Ethiopia | ነዳጅ መኖሩን የሚያመላክቱ መረጃዎች ተገኙ

በመላ አገሪቱ በአሁኑ ወቅት ከመቼውም ጊዜ በላይ የነዳጅ ፍለጋ በተጠናከረ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን የማዕድን ሚኒስትሯ አስታወቁ፡፡

በደቡብ ኦሞ ዞን እየተካሄደ ባለው የነዳጅ ፍለጋ ነዳጅ እንዳለ አመላካች የሆኑ መረጃዎች መገኘታቸውን ታሎ ኦይል የተባለው ኩባንያ ይፋ አደረገ፡፡ ይሁንና መረጃዎቹ ተጨማሪ ጥናትና ምርምሮች የሚጠይቁ መሆናቸውን ገልጿል፡፡

የማዕድን ሚኒስትሯ ወይዘሮ ስንቅነሽ እጅጉ በተለይ ለኢዜአ እንደገለጹት ትላልቅ ዓለም ዓቀፍ ኩባንያዎች በመላ አገሪቱ የነዳጅ ፍለጋ በተጠናከረ ሁኔታ እያካሄዱ ናቸው፡፡ በኦጋዴን፣ በዓባይ፣ በጋምቤላና በኦሞ ቤዚን ሰባት ዓለም ዓቀፍ ኩባንያዎች 10 ፈቃዶችን በመውሰድ የነዳጅ ፍለጋ ሥራ በማካሄድ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ታሎ የተባለው ኩባንያ በኦሞ ቤዚን በሚያካሂደው የነዳጅ ጉድጓድ ቁፋሮ የሃይድሮካርበን ምልክቶች ማግኘቱን ጠቅሰው ሥራው ግን ገና ቀጣይነት ያለው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ የነዳጅ ፍለጋውን የሚያካሂደው ኩባንያ ጥሩ የቴክኒክ ብቃት እንዳለው ጠቅሰው በጋና፣ በኡጋንዳና በኬንያ በነዳጅ ፍለጋ ሥራ ላይ ውጤታማ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

እንዲሁም ሳውዝ ዌስት የተባለ ኩባንያ በደገሃቡር አካባቢ፣ ፋልከን የተባለ ኩባንያ በዓባይ ቤዚን ወረኢሉ አካባቢና አፍሪካ ኦይል ኒው ኤጅ የተባለ ኩባንያ ደግሞ ኤርኩራን በተባለ አካባቢ የነዳጅ ጉድጓድ ለመቆፈር በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በደቡብ ኦሞ ዞን እየተካሄደ ባለው የነዳጅ ፍለጋ ነዳጅ እንዳለ አመላካች የሆኑ መረጃዎች መገኘታቸውን ታሎ ኦይል የተባለው ኩባንያ ይፋ አድርጓል፡፡ ይሁንና መረጃዎቹ ተጨማሪ ጥናትና ምርምሮች የሚጠይቁ መሆናቸውን ገልጿል፡፡

የኩባንያው የኮርፖሬት ጉዳዮች ከፍተኛ አማካሪ አቶ ሲሳይ ዘሪሁን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ሳቢሳ ተብሎ በተሰየመው የነዳጅ ፍለጋ ጉድጓድ በጠቅላላው 1 ሺህ 810 ሜትር ቁፋሮ ተካሂዷል፡፡ በቁፋሮው ሂደት ነዳጅ መኖሩን የሚያመላክቱ መረጃዎች በክሌይ ስቶን በተሸፈነ አሸዋ ውስጥ መስተዋሉን አስታውቀዋል፡፡

ይሁንና የጉድጓዱ ውስብስብነትና አስቸጋሪነት መነሻ በማድረግ የተሟላ መረጃ ለማግኘት የጎንዮሽ መቆፈር አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን ገልጸዋል፡፡ እንደ አቶ ሲሳይ ገለጻ የነዳጅ ፍለጋው የጎንዮሽ ቁፋሮ በአሁኑ ወቅት በመካሄድ ላይ ሲሆን በግንቦት ወር አጋማሽ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የታሎ ኦይል የኤክስፕሎሬሽን ዳይሬክተር ሚስተር አንገስ ማኮስ እንደገለጹት የሳቢሳ ጉድጓድ በቴክኒክ ረገድ እጅግ አስቸጋሪና ውስብስብ ሲሆን ይህ ደግሞ በፍሮንቲየር ቤዚኖች ላይ ብዙ ጊዜ የሚያጋጥም ነው፡፡ የጉድጓዱ አስቸጋሪነት ወደ ጎን እንድንቆፍርና ፍንጩ በታየበት ጥልቀት አካባቢ ናሙና ለመውሰድ አስገድዷልያሉት ሚስተር ማኮስ በደቡብ ኦሞ ዞን ሊሰራ የሚችል የነዳጅ ዑደት መኖሩ እንዳበረታታቸው ገልጸዋል፡፡

በመላ አገሪቱ አሥር ያህል ፈቃዶችን በመውሰድ የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋ በማካሄድ ላይ የሚገኙት ታሎ ኦይል፣ አፍሪካ ኦይል፣ ፔክሲኮ፣ ሳውዝ ዌስት ኢነርጂ፣ አፋር ኤክስፕሎሬሽን፣ ኒው ኤጅና ፋልከን የተባሉ ኩባንያዎች ናቸው::

**********

Source: Ethiopian News Agency – April 19, 2013. Originally titled “አገሪቱ የነዳጅ ፍለጋ በተጠናከረ ሁኔታ እየተካሄደ ነው፤ በደቡብ ኦሞ ነዳጅ እንዳለ አመላከች መረጃዎች ተገኙ”

9.14540.489673
Daniel Berhane

Daniel Berhane

Recent Posts

ኪዳነ ኣመነ – እንደህዝብ አንድ ሆነናል ያስቸገረን የህወሓት አስተሳሰብ ነው

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 2 - ለውጥ…

5 years ago

ኪዳነ አመነ – ለትግራይ ታላቅነት ሼምለስ ሆነን እንሰራለን

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 1 - ለትግራይ…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ትዴት ኢትዮጲያዊ ማንነት ብቻ እንዳለ ነው የሚያምነው (video)

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ (ክፍል 2)- ስለትዴት…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ኢሳት የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ ነው የሰራው (Video)u

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ (ክፍል 1) -…

5 years ago

የበረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ መታሰር -ሕጋዊ ወይስ ፖለቲካዊ እርምጃ?

(የማነ ካሣ) እንደሚታወቀው አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከጥረት ኮርፖሬሽን ጋር በተያያዘ…

5 years ago

ኣስተያየት በ’ኣብራክ’ ልብወለድ ድርሰት ላይ

(መርስዔ ኪዳን - ሚኔሶታ) ኣብራክ የተባለውን የሙሉጌታ ኣረጋዊ መጽሓፍ ኣነበብኩት። ኣገራችን ከሊቅ አስከደቂቅ በዘውጌ ብሄርተኝነት…

5 years ago