የሀይማኖቶቸ ጉባኤ የፀረ-አክራሪዎች ሰልፍ ሊያካሂድ ነው

(ፍቃዱ ፈንቴ)

አክራሪዎች በእምነት ስም የህዝብን ሰላም ለማደፍረስ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በመቃወም እሁድ ነሃሴ 26/2005 ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርግ የአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ገለፀ፡፡

ሰልፉ ሁሉም የሀይማኖት ተከታዮች በሰላም አብሮ ለመኖር ያላቸውን ቁርጠኝነት ማሳያ ነው ተብሏል፡፡

ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ በእምነት ስም የሀገሪቱን ሰላም ለማደፍረስ ጥረት የሚያደርጉ አካላትን በመቃወም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተደጋጋሚ ሰላማዊ ሰልፍ መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡

በ10ሩም ክፍለ ከተሞች ውይይት ያደረጉት ነዋሪዎቹ በእምነት ስም የሚደረግ ማንኛውም የአክራሪነት እንቅስቃሴ በመቃዎም ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ እንደሚፈልጉ ለመንግስት ጥያቄ ማቅረባቸውን የአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤት ገልጿል፡፡

የሁሉም ሀይማኖት ተከታዩች በተገኙበት የሚካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ የሀይማኖት ተከታዮቹ አብሮ በሰላም ለመኖር ያላቸውን ቁርጠኝነት ማሳያ መሆኑን የአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤት ቦርድ ሰብሳቢ ርዕሰ ደብር በርሁን አርአያ ገልጸዋል፡፡

የሀይማኖት እኩልነት ባልተከበረበት ወቅት ጭምር ህዝቡ ጠብቆ ያቆየውን የመቻቻልና የአብሮነት እሴት ጥቂት አክራሪዎች ለማደፍረስ መሯሯጣቸውን ለመቃወም ሁሉም የሀይማኖት ተከታዮች በዕለቱ እንደሚሳተፉ ርዕሰ ደብር በርሁን አርአያ ጠቁመዋል፡፡

እሁድ 26/2005 በሚካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ የሁሉም ቤተ እምነት መሪዎች እና ተከታዮቻቸው የሰላም መልእክቶችን በመያዝ ከየአቅጣጫው ወደ መስቀል አደባባይ ያመራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

**********

Source: Aug. 26, 2013 – titled “የአክራሪዎችን እንቅስቃሴ በመቃወም በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ሊካሄድ ነው”

Curated Content

Content gathered and compiled from online and offline media by Hornaffairs staff based on relevance and interest to the Horn of Africa.

Recent Posts

ኪዳነ ኣመነ – እንደህዝብ አንድ ሆነናል ያስቸገረን የህወሓት አስተሳሰብ ነው

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 2 - ለውጥ…

5 years ago

ኪዳነ አመነ – ለትግራይ ታላቅነት ሼምለስ ሆነን እንሰራለን

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 1 - ለትግራይ…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ትዴት ኢትዮጲያዊ ማንነት ብቻ እንዳለ ነው የሚያምነው (video)

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ (ክፍል 2)- ስለትዴት…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ኢሳት የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ ነው የሰራው (Video)u

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ (ክፍል 1) -…

5 years ago

የበረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ መታሰር -ሕጋዊ ወይስ ፖለቲካዊ እርምጃ?

(የማነ ካሣ) እንደሚታወቀው አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከጥረት ኮርፖሬሽን ጋር በተያያዘ…

5 years ago

ኣስተያየት በ’ኣብራክ’ ልብወለድ ድርሰት ላይ

(መርስዔ ኪዳን - ሚኔሶታ) ኣብራክ የተባለውን የሙሉጌታ ኣረጋዊ መጽሓፍ ኣነበብኩት። ኣገራችን ከሊቅ አስከደቂቅ በዘውጌ ብሄርተኝነት…

5 years ago