ጡረታ አልባው የተቃውሞ ፖለቲካ በብዥታ ውስጥ

(በኃይሉ ሚዴቅሳ)

(በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ነጭነጩን ስለገለጽን እባክዎትን ከስሜት ጸድተው ያንብቡ)

መቼም ‹‹ዓብይን እወደዋለሁ›› የማይል ሰው የለም፡፡ አሁን እርሱን አልወደውም ማለት በራሱ እያስወነጀለ ነው፡፡ የሚወነጅለው ሕዝቡ ነው፡፡ ሕዝብ ጨቋኝ ሲሆን ዴሞክራሲ አፈር ይበላል፡፡

ለማንኛውም ‹‹ዓብይን አለማድነቅ አይቻልም፤ በፈረዖን ቤት ያደገ ሙሴ ነው፤›› ወዘተ እየተባለ መነገር ተለምዷል፡፡ ለምን እንደወደደው ሲናገር ግን ከዕውቀት ይልቅ ስሜት የተጫነው ማብራሪያ ከመስጠት የተለየ በተን ያለ ሳይንሳዊ ገለጻ አያደርግም፡፡

በዚህ ረገድ ቋሚ የኢሕአዴግ ተቃዋሚዎች ብሰዋል፡፡ ኢሰፓም በላቸው ኢሕአፓ፣ ቅንጅትም በለው ግንቦት ሰባት ከኢሕአዴጎች በላይ የኢሕአዴጉን ሊቀመንበር ‹አፍቅረውት› ሊሞቱ ነው፡፡ ይህ በዕውነቱ ጥሩ ነው፡፡ ወደ አንድ ዓይነት ‹ሪዞሊውሽን› መምጣት ለአገር ይጠቅማል፡፡

ግን እነርሱ ዓብይን የማድነቅና የመውደድ መብት እንዳላቸው ሁሉ ሌላውም ሰው የመቃወም መብት እንዳለው መርሳት የለባቸውም፡፡ እነዚህ ነባር የኢሕአዴግ ተቋዋሚዎች በኢሕአዴጉ ሊቀመንበር ምክንያት ኢሕአዴግን ቢደግፉ የሚገርም ቢሆንም፣ እንዳልኩት ወደ አንድ የፖለቲካ ማኅበረሰብ ውስጥ መሰባሰብ መቻላችን ጥሩ ነው፡፡

ነገር ግን ተቀዋሚው ኃይል አሁን እርባና ቢስ የገደል ማሚቶ መሆኑ ተገረጋግጧል፡፡ በውጭም በሀገር ውስጥም ያለው ተቃዋሚ ከዚህ ወቅት የተሻለ አጋጣሚ አይኖረውም ነበር፡፡ ሕዝብ ታግሎ ያመጣላቸውን ሰሞነኛ ነጻነት ተጠቅመው ተግባራዊ የሆነ እንቅስቃሴ ማድረግ አልቻሉም፡፡ የእነሱን ጥያቄ የኢሕአዴጉ ሊቀመንበር እያቀነቀኑት ነው፡፡

‹‹የጀግና አገሩ እስር ቤት ነው፤ ጀግናችን እከሌ ይፈታ፤ አቶ እከሌ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው፤ ቃሊቲና ማዕከላዊ ይዘጉ …›› በሚል ቅስቀሳ ላይ የተመሠረተ ተቃዋሚ ድሮም ዋጋ የሌለው መሆኑ የታመነ ነው፡፡ ግቡን እስረኛን ማስፈታትና እስር ቤትን ማዘጋት አድርጎ የከረመ ተቃዋሚ ከዚህ በኋላ ሊቀጥል እንደማይችል ይታወቃል፡፡

መርህና ርዕዮተ-ዓለም ላይ ያልተመሠረተው የተቃዋሚው ጎራ የተቃውሞ ፖለቲካ የአፈጻጸም አጀንዳውን ኢሕአዴግ ቀምቶታል፡፡ ሙሉ በሙሉ ጥያቄዎችን መልሷቸዋል፡፡

ተቃዋሚው በዘርና በቀበሌ ሲደራጅ፣ ኢሕአዴግ በኢትዮጵያዊነት መርህ ተመልሶ መጣ፡፡ ኢሕአዴግ እስር ቤቱንም ዘጋው፤ እስረኛውንም ፈታው፡፡ ከዚህ በኋላ ተቃዋሚው የሚሆነው ነገር እንደሌለው ታውቋል፡፡

ስደተኛ ፖለቲከኞችም ከዚህ የተሻለ ነገር የላቸውም፡፡ በዘር ተቧድኖ፣ ቤተክርስቲያንን ሳይቀር በብሔር ከፋፍሎ፣ የሰንበት ፖለቲካውን በሳይበርና በቴሌቭዥን ላይ ሲቀድ የሚውል ስደተኛ ፖለቲከኛ፣ በየሆቴሉ እየሄደ የመንግሥትን ባለሥልጣናት መሳደብን እንደ ድል የሚቆጥር የእረፍት ቀን ፖለቲከኛ፣አሁን ግራ ገብቶታል፡፡

በጥላቻና በምቀኝነት ላይ ብቻ የተመሠረተው የዚህ ቡድን ፖለቲካ ዋጋ አጥቷል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አሕመድ እንዳሉት 23ሺህ የቀይ ሽብር ወንጀለኞች በሰሜን አሜሪካና አውሮጳ ይኖራሉ፡፡

ይህ የቀይ ሽብር ስደተኛና በ1997 ዓ.ም ፖለቲካ፣ ዜግነት ቀይሮ እንግሊዛዊና አሜሪካዊ የሆነ ፖለቲከኛ ሁሉ ለኢትዮጵያ አስብላታለሁ ሲል የከረመው በጥላቻና ምቀኝነት ላይ ተመሥርቶ እንደነበር ተጋልጧል፡፡ ሥር የሠደደ ርዕዮተ-ዓለም ስላልነበረው ኢሕአዴግ አጀንዳውን ቀማው!

በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ከወሰኑት ውሳኔ አንዱ ነባር የኢሕአዴግ ባለሥልጣናትን በጡረታ ማሰናበት ነው፡፡ ይህ ተገቢ ነው፡፡ አዲሱ ትውልድም (እንደ ዓብይ ያለው) ሊሞከርና ዕድል ሊሰጠው ይገባል፡፡

ግን ተቃዋሚዎችን የሚመሩት ሰዎች ጡረታ የሚወጡት መቼ ነው? አንዳርጋቸው ጽጌ እኮ የዓባይ ፀሐዬ ባች ናቸው፡፡ አቶ አባይ ማገብት የተባለውን ድርጅት ለመመስረት አምባሳደር ካፌ ሲዶልቱ እኮ፣ አቶ አንዳርጋቸው ኢሕአፓን ተቀላቅለው በኢሕአወሊን ጥናት ክበባት ውስጥ ይውሉ ነበር፡፡

ካሱ ኢላላና ብርሃኑ ነጋም እኮ የአንድ ሰሞን ትውልዶች ናቸው፡፡ ዶ/ር ካሱ የኢሕአፓ አባል ሆነው ትግል ሲመሰርቱ እኮ፣ ዶ/ር ብርሃኑ የኢሕአፓ አመራሮች (ዶ/ር ተሥፋዬ ደበሳይ) ሹፌር ነበሩ፡፡ እኩል ነው ኢሕአፓን የተላቀሉት፡፡ አቶ ታደሰ ኃይሌና ዶ/ር መረራ ጉዲና በምን እንደሚበላለጡ እንዴት ማብራራት ይቻላል…? በየነ ጴጥሮስ ከሥብሓት ነጋ በምን ያህል እድሜ ይበላለጣሉ?

የኢሕአዴግ ሰዎች በሊቀመንበራቸው አማካኝነት ጡረታ እንዲወጡ ተደረገ፡፡ የተቃውሞውን ጎራ የሚመሩት ሰዎች ግን ከ1964 ዓ.ም ጀምሮ ፖለቲካው ላይ አሉ፡፡ ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ የድርጅቶቻቸው ሊቀመንበር ሆነው የቀጠሉ ሰዎች መቼ ነው? ለአዳዲስ ትውልድና ለአዳዲስ አስተሳሰብ ዕድል የሚሠጡት…? ምክትል ሊቀመንበራቸው እንኳ ሳይታወቅ አሁንም ፓርቲ የሚመሩ ሰዎች ጡረታ ይወጡ ዘንድ የሚጠይቅ አባልም የለም፡፡

********

Guest Author

Guest Author

Recent Posts

ኪዳነ ኣመነ – እንደህዝብ አንድ ሆነናል ያስቸገረን የህወሓት አስተሳሰብ ነው

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 2 - ለውጥ…

5 years ago

ኪዳነ አመነ – ለትግራይ ታላቅነት ሼምለስ ሆነን እንሰራለን

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 1 - ለትግራይ…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ትዴት ኢትዮጲያዊ ማንነት ብቻ እንዳለ ነው የሚያምነው (video)

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ (ክፍል 2)- ስለትዴት…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ኢሳት የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ ነው የሰራው (Video)u

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ (ክፍል 1) -…

5 years ago

የበረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ መታሰር -ሕጋዊ ወይስ ፖለቲካዊ እርምጃ?

(የማነ ካሣ) እንደሚታወቀው አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከጥረት ኮርፖሬሽን ጋር በተያያዘ…

5 years ago

ኣስተያየት በ’ኣብራክ’ ልብወለድ ድርሰት ላይ

(መርስዔ ኪዳን - ሚኔሶታ) ኣብራክ የተባለውን የሙሉጌታ ኣረጋዊ መጽሓፍ ኣነበብኩት። ኣገራችን ከሊቅ አስከደቂቅ በዘውጌ ብሄርተኝነት…

5 years ago