቱን ለማጐልበት የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክሪ ቤት ተጠናክሮ እንዲቀጥል፤ ሚዲያዎች የህዝቡ ልሳን በመሆን ፍላጎቶችንና ሃሳቦቹን በአግባቡ እንዲስተናገዱ ፣ የህዝቡ ቀጥተኛ ተሳትፎ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን ጉባኤያችን አስቀምጧል፡፡ በመሆኑም እኛ የዚህ ታሪካዊ ጉባኤ ተሳታፊዎች ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በብቃት ለመፈጸም ቃል እንገባለን፡፡

  8. የሴቶችና የወጣቶች ሁሉን አቀፍ ተሳትፎና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ፣ ለመልካም አስተዳደር መስፈንና ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የጎላ ሚና እንዲጫወቱ አደረጃጀታቸውን የማጠናከርና አቅማቸውን የመገንባት ስራችን መሻሻል የታየበት ቢሆንም አሁንም የወጣቶችንና የሴቶች ተጠቃሚነት የበለጠ ለማረጋገጥ በትጋት መስራት እንደሚጠበቅብን ተገንዝበናል።በመሆኑም የወጣቶቸንና የሴቶቸን የስራ ፈጠራና አቅም በመገንባት እና የስራ እድል በማስፋት ከጠባቂነት ተላቀው በፈጣን ኢኮኖሚያዊ እድገትና ዴሞክራሴያዊ ስርአት የመገንባት ትግላቸን በንቃት በመሳተፍ ተጠቃሚነታቸውን እንዲያረጋግጡ አበክረን እንሰራለን።

  9. ጉባኤያችን በመልካም አስተዳደር ዘርፍ እየታዩ ባሉ መጠነኛ ለውጦችና ሰፊ ትግል በሚጠይቁ ችግሮች ዙሪያ ጥልቀት ያለው ግምገማ አካሄዷል። የመልካም አስተዳደር ጉዳይ ከልማታቸን ጋር በእጅጉ የተሳሰረና የህልውና ጉዳይ በመሆኑ የህዝቡን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ያረጋገጠ ፈጣን ልማት እየተመዘገበ መሆኑ እንዲሁም የመንግስትን አሠራር ግልጽነትና ተጠያቂነት በማረጋገጥ ረገድ ከጊዜ ወደ ጊዜ አዳጊ ለውጦች እየተመዘገቡ መሆናቸውን ገምግመናል።ይሁን እንጂ የኪራይ ሰብሳቢነት ፖለቲካል ኢኮኖሚ በሚፈለገው ደረጃ እየተዳከመ ባለመሄዱ ምክንያት በአገልግሎት አሰጣጣችን የሚፈለገውን ለውጥ ህዝባዊ እርካታ ለመረጋገጥ እንዳተቻለ ፤ ህዝባችንን ቅሬታ ውስጥ የሚያስገቡ እና የልማታችን እንቅፋት የሆኑ አድሎአዊ አሰራሮች የኪራይ ሰብሳቢነት ተግባራት እንዲሁም ሙስናን የመሳሰሉ ብልሹ አሠራሮች እንዳሉ ጉባዔያችን በአጽንኦት አይቷል፡፡ በመሆኑም እኛ የ10ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ ተሳታፊዎች የድርጅታቸን ህዝባዊ መርሆዎች እና አሰራሮች እንዲከበሩና የህዝቡን ተሳትፎና ባለቤትነት እንዲሁም ፍትሃዊ ተጠቃሚነቱን የሚያረጋግጡ አቅጣጫዎችን በመያዝ እና የመልካም አስተዳዳር ችግሮችን መፍታት የሞት ሽረት ጉዳይ መሆኑን በመገንዘብ በምርጫ ያከበረንና ችግሮቻችን እኛው እንደምንፈታ በማመንና ግልፅ መልእክት በማስተላለፍ በድጋሚ እንድንመራው ፈቃድ የሰጠንን የሀገራችንን አስተዋይና አርቆ አሳቢ ህዝብ በጠንካራ የተቋማት ግንባታ ፣ በግልፅነትና ተጠያቅነት ስርዓት ለማገልገል በድርጅታችን ፀንቶ የቆየውን የውስጠ ድርጅት ትግል በመቀጣጠል እና ህዝቡን በተደራጀ አግባብ በማሳተፍ በመልካም ኣስተዳደር ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት ቃል እንገባለን፡፡

መላው የድርጅታችን አባላትና ደጋፊዎች !

ድርጅታችን ኢህአዴግ መላ የሀገራችንን ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ከነበሩበት እስር ቤት እንዲወጡ አታግሎ በታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ አገላለፅ ” የድህነት እና ኋላ ቀርነት ዘበኛ” የነበረውን አስከፊ ስርኣት ከገረሰሰ በኋላ እነሆ ሀገራችንን ከቁልቁለት ጉዞ በማውጣት ተከታታይ ስኬት እያስመዘገብን በአለም አደባባይ ከፍ ብለን መታየት የጀመርንበትና በበርካታ ጉዳዮች በመልካም አብነት መጠራት የቻልንበት ሁኔታ ተፈጥሯል። ዛሬ በሀገራችን የመለወጥ እና የማደግ ተስፋ ለምልሟል፡፡ ይህ ይሆን ዘንድ ደግሞ የእናንተያልተቆጠበ ጥረትናትጋት ከፍተኛ ድርሻ ያለው መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ህዝባችንም በድርጅታችን ላይ ያለውን እምነት በማሳየት ጥንካሬዎቻችን እና ድክመቶቻችንን መዝኖ አሁንም እንድንመራው ፈቅዶልናል፡፡ ይህንን ውሳኔም ሲወስን ድክመቶቻቻንን የመፍታት ልምድና ብቃት አንዳለን በማመን ነው፡፡በመሆኑም ድርጅታችን ታላቅና ከባድ የህዝብ አደራ የተሸከመ ድርጅት መሆኑን በመገንዘብ ይህንኑ ከባድ አደራ በብቃት ለመወጣት በሁሉም የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ መስኮች የጀመራችሁትን ጥረት ከምንግዜውም በላቀና በአዲስ የትግል ወኔ፣ በተሟላ የተነሳሽነት መንፈስና ዝግጁነት ለመፈፀም የውስጠ ድርጅት ትግል በመለኮስ እና ትግሉን የህዝቡ ለማድረግበ10ኛው ድርጅታዊ ጉባኤያችን በአጽንኦት የተመከረባቸውና ውሳኔ የተላለፈባቸውን ጉዳዮች በተለይምየሁለተኛውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ግቦች በማሳካት የአገራችን ህዝቦች ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ጽናት በተሞላበት መንፈስ ለላቀ ድል እንደትነሳሱ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

መላው የአገራችን ህዝቦች!

ዛሬ በዚህ በርካቶች ለህዝብ ጥቅም ሲሉ የከፈሉትን መስዋዕትነት ለማሰብ በተገነባው የትግራይ ሰማዕታት ሀውልት አዳራሽ ሆነን የተሰውለትን ዓላማ ሙሉ በሙሉ ለማሳካት እየመከርን ባለንብት 10ኛው ድርጅታዊ ጉባዔያችን ላይ ሆነን በምርጫው ያስተላለፋችትን ውሳኔና ከውሳኔው ጋር የሰጣችሁን መልዕክት በአግባቡ እንረዳለን፡፡ የሉአላዊ ስልጣን ባለቤትነታችሁን ተጠቅማችሁ የሰጣችሁት ውሳኔ ባስመዘገብናቸው ስኬቶች እና እስከ አሁን ባልረካችሁባቸው ጉዳዮችም ኢህአዴግ ከህዝባዊና አብዮታዊ ባህሪው በመነሳት ይፈታቸዋል የሚል እምነት አሳድራችሁ እንደሆነም እንገነዘባለን ። በመሆኑም ስላስተስተላለፋችሁት በሳልና ምክንያታዊ ውሳኔ እኛ ኢህአዴጎች በዚህ አጋጣሚ እንደ ታላቁ መሪያችን ሁሉ እጅ እንነሳለን፤ እናመሰግናለን፡፡ በ10ኛው ድርጅታዊ ጉባኤያችን የተላለፉ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ይበልጥ ተጠቃሚነታችሁን የሚያረጋግጡበመሆናቸው፤ መላው የአገራችን አርሶ አደሮች፣አርብቶ አደሮች፤ የከተማ ነዋሪዎች፤ ወጣቶች፤ ሴቶች እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ለተፈፃሚነታቸው በባለቤትነት እና በከፍተኛ ተሳትፎ እንድትረባረቡ ጥሪያችንን እናቀርብላችኋለን፡፡

በተለያየ የስራ መስክ የተሰማራችሁ ሰራተኞች፤ ምሁራን፣ የፍትህና ፀጥታ አካላት፣ ህዝባዊ ተቋማት!!

በአሁኑ ሰዓት በአገራችን በገጠርም ሆነ በከተማ የሚካሄዱትን የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች በመፈፀምና ህዝባችንን በቅርበት በማገልገል ለተገኙ ውጤቶች ላደረጋችሁት ትጋት የተሞላበት ጥረት ኢህአዴግ ታላቅ አክብሮትና ልዩ አድናቆት አለው፡፡ በመሆኑም የጀመርነው ድህነትንና ኋላቀርነትን የመቅረፍና ህዝባችንን ተጠቃሚ የማድረግ አቅጣጫ ጎልብቶ የህዳሴ ጉዟችን እንዲሳካ እንደ ወትሯችሁ በሁሉም መስክ የላቀ ርብርብ እንድታደርጉ ጥሪያቸን እናቀርብላቹኃለን፡፡

ለመላው የአገራችን ባለሃብቶች !

እስከአሁን በአገራችን ለተካሄዱ የልማት እንቅስቃሴዎች እና ለተመዘገበው አኩሪ ድል እያደረጋችሁት ያላችሁትን የማይተካ አስተዋጽኦ በልዩ አክብሮት እንመለከተዋለን፡፡ ይኸው ተሳትፏችሁ ይበልጥ እንዲጎለብት ድርጅታችን ያላሰለሰ ጥረት ያደርጋል፡፡ በእናንተም በኩል ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ያልሆኑ ተግባራት ለእናንተም ሆነ ለአገሪቱ ሁለንተናዊ እድገትና የህዝብ ተጠቃሚነት እንደማይበጁ ተገንዝባችሁ ነፃና ፍትሃዊ ውድድር ላይ ለተመሰረተ የኢኮኖሚ ግንባታ ያልተቆጠበ ጥረታችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ፣ ለህዳሴ ጉዛችን ወሳኝ በሆኑት የማኒፋክቸሪግ የኢንዱስትሪ ዘርፍና የወጪ ንግድ በብቃት እንድትሳተፉ እና ድርጅታችን ኪራይ ሰብሳቢነትን ለመታገል በሚያደርገው ትግልም ከጎናችን እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

ለድርጅታችን አጋሮች፣ ደጋፊዎችና ወዳጆቻችን!!

እስከአሁን ባለን ግንኙነት አገራችንን ለመለወጥ ባደረግነው ርብርብ በልዩ ልዩ መንገድ በመደገፍ ከድርጅታችን ጎን በመሰለፍ በድህነት ትግላችን ላይ ያደረጋችሁትን አስተዋጽኦ በታላቅ አክብሮትና የአጋርነት መንፈስ እንመለከተዋለን፡፡ በቀጣይም አጋርነታችን ተጠናክሮ እንዲቀጥል እና ወደ ላቀ ደረጃ እንድናደርሰው ጥሪያቸንን እናቀርባለን።

በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጲያዊያንና ትውልደ ኢትዮጲያዊያን፣!

በሀገር ውስጥ የሚኖረው ወገናችሁ በልማትና በዴሞክራሲ ጎዳና በመረማመድ ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ በማድረግ በሀገር ግንባታ በመሳተፍቀጣይነት ያለው ተጠቃሚነቱን እያረጋገጠ ይገኛል፡፡ ይህ አኩሪ ድል የእናንተንም የላቀ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ይሻል፡፡ በመሆኑም ባላችሁ እውቀትና ሃብታችሁን በማስተሳሰር አገራችሁን በማልማት ተጠቃሚነታችሁን እንድታረጋግጡ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

በአጠቃላይ ድርጅታችን ኢህአዴግ በቀደሙት ዘጠኝ ተከታታይ ጉባኤዎቹ ሲያደርግ እንደመጣው ሁሉ 10ኛው ድርጅታዊ ጉባኤያችን ድህነትንና ኋላቀርነትን በማስወገድ፣ የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ጎልብቶ በኪራይ ሰብሳቢነት ፖለቲካል ኢኮኖሚ ላይ የበላይነቱን እንዲያረጋግጥ ፤ ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር ተጠናክሮ የህዝባችን ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነት እውን እንዲሆን የቀጣይ ትግል ትጥቅና ቁርጠኝነት የተሞላበት ጽናት እንድንላበስ አስችሎናል፡፡ ስኬታማ ጉዟችን በመፈታታን ደንቃራ የሆኑትን የመልካም አስተዳደርና የኪራይ ሰብሳቢነት ችግሮችን የመፍታት ጉዳይ የሞት ሽረት ጉዳይ አድርገን በመውሰድ ችግሩን ለመፍታት በቁርጠኝነት ተነስተናል፡፡ እንደየመድረኩ ጥያቄና ባህሪ መስዋዕትነት ስንከፍል እንደቆየነው ሁሉ ዛሬም ሁሉንም ፈተናዎች በጽናት በመመከት ህዝቡ የሰጠንን ታላቅ አደራ በላቀ እድገትና ትራንስፎርሜሽን ለመወጣት ራሳችንን ያዘጋጀን በመሆኑ መላ የድርጅታችን አባላትና ደጋፊዎች፣የአገራችንብሄር ብሔረሰቦችና ህዝቦች፣ የመንግስት ሰራተኞችና የፀጥታ አካላት ፣ ልማታዊ ባለሀብቶች፣ ህዝባዊ አደረጃጀትና ተቋማት እንዲሁም ለድርጅታችን አጋሮችና ደጋፊዎች ከጎናችን እንድትቆሙና የጋራ ፕሮጀክታችን የሆነውን የኢትጵያ ህዳሴ ለማረጋገጥ ለሚደረገው ጉዞ እጅለእጅ ተያይዘን ችግሮችን በመቅረፍ በስኬት ጐደና እንድንገሰግስ ጥሪያችን እናቀርባለን፡፡

“ህዝባዊ አደራን

በላቀ ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን!!”

ዘላለማዊ ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!!

ነሀሴ 25/2007 ዓ.ም

መቀሌ

**********

Curated Content

Content gathered and compiled from online and offline media by Hornaffairs staff based on relevance and interest to the Horn of Africa.

Recent Posts

ኪዳነ ኣመነ – እንደህዝብ አንድ ሆነናል ያስቸገረን የህወሓት አስተሳሰብ ነው

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 2 - ለውጥ…

5 years ago

ኪዳነ አመነ – ለትግራይ ታላቅነት ሼምለስ ሆነን እንሰራለን

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 1 - ለትግራይ…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ትዴት ኢትዮጲያዊ ማንነት ብቻ እንዳለ ነው የሚያምነው (video)

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ (ክፍል 2)- ስለትዴት…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ኢሳት የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ ነው የሰራው (Video)u

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ (ክፍል 1) -…

5 years ago

የበረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ መታሰር -ሕጋዊ ወይስ ፖለቲካዊ እርምጃ?

(የማነ ካሣ) እንደሚታወቀው አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከጥረት ኮርፖሬሽን ጋር በተያያዘ…

5 years ago

ኣስተያየት በ’ኣብራክ’ ልብወለድ ድርሰት ላይ

(መርስዔ ኪዳን - ሚኔሶታ) ኣብራክ የተባለውን የሙሉጌታ ኣረጋዊ መጽሓፍ ኣነበብኩት። ኣገራችን ከሊቅ አስከደቂቅ በዘውጌ ብሄርተኝነት…

5 years ago