የኢትዮጽያን ታሪክ በተመለከተ ከአቶ ለማ መገርሳ አንደበት – የኦህዴድ ሊቀመንበርና የኦሮሚያ ፕሬዝዳንት(+Video)

የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ ከባለሀብቶች ጋራ በኦሮሞ ባህል ማዕከል ያደረጉት ውይይት (ሚያዝያ 12፣ 2009 ዓ.ም.)

“…80፤ 60፤ 100 እና 3ሺህ ዓመት እየቆጠርን፣ ያ ትውልድ እኮ የመሰለውን ሰርቶ አልፏል። ጥሩም ይሁን መጥፎ በመሰለው መንገድ የራሱን ግዴታ ተወጥቶ አልፏል። እኛ ሌላ ትውልድ እኮ ነን! ለምን የራሳችንን ታሪክ አንሰራም? የራሳችንን ታሪክ! ሁልጊዜ ወደኋላ በማየት ወደፊት መራመድ አንችልም። ተደናቅፈን እንወድቃለን…”

“…የኋላውን ጥሩም ይሁን መጥፎ ለታሪክ እንተወው! ዛሬ ያለን ትውልድ የራሳችንን ታሪክ አዲስ ታሪክ እንስራ። አዲስ ታሪክ፤ እኛም የማናፍርበት የነገውም ትውልድ እኛ የሰራነውን እንደ ጥሩ ተምሳሌት ወሰዶ የራሱን ታሪክ የሚሰራበት የራሳችን አዲስ ታሪክ እንስራ…”

“…በየመንደሩ መናቆሩ፤ ታሪክ እየቆጠሩ፤ አንድ አንዱ Fabrications… Fabrications! እውነት ይሁን ውሸት በማናውቀው ባላየነው ባልጨበጥነው ማረጋገጫ መናቆሩ አይጠቅመንም። ይበትነናል ይጎዳናል። ነቀርሳ ነው፤ Cancer…”

“…የኛም የልጆቻችንም ዋስትና ይሀ ነው። ይቅርና በየመንደሩ ተከፋፍለን አንድም ሆነን ዳገቱን መግፋት አልቻልንም። አለም ወዶ Globalization… አይደለም ወደ አንድ መንደር፤ ሳይፈላለግ መፈላለግ የጀመረው፣ ሳይፈላለግም መተቃቀፍን የመረጠው ወዶ አይደለም። ያ ሊታየን ካልቻለ ያ ካልተገለጠልን፤ ጨለማ ውስጥ ተጉዘን ልንለወጥ ልናድግ አንችልም…”

“…ምንጊዜም ሁላችንም መሳት የሌለብን: ለዚህች ሀገር አንድነት ለሀገራችን ለውጥ፤ በዬትም እንሰማራ በዬትም እንሂድ በዬትም እንግባ እንውጣ… ለዚህች ሀገር አንድነት ለሀገራችን ለውጥ ማሰብ መስራት መትጋት! በውስጣችን እየገባ ልዩነታችንን ሊያጎላ የሚፈልገው ላይ ደግሞ ሳንሸማቀቅ ፊት ለፊት መቃወም: መታገል አለብን። ይጎዳናል! ሰው በሽታ በላዩ ላይ ሲያይ ሃኪም ቤት ሄዶ ነው የሚታከም እንጂ ነገ እኮ እንደሚገድል አያይም፡ ይገድላል…”

“…ሁላችንም አንድ ሀገር ነው ያለን፣ ኦሮሚያም የራሳችሁ ሀገር ነው። ኦሮሚያ ስለተባለ ከሌላ ዓለም የተፈጠረ ደሴት አይደለም። በሙሉ ነጻነት፣ በሙሉ Confidence ስራችሁን መስራት ነው፣ ያ ነው ሀገራችንን ሊቀይር የሚችለው…”

“…እንደ መንግስትም፣ እንደ ኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ይሀን ህዝብ ለመምራት ሀላፊነት እንደወሰድን አካላት፤ ከመራን ይሀን ህዝብ በዚህ ቅኝት እና ቅኝት፣ በዚህ Compass ነው። ሌላ መንገድ እና መሰመር የለንም። ሌላ ሀገርን የመቀየር ፍልስፍና የለንም። እንድ እና አንድ ነው። በዚህ ላይ መስማማት አለብን። ስንነጋገርም አብረን ስንሰራም ከልብ በዚህ ደረጃ ተነጋግረን ነው መስራት ያለብን። የኔ ትልቁ መልእከት ይሀ ነው…”

****** 

Watch the video:

 

Abdulbasit Abdusemed

Abdulbasit Abdusemed

Recent Posts

ኪዳነ ኣመነ – እንደህዝብ አንድ ሆነናል ያስቸገረን የህወሓት አስተሳሰብ ነው

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 2 - ለውጥ…

5 years ago

ኪዳነ አመነ – ለትግራይ ታላቅነት ሼምለስ ሆነን እንሰራለን

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 1 - ለትግራይ…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ትዴት ኢትዮጲያዊ ማንነት ብቻ እንዳለ ነው የሚያምነው (video)

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ (ክፍል 2)- ስለትዴት…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ኢሳት የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ ነው የሰራው (Video)u

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ (ክፍል 1) -…

5 years ago

የበረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ መታሰር -ሕጋዊ ወይስ ፖለቲካዊ እርምጃ?

(የማነ ካሣ) እንደሚታወቀው አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከጥረት ኮርፖሬሽን ጋር በተያያዘ…

5 years ago

ኣስተያየት በ’ኣብራክ’ ልብወለድ ድርሰት ላይ

(መርስዔ ኪዳን - ሚኔሶታ) ኣብራክ የተባለውን የሙሉጌታ ኣረጋዊ መጽሓፍ ኣነበብኩት። ኣገራችን ከሊቅ አስከደቂቅ በዘውጌ ብሄርተኝነት…

5 years ago