የአራቱ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ፈተናዎች

(በብአዴን/ኢህዴን 35ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ የጻፍኩት)

የህወሓት ፈተና – ‹‹የታገልኩት፣ የቆሰልኩት፣ የሞትኩትም እኔ ብቻ ነኝ እና የታሪኩ ባለቤትም የትግሉ ውጤት ይበልጥ ተጠቃሚም መኾን ያለብኝ እኔ ነኝ››። ይህ ትርክት ጫፍ ሄዶ ሄዶ ኢዲሞክራሲያዊነት እና ጠባብነት የወለደው ኾኖ ወደ ትምክህተኝነት ሊያድግ ይችላል። ኣብዛኞቹ የዚህ ፈተና ሰለባ የኾኑ የድርጅቱ ኣባሎች ብ1993ቱ የድርጅቱ የውስጥ ትግል የተሸኙ ሲኾን የነሱ ደጋፊዎች እዚሁ የማሕበረሰብ ሚዲያ ላይ የሚያሳዩት ትምክህት አሁንም አለ። ድርጅቱ የዚህ አይነቱ አዝማሚያ ዋናው ፈተናው ሲኾን በቀጣይ የቀሩ ትርፍራፊ የማጽዳት ስራዉን አጠናክሮ የማካሄድ ሓላፊነት አለበት። ይህንን ፈተና ተቋቁሞ እኩልነት በመቀበል የታገልነው በጋራ እና ለጋራ ጥቅም ነው በማለት እዚህ ለበቃ አብዛኛው አባሉን በዚህ አስተሳሰብ ዙሪያ ማሰለፍ ከቻለ ህወሓት ውጤታማ ይኾናል።

ብአዴን፦ ያለፉ ስርዓቶች፣ በተለይ የአጼኣዊው የዘውድ ስርዓት፣ ናፍቆት። ይህ በእኩልነት ያለማመን የአንዳንድ የብአዴን ትልቁ ፈተና ነው። የጥንት ታሪኮች የአንድ ብሔር ይኾኑ ዘንድ የመመኘት ከዚህ በዘለለም የትምክህት ሃይሉ የሚያራምደው በአለፉት ስርአቶች የተፈጸሙ በደሎች የመካድ አዝማሚያ። ብአዴን የዚህ አይነቶቹ አባላት ሽኝቶ ብቻ ሳይኾን የተፈጠረው አዲስ የኢትዮጵያዊነት የእኩልነት ትርጉም አልጥም ብሏቸው ወደ ድሮ አመለካከታቸው በመኮብለል ብዙ አባላቶቹ እና አመራሮች ሳይቀር ከመስመሩ ወጥተዋል። አንዳንዶቹ ወደ ትክክለኛ ቀለማቸው በመሄድ ፓርቲዎች አቋቁመው ብአዴንን ዞረው ታግለዉታል። ይህንን ፈተና ተቋቁሞ የጋራ ሀገር ነው ያለን የልፉት ስርዕእቶች ሁላችንንም በድለዋል። እነዚህ ስርዓቶች ላይመለሱ በተባበረ ክንድ ተወግደዋል። ስርዓቶቹን ለማስወገድ የአማራ ብሔር ተወላጆችም አኩሪ ተጋድሎ መፈጸማቸውን ማስተማር እና በአስተሳሰቡ ዙሪያው አባላቶቹን ማሰለፍ ከቻለ ብአዴን ትልቅ ድል ማስምዝገብ ይችላል።

ኦህዴድ፦ የዚህ ድርጅት ፈተና ጠባብነት እና ያለፉ ስርዓቶች በደል ላይ ሙጥኝ የማለት ነው። በኦነግ የተነደፉ ትርክቶች ተከትሎ የመንጎድ አዝማሚያዎች ያላቸው አባላት ይታዩበታል። አንዳንዴ ገንፍለው በመውጣት የድርጅቱን ህልውና አድጋ ውስጥ እስከ መክተት ላይ ይደርሳሉ። ላለፉት ስርዓቶች በደል አሁን ላይ የመበቀል መንፈስም በአንዳንድ አባሎቹ ይስተዋላል። እነዚህን አዝማሚያዎችን በመታገል፣ አሁን በመፈቃቀድ እና እኩልነት ላይ የተመሰረተች ኢትዮጵያ የተቀበለ እና ያለፉት ስርዓቶች በደል እንዳይደገሙ በመታገል፣ ሕብረ ብሄራዊት እና በዜጎች መፈቃቀድ ላይ የተመሰረት አንድነት ያላት ኢትዮጵያ ተጠናክራ እንድትቀጥል የማድረግ አስተሳሰብ አባላቶቹ እንዲያዳብሩ ማድረግ ከቻለ ፈተናውን በሚገባ መሻገር የቻለ ድርጅት ተብሎ በሌሎች አባል ድርጅቶች የሚታይ መሰል አዝማሚያ የመታገል አብነት ይኾናል።

ደኢህዴን፦ ከሚያጋጥሙት የተሻሉ ፈተናዎች አንጻር የተሻለ የኢህአዴግ አባል ድርጅት ነው ማለት ይቻላል። እርግጥ ቀላል የሚባል ፈተና የለም። ኦህዴድ የሚያጋጥሙት በአለፉ በደሎች ላይ ሙጥኝ የማለት እና የጠባብ አመለካከቶች አዝማሚያ በአንዳንድ አባሎቹ አልፎ አልፎ ይታያል። የፖለቲካ አቅሙን አጠናክሮ በቂ አመራሮች ማፍራት ከቻለ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ ሕብረ ብሔራዊነት ተስፋ የሚኾን የኢህአዴግ አባል ድርጅት ነው ማለት ይቻላል።

መልካም በዓል ለብአዴን/ኢህአዴግ!

***********

Alula Solomon

Alula Solomon

Recent Posts

ኪዳነ ኣመነ – እንደህዝብ አንድ ሆነናል ያስቸገረን የህወሓት አስተሳሰብ ነው

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 2 - ለውጥ…

5 years ago

ኪዳነ አመነ – ለትግራይ ታላቅነት ሼምለስ ሆነን እንሰራለን

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 1 - ለትግራይ…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ትዴት ኢትዮጲያዊ ማንነት ብቻ እንዳለ ነው የሚያምነው (video)

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ (ክፍል 2)- ስለትዴት…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ኢሳት የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ ነው የሰራው (Video)u

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ (ክፍል 1) -…

5 years ago

የበረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ መታሰር -ሕጋዊ ወይስ ፖለቲካዊ እርምጃ?

(የማነ ካሣ) እንደሚታወቀው አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከጥረት ኮርፖሬሽን ጋር በተያያዘ…

5 years ago

ኣስተያየት በ’ኣብራክ’ ልብወለድ ድርሰት ላይ

(መርስዔ ኪዳን - ሚኔሶታ) ኣብራክ የተባለውን የሙሉጌታ ኣረጋዊ መጽሓፍ ኣነበብኩት። ኣገራችን ከሊቅ አስከደቂቅ በዘውጌ ብሄርተኝነት…

5 years ago