Categories: EthiopiaNewsSecurity

በአሶሳ ዞን ታጣቂዎች ዘጠኝ ሰዎች ገደሉ

ትላንት ሚያዚያ 7/2006ዓ.ም ማለዳ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአሶሳ ዞን ሰዎችን ጭኖ ሲጓዝ በነበረ ፒካ አፕ መኪና ላይ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት በሰው ህይወትና አካል ላይ ጉዳት መድረሱን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ገለፀ፡፡

ጽ/ቤቱ ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች በተሽከርካሪው ላይ ጥቃቱን ያደረሱት ከንጋቱ 12 ሰዓት ተኩል አካባቢ፣ የክልሉ ርዕሰ መዲና ከሆነው ከአሶሳ ከተማ 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገ‚ው ሸርቆሌ ወረዳ ልዩ ስሙ ጠይባ ከሚባለው አካባቢ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ዘጠኝ ሰዎች ሲገደሉ በስድስቱ ላይ ደግሞ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑ ታውቋል፡፡

ጥቃቱን ፈፅመው የተሰወሩ ግለሰቦችን አድኖ በህግ ፊት ለማቅረብ የህግ አስከባሪ ኃይሎች ክትትል በማድረግ ላይ መሆናቸውን የገለጸው ጽ/ቤቱ በጥቃቱ ተጠያቂ የሆኑትን ግለሰቦች ማንነት ለማጣራትም ምርመራ መጀመሩን እና የምርመራውን ውጤት የሚመለከቱ መረጃዎችን በወቅቱ ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ ጽ/ቤቱ ጨምሮ ገልጿል፡፡

********

Curated Content

Content gathered and compiled from online and offline media by Hornaffairs staff based on relevance and interest to the Horn of Africa.

Recent Posts

ኪዳነ ኣመነ – እንደህዝብ አንድ ሆነናል ያስቸገረን የህወሓት አስተሳሰብ ነው

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 2 - ለውጥ…

5 years ago

ኪዳነ አመነ – ለትግራይ ታላቅነት ሼምለስ ሆነን እንሰራለን

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 1 - ለትግራይ…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ትዴት ኢትዮጲያዊ ማንነት ብቻ እንዳለ ነው የሚያምነው (video)

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ (ክፍል 2)- ስለትዴት…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ኢሳት የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ ነው የሰራው (Video)u

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ (ክፍል 1) -…

5 years ago

የበረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ መታሰር -ሕጋዊ ወይስ ፖለቲካዊ እርምጃ?

(የማነ ካሣ) እንደሚታወቀው አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከጥረት ኮርፖሬሽን ጋር በተያያዘ…

5 years ago

ኣስተያየት በ’ኣብራክ’ ልብወለድ ድርሰት ላይ

(መርስዔ ኪዳን - ሚኔሶታ) ኣብራክ የተባለውን የሙሉጌታ ኣረጋዊ መጽሓፍ ኣነበብኩት። ኣገራችን ከሊቅ አስከደቂቅ በዘውጌ ብሄርተኝነት…

5 years ago