የቅማንት የህዝበ ውሳኔ የጊዜ ሰሌዳና አፈፃፀም ላይ እየተመከረ ነው

(የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ)

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የአማራና ቅማንት ህዝቦች ተቀላቅለው የሚኖርባቸው 12 ቀበሌዎች ህዝበ ውሳኔ እንዲያካሂድ በፌዴሬሽን ምክር ቤት በቀረበለት ጥያቄ መሰረት በማድረግ ቅድመ ዝግጅቶች መጀመሩ የቦርዱ ሰብሳቢ ክቡር ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ገለፁ።

ባሳለፍነው ወር የቦርዱ ፅ/ቤቱ የቴክኒክ ጉዳዮችን ለመመርመር አንድ ቡድን ወደ ቦታው በመላክ የቅድመ ዝግጅት ዳሰሳ ማካሄዱንና ስንት ምርጫ ጣቢያዎች ማቋቋም እንዳለበትና ስንት የምርጫ አስፈፃሚዎችና የህዝብ ታዛቢዎች ማሰማራት እንዳለበት መለየቱን ቦርዱ አሳውቋል።

የአሁኑ ስብሰባም በህዝበ ውሳኔ አፈፃፀም የጊዜ ሰሌዳ ረቂቅ ላይ ለመመካከርና የአማራና ቅማንት ህዝቦች ተቀላቅለው በሚኖርባቸው 12 ቀበሌዎች በሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ የአፈፃፀም ማብራሪያ ላይ ከክልሉ መስተዳድር አካላት እና በክልሉ የተዋቀሩ የሁለቱ ህዝቦች የጥምር ኮሚቴ አባላት ጋር ጥልቅ ውይይት ተካሂዷል።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ይርሳው ታምሬ በአካባቢው የነበሩትን ጥያቄዎች አብዛኛዎቹ ከህዝብ ጋር በመወያየት፣ በመግባባት እና በመተማመን የተፈቱ መሆናቸውን በማስታወስ ህዝበ ውሳኔ የሚካሄድባቸው 12 ቀበሌዎች ግን በህዝብ ውሳኔ መፍትሄ እንዲያገኙ በሁለቱ ወገኖች ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ጥያቄ መቅረቡን አስታውሰዋል፡፡

ምርጫ ቦርዱ በነዚህ አካባቢዎች ለሚያካሂደው ህዝበ ውሳኔ አስፈላጊውን ትብብርና ድጋፍ እንደሚደረግና ህዝበ ውሳኔው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ እምነት እንዳላቸው ተናግሯል። በመቀጠልም የሁለቱ ህዝቦች በሰላም አብሮ የመኖር ታሪካቸውን የሚያጠነክርና የሚያጎለብት ህዝበ ውሳኔ እንደሚሆን ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

በሁለቱ ህዝቦች ለዘመናት የዘለቀውን ተቻችሎና ተግባብቶ አብሮ የመኖር ግንኙነትና ዝምድና የሚጠናከርበት፣ ችግሮች ተወግደው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማታቸው የሚጎለብትበት፣ የህዝቦቹ ዘላቂ ሰላምና ብልፅግና የሚረጋገጥበት ህዝበ ውሳኔ እንዲሆን የበኩላቸውን እንደሚወጡ የመድረኩ ተሳታፊዎች አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ መንግሥት አንቀጽ 102 እና በተሻሻለው የኢትዮጵያ የምርጫ ሕግ አዋጅ ቁጥር 532/1999 ዓ.ም. መሠረት የተቋቋመ ተቋም ነው።

ቦርዱ ግዙፍ ሕዝባዊና ሕገ-መንግሥታዊ ኃላፊነት ተሸክሞ ወደ ሥራ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ በየአምስት ዓመቱ በተከታታይ የሚካሄዱ ምርጫዎችን የጠቅላላ ምርጫ አምስት ጊዜ፣ የአካባቢ ምርጫ አምስት ጊዜ እንዲሁም በተለያዩ ደረጃ የምርጫ ዓይነቶች ማለትም የማሟያ ምርጫ፣ ድጋሜ ምርጫ እና ህዝበ-ውሳኔዎችን ነፃ፣ ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እንዲሁም በህዝብ ዘንድ ተዓማኒ ሆነው እንዲጠናቀቁ በማድረግ በርካታ ልምድ ያካበተ ተቋም ነው።

ህዝበ ውሳኔ ማለት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት ሲወሰን የህዝብ ፍላጎትን ለመለካት እና የህዝብን ውሳኔ ለማወቅ ድምፅ የሚሰጥበት ስርዓት ነው። በዚሁ መሰረት ቦርዱ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ የህዝበ ውሳኔ ምርጫዎችን በብቃት በማካሄድ የህዝቦችን የሉዓላዊ ስልጣን ባለቤትነትን አረጋግጧል።

ለአብነት ለመጥቀስ የቤጊ ህዝብ ህዝበ ውሳኔ፣ በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ አዋሳኝ ቀበሌዎች፣ እንዲሁም በኦሮሚያ እና በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልሎች አዋሳኝ በሆኑት ቀበሌዎች ላይ የተካሄዱ ህዝበ ውሳኔዎች ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መጠናቀቃቸውን ይታወሳል።

***********

Curated Content

Content gathered and compiled from online and offline media by Hornaffairs staff based on relevance and interest to the Horn of Africa.

Recent Posts

ኪዳነ ኣመነ – እንደህዝብ አንድ ሆነናል ያስቸገረን የህወሓት አስተሳሰብ ነው

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 2 - ለውጥ…

5 years ago

ኪዳነ አመነ – ለትግራይ ታላቅነት ሼምለስ ሆነን እንሰራለን

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 1 - ለትግራይ…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ትዴት ኢትዮጲያዊ ማንነት ብቻ እንዳለ ነው የሚያምነው (video)

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ (ክፍል 2)- ስለትዴት…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ኢሳት የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ ነው የሰራው (Video)u

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ (ክፍል 1) -…

5 years ago

የበረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ መታሰር -ሕጋዊ ወይስ ፖለቲካዊ እርምጃ?

(የማነ ካሣ) እንደሚታወቀው አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከጥረት ኮርፖሬሽን ጋር በተያያዘ…

5 years ago

ኣስተያየት በ’ኣብራክ’ ልብወለድ ድርሰት ላይ

(መርስዔ ኪዳን - ሚኔሶታ) ኣብራክ የተባለውን የሙሉጌታ ኣረጋዊ መጽሓፍ ኣነበብኩት። ኣገራችን ከሊቅ አስከደቂቅ በዘውጌ ብሄርተኝነት…

5 years ago