Categories: EthiopiaNewsRailway

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ፕሮጀክት 56 በመቶ ተጠናቀቀ

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ፕሮጀክት ግንባታ 56 በመቶ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አስታወቀ።

የ7ኛው አገር አቀፍ የከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ጉባኤ ተሳታፊዎች ፕሮጀክቱን ጎብኝተዋል።

በኮርፖሬሽኑ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር በሃይሉ ስንታየሁ እንደገለጹት የሰራው ዋና ዋና የሚባሉት ሰራዎች በመጠናቀቅ ላይ ሲሆኑ ግንባታውም በጥሩ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል።

ከባድ ከሚባሉት ስራዎች ባቡሩ በመሬት ውስጥ ለውስጥና በድልድይ ላይ የሚሄድበትን ግንባታ ማከናወን ሲሆን በመሬት ውስጥ ለውስጥ የሚሄድበት ተጠናቋል። አሁን የፌርማታ ስራ እየተከናወነ ሲሆን እሱም መጪው ክረምት ከመግባቱ በፊት የሚጠናቀቅ ይሆናል ብለዋል።

እንደ ኢንጂነር በሃይሉ ባቡሩ በድልድይ የሚሄድበት በተለይ  ከመስቀል አደባባይ እስከ ኮካ ኮላ ያለው ዋናው ክፍል ግንባታ ተጠናቋል።

ከአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ጋር በቅንጅት የሚሰሩ የሜክሲኮ፣ልደታና ቄራ ቦታዎች በተወሰነ መልኩ የመዘግየት አዝማሚያ የነበረ ቢሆንም በአሁን ወቅት ሙሉ በሙሉ ወደ ግንባታ ተገብቶ በመፋጠን ላይ ይገኛል።

እነዚህ ግንባታዎች ሲጠናቀቁም ድልድይ የመደርደሩ ሰራ እንደሚጀመር ጨምረው ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ፕሮጀክት 39 የመንገደኞች መሳፈሪያና መውረጃ ፌርማታዎች የሚኖሩት ሲሆን በፌርማታዎቹ መካከል የሚኖረው አማካይ ርቀትም እስከ 700 ሜትር ይደርሳል።

ፕሮጀክቱን ከጎበኙት መካከል ኢዜአ ያነጋገራቸው አቶ ማሪያ ወልደ ሚካኤልና አቶ እንድሪስ ኤዶ የተባሉ  ተሳታፊዎች  እንዳሉት የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ፕሮጀክት የከተማይቱ ብሎም የሃገሪቱ ዕድገት አንዱ ማሳያ ነው፤ በግንባታው ሂደትና አጠቃላይ ባዩት ነገርም መደሰታቸውን ገልጸዋል።        

*******

ምንጭ፡- ኢዜአ፣ መጋቢት 4/2006፣ ‹‹የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ፕሮጀክት 56 በመቶ ተጠናቀቀ››

Curated Content

Content gathered and compiled from online and offline media by Hornaffairs staff based on relevance and interest to the Horn of Africa.

Recent Posts

ኪዳነ ኣመነ – እንደህዝብ አንድ ሆነናል ያስቸገረን የህወሓት አስተሳሰብ ነው

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 2 - ለውጥ…

5 years ago

ኪዳነ አመነ – ለትግራይ ታላቅነት ሼምለስ ሆነን እንሰራለን

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 1 - ለትግራይ…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ትዴት ኢትዮጲያዊ ማንነት ብቻ እንዳለ ነው የሚያምነው (video)

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ (ክፍል 2)- ስለትዴት…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ኢሳት የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ ነው የሰራው (Video)u

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ (ክፍል 1) -…

5 years ago

የበረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ መታሰር -ሕጋዊ ወይስ ፖለቲካዊ እርምጃ?

(የማነ ካሣ) እንደሚታወቀው አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከጥረት ኮርፖሬሽን ጋር በተያያዘ…

5 years ago

ኣስተያየት በ’ኣብራክ’ ልብወለድ ድርሰት ላይ

(መርስዔ ኪዳን - ሚኔሶታ) ኣብራክ የተባለውን የሙሉጌታ ኣረጋዊ መጽሓፍ ኣነበብኩት። ኣገራችን ከሊቅ አስከደቂቅ በዘውጌ ብሄርተኝነት…

5 years ago