የሰማያዊ ፓርቲ ኦዲትና ኢንስፔክሽን ኮሚቴ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር በሆኑት በኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ላይ የገንዘብ መቀጮ ሲጥል አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድን ከድርጅት ጉዳይ ኃላፊነት እንዲነሱ ውሳኔ ማስተላለፉ ተገለፀ።
የሰማያዊ ፓርቲ ኢዲትና ኢንስፔክሽን ኃላፊ አቶ ብርሃኑ መሰለ በበኩላቸው የተወሰደ የዲስፒሊን እርምጃ መኖሩን አምነው ቅጣት የተላለፈባቸው አባላት የይግባኝ መብታቸው የተጠበቀ በመሆኑ አሁን ላይ ሆኖ ዝርዝር መረጃ ለመስጠት እንደሚቸገሩ ገልፀውልናል።
ኢንጅነር ይልቃል ባሳዩት ተደጋጋሚ የዲሲፕሊን ግድፈት መሆኑን ምንጫችን ጠቁሞ ግድፈቶቹ ምን እንደሆኑ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል።
ጉዳዩ የቀረበለት የፓርቲው ኦዲትና ኢንስፔክሽን ኮሚቴ በሊቀመንበሩ ላይ የ500 መቶ ብር መቀጫ እንዲከፍሉ ኦዲት ኮሚሽኑ ውሳኔ አስተላልፎባቸዋል።
እንዲሁም የፓርቲ ሚስጥር ለመገናኛ ብዙሃን አሳልፋ ይፋ አድርጋለች ተብላ ከሥራ አስፈፃሚ የታገደችው ሃና እና ሌሎች ተጨማሪ አባላት ከአንድ መቶ ብር እስከ ሰባት መቶ ብር መቀጫ የተጣለባቸው መሆኑን ለማወቅ ችለናል።
*******
ሰንደቅ፡- ጥቅምት 29፣ 2007
ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 2 - ለውጥ…
ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 1 - ለትግራይ…
የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ (ክፍል 2)- ስለትዴት…
የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ (ክፍል 1) -…
(የማነ ካሣ) እንደሚታወቀው አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከጥረት ኮርፖሬሽን ጋር በተያያዘ…
(መርስዔ ኪዳን - ሚኔሶታ) ኣብራክ የተባለውን የሙሉጌታ ኣረጋዊ መጽሓፍ ኣነበብኩት። ኣገራችን ከሊቅ አስከደቂቅ በዘውጌ ብሄርተኝነት…