ዶ/ር መረራ ጡረታ እንዲወጡ እንደተጠየቁና ጥያቄውን እንዳልተቀበሉት ተናገሩ

ላለፉት 28 ዓመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት ያገለገሉት ዶ/ር መረራ ጉዲና ከኮንትራት ቅጥር አፈፃፀም ጋር በተያያዘ ከዩኒቨርሲቲው ጋር አለመስማማታቸው ታወቀ።

ዶ/ር መረራ ስለጉዳዩ ከሰንደቅ ጋዜጣ ተጠይቀው ካለፈው ሐምሌ ወር 2006 ዓ.ም ጀምሮ ጡረታ እንዲወጡ እንደተጠየቁና ጥያቄውን እንዳልተቀበሉት ተናግረዋል።

ለዚህም የሰጡት ምክንያት አንድ ለጡረታ የደረሰ ሰው ሦስት ዓመት እንዲራዘምለት መጠየቅ የሚችልበት የሕግ አግባብ ስላለ ነው ብለዋል። ከሐምሌ 2006 ዓ.ም ጀምሮ የዩኒቨርሲቲው የሶሻል ሳይንስ ኮሌጅ በኮንትራት እንዲሰሩ የቀጠራቸው መሆኑን አስታውሰው ሆኖም የዩኒቨርሲቲ ፐርሶኔል ክፍል ቅጥሩን አልቀበልም በማለቱ እስካሁን ጉዳዩ በእንጥልጥል ላይ መሆኑን ገልፀዋል።

በዩኒቨርሲቲው የሴኔት ሕግ መሠረት ኮሌጆቹ የሚፈልጉትን መምህር የመቅጠር መብት እንዳላቸው በማስታወስ የፐርሶኔል ክፍሉ በማያገባው ገብቶ ቅጥሩን ከልክሏል ብለዋል።

ከዚሁ አለመግባባት ጋርም ተያይዞ ላለፉት ስድስት ወራት ደመወዛቸው መቋረጡን ጠቅሰው፤ ከዩኒቨርሲቲው ጋር ያላቸውን ሁኔታ ተከታትለው መፍትሄ ከጠፋ መብታቸውን በሕግ ለማስከበር ማሰባቸውን ጨምረው ገልፀዋል።

በጉዳዩ ላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም። ዶ/ር መረራ ጉዲና ከዩኒቨርሲቲው መባረራቸውን ሰሞኑን በአንዳንድ ማኅበራዊ ድረገጾች መዘገቡም አይዘነጋም።

*******

ምንጭ፡- ሰንደቅ፣ ታህሳስ 22-2007

Curated Content

Content gathered and compiled from online and offline media by Hornaffairs staff based on relevance and interest to the Horn of Africa.

Recent Posts

ኪዳነ ኣመነ – እንደህዝብ አንድ ሆነናል ያስቸገረን የህወሓት አስተሳሰብ ነው

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 2 - ለውጥ…

5 years ago

ኪዳነ አመነ – ለትግራይ ታላቅነት ሼምለስ ሆነን እንሰራለን

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 1 - ለትግራይ…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ትዴት ኢትዮጲያዊ ማንነት ብቻ እንዳለ ነው የሚያምነው (video)

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ (ክፍል 2)- ስለትዴት…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ኢሳት የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ ነው የሰራው (Video)u

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ (ክፍል 1) -…

5 years ago

የበረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ መታሰር -ሕጋዊ ወይስ ፖለቲካዊ እርምጃ?

(የማነ ካሣ) እንደሚታወቀው አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከጥረት ኮርፖሬሽን ጋር በተያያዘ…

5 years ago

ኣስተያየት በ’ኣብራክ’ ልብወለድ ድርሰት ላይ

(መርስዔ ኪዳን - ሚኔሶታ) ኣብራክ የተባለውን የሙሉጌታ ኣረጋዊ መጽሓፍ ኣነበብኩት። ኣገራችን ከሊቅ አስከደቂቅ በዘውጌ ብሄርተኝነት…

5 years ago