Categories: EthiopiaNews

የመንግሥት ሠራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት ሰኞ ይጀመራል

የፌዴራልና የአዲስ አበባ ሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት የሙከራ ስምሪት የፊታችን ሰኞ እንደሚጀመር የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት አስታወቀ፤ለጊዜው አገልግሎት መስጠት ከሚጀምሩት 55 አውቶቡሶች በተጨማሪ ዘግይተው የደረሱ መረጃዎችን መሠረት በማድረግ ሌሎች አዳዲስ አውቶቡሶች እንደሚሰማሩ ታውቋል።

የድርጅቱ ዋና ሥ ራ አስኪያጅ አቶ ደረጀ ወልደ ዮሐንስ እንደተናገሩት፤ መስከረም 5 ቀን 2007 ዓ.ም የሚጀመረው አገልግሎት ለመነሻ 10 የሙከራ ስምሪት መስመሮች ይኖሩታል። ከመስመሮቹ መካከል ጨፌ-ሃያት፣ ጀሞ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ የሺ ደበሌና አስኮ ሳንሱሲ ይገኙበታል። የሙከራ ስምሪቱ የጉዞ አቅጣጫቸው በጎን በኩል በተጻፈባቸው 55 አውቶቡሶች የሚጀመር ይሆናል።

ሠራተኞችን ለማጓጓዝ በጊዜያዊነት የአንበሳ አውቶቡስ ፌርማታዎችን እንደሚጠቀሙ አቶ ደረጀ ተናግረዋል። ለጊዜው አገልግሎቱ የሚሰጠው አስፈላጊ የሠራተኞቻቸውን መረጃ ቀድመው ለላኩ መስሪያ ቤት ሠራተኞች ሲሆን፣ ቀስ በቀስ አውቶቡሶችን በመጨመር ሁሉም የፌዴራል ሠራተኞች አገልግሎቱን እንዲያገኙ ይደረጋል።

ዘግይተው የቀረቡ መረጃዎችን በማደራጀትና ጥቆማዎችን ተቀብሎ እርምት በመውሰድ የአውቶቡሶችን ቁጥር በመጨመር አገልግሎቱ እንደሚሻሻልም ተናግረዋል። የአገልግሎቱ መጀመር የመንግሥት ሠራተኞችን ገንዘብ፣ ጊዜና እንግልት ይቀንሳል ብለዋል አቶ ደረጀ።

መስሪያ ቤቶች ሠራተኞች አገልግሎቱን ማግኘት የሚችሉበትን መታወቂያ እየወሰዱ እንደሚገኙ የገለጹት ዋና ሥራ አስኪያጁ መታወቂያውን ያልወሰዱ መስሪያ ቤቶች ከዛሬ ጀምሮ መጥተው እንዲወስዱ አሳስበዋል። ለጊዜው የተሰሩት መታወቂያዎች የሠራተኞቹን መነሻና መድረሻ የጉዞ መስመር ጨምሮ የተለያዩ መረጃዎችን አካተተዋል። ሠራተኛው በተመደበለት አውቶቡስ ብቻ መጠቀም እንደሚገባውም ጠቁመዋል። ወደ ፊት ኤሌክትሮኒክስ መታወቂያዎችን አገልግሎት ላይ እንደሚያውሉም ተናግረዋል።

የትራንስፖርት አገልግሎቱ ሙሉ ለሙሉ ሲጀመር ከፍተኛ የነዋሪ ብዛት ካለባቸው 26 መስመሮች በመነሳት የመንግሥት መስሪያ ቤቶች በብዛት ወደሚገኙባቸው 11 መዳረሻዎች ሠራተኞችን ማጓጓዝ ያስችላል።

*******

ምንጭ፡ አዲስ ዘመን

Curated Content

Content gathered and compiled from online and offline media by Hornaffairs staff based on relevance and interest to the Horn of Africa.

Recent Posts

ኪዳነ ኣመነ – እንደህዝብ አንድ ሆነናል ያስቸገረን የህወሓት አስተሳሰብ ነው

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 2 - ለውጥ…

5 years ago

ኪዳነ አመነ – ለትግራይ ታላቅነት ሼምለስ ሆነን እንሰራለን

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 1 - ለትግራይ…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ትዴት ኢትዮጲያዊ ማንነት ብቻ እንዳለ ነው የሚያምነው (video)

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ (ክፍል 2)- ስለትዴት…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ኢሳት የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ ነው የሰራው (Video)u

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ (ክፍል 1) -…

5 years ago

የበረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ መታሰር -ሕጋዊ ወይስ ፖለቲካዊ እርምጃ?

(የማነ ካሣ) እንደሚታወቀው አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከጥረት ኮርፖሬሽን ጋር በተያያዘ…

5 years ago

ኣስተያየት በ’ኣብራክ’ ልብወለድ ድርሰት ላይ

(መርስዔ ኪዳን - ሚኔሶታ) ኣብራክ የተባለውን የሙሉጌታ ኣረጋዊ መጽሓፍ ኣነበብኩት። ኣገራችን ከሊቅ አስከደቂቅ በዘውጌ ብሄርተኝነት…

5 years ago