ዓባይ ወልዱ፡- ህወሓትን ለድል ያበቃው የውጭና የሌሎች ድጋፍ ሳይሆን የጠራ ሕዝባዊ መስመር ነው

«ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት ) እና የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ ጭቁን ህዝቦች ጋር በመሆን ያካሄዱትን የትጥቅ ትግል በድል ያጠናቀቁት የውጭና የሌሎች ድጋፍ አግኝተው ሳይሆን የጠራ ህዝባዊ መስመር በመያዛቸው ነው» ሲሉ የህወሓት ሊቀመንበር አስታወቁ።

ህወሓት የትጥቅ ትግል የጀመረበትን የደደቢት በረሃና ሌሎች ታሪካዊ ስፍራዎች በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገቡ ጥረት እንደ ሚያደርጉ ታሪካዊ ስፍራዎችን የጎበኙ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ገልጸዋል።

የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች በመጪው የካቲት የሚከበረውን የህወሓት 40ኛው ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ በክልሉ የትጥቅ ትግል የተካሄደባቸውን ስፍራዎችና የማዘዣ ጣቢያዎችን ለአንድ ሳምንት ያህል ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የህወሓት ሊቀመንበር አቶ ዓባይ ወልዱ የጉብኝቱን መርሐ ግብር መጠናቀቅ አስመልክቶ ትናንት ማምሻውን በመቀሌ በተዘጋጀው የማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ እንደገለጹት፤ ህወሓትና የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ ጭቁን ህዝቦች ጋር በመሆን የትጥቅ ትግሉን በአሸናፊነት ሊወጡ የቻሉት የጠራ ህዝባዊ መስመር በመያዛቸው ነው።

የክልሉ ህዝብ ቀደም ሲሉ በነበሩትና በደርግ ሥርዓቶች ሲደርስበት የቆየውን ብሔራዊ ጭቆና ለማስወገድ ህወሓት የትጥቅ ትግሉ መጀመሩን ገልጸው፤ በወቅቱ የተሳሳተ ዓላማ ያነገቡ ኃይሎች ትግሉን ገና ከጅምሩ በእንጭ ጩ ለማኮላሸት ተንቀሳቅሰው እንደነበር አስታ ውሰዋል።

«ህወሓት የያዘውን ህዝባዊ ዓለማና ትክክለኛ መስመር የሚደግፉ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎችን ከጎኑ እያሰለፈ ህዝቡን የትግሉ ባለቤት ማድረጉ ትግሉን በአሸናፊነት እንዲወጣ አስችሎታል» ብለዋል።

ሊቀመንበሩ እንዳሉት ህወሓት በወቅቱ ሲያጋጥሙት የነበሩትን በርካታ ተግዳሮቶችና እንቅፋቶችን ተቋቋሞ ትግሉን በአሸናፊነት ሊወጣ የቻለው የጠራ ህዝባዊ መስመር በመያዙና ባለው የዓላማ ፅናት ነው።

ህወሓትና የትግራይ ህዝብ የትጥቅ ትግሉን ያካሄዱት ይደርስባቸው የነበረውን ብሄራዊ ጭቆና በመገርሰስ ከኢትዮጵያ ህዝቦች ጎን ተሰልፈው በአገራቸው ጉዳዮች ላይ እኩል ተጠቃሚ ለመሆን እንጂ «የተለየ ፋይዳ ለማግኘት አይደለም» ብለዋል።

የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን በበለጠ በማጠናከር የኢትዮጵያን የህዳሴ ጉዞ እውን ለማድረግ እየተደረገ ላለው ሁሉን አቀፍ ጥረት ስኬት የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች የላቀ ድርሻ ያላቸው በመሆኑ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል።

ህወሓት የትጥቅ ትግል የጀመረበትን የደደ ቢት በረሃንና ሌሎች ታሪካዊ ስፍራዎችን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ የሚጠበ ቅባቸውን ሁሉ እንደሚወጡ ታሪካዊ ስፍራዎ ቹን የጎበኙ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች አረጋ ግጠዋል።

ከባለሙያዎቹ መካከል ደራሲ ጌታቸው በለጠና አርቲስት ሙሉ ገበየሁ እንደገለጹት፤ የትግራይ ወጣቶች በአፍላ ዕድሜአቸው ህዝባዊ ዓላማ አንግበው ወደ ደደቢት በረሃ በመውጣት ትግል የጀመሩበትና ያሳለፏቸው ውጣ ውረዶች ለትውልድ እንዲተላለፉ የበኩላቸውን ጥረት ያደርጋሉ።

በተለይ የትጥቅ ትግሉ የተጀመረበት የደደቢት በረሃና የማዘዣ ጣቢያዎች አሁን በአገሪቱ እየተገነባ ላለው የሰላም፣ የልማትና የዴሞክራሲ ሥርዓትና ኢትዮጵያ ለጀመረችው የህዳሴ ጉዞ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጋቸውንም ገልጸዋል።

በመሆኑም እነዚህና ሌሎች ታሪካዊ ሥፍራዎች በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገቡ የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ባለሙያዎቹ አረጋግጠዋል።

በዚሁ የጉብኝቱ የማጠቃለያ ሥነ-ሥርዓት ላይ የትጥቅ ትግሉ መስራቾችና ከፍተኛ አመራር አባላት እንዲሁም የከተማው ህዝብ ተወካዮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን፤ ለኪነ-ጥበብ ባለሙያዎቹም ሽልማት ተበርክ ቶላቸዋል።

*********

ምንጭ፡- አዲስ ዘመን፣ ታህሳስ 18-2007

Curated Content

Content gathered and compiled from online and offline media by Hornaffairs staff based on relevance and interest to the Horn of Africa.

Recent Posts

ኪዳነ ኣመነ – እንደህዝብ አንድ ሆነናል ያስቸገረን የህወሓት አስተሳሰብ ነው

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 2 - ለውጥ…

5 years ago

ኪዳነ አመነ – ለትግራይ ታላቅነት ሼምለስ ሆነን እንሰራለን

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 1 - ለትግራይ…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ትዴት ኢትዮጲያዊ ማንነት ብቻ እንዳለ ነው የሚያምነው (video)

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ (ክፍል 2)- ስለትዴት…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ኢሳት የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ ነው የሰራው (Video)u

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ (ክፍል 1) -…

5 years ago

የበረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ መታሰር -ሕጋዊ ወይስ ፖለቲካዊ እርምጃ?

(የማነ ካሣ) እንደሚታወቀው አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከጥረት ኮርፖሬሽን ጋር በተያያዘ…

5 years ago

ኣስተያየት በ’ኣብራክ’ ልብወለድ ድርሰት ላይ

(መርስዔ ኪዳን - ሚኔሶታ) ኣብራክ የተባለውን የሙሉጌታ ኣረጋዊ መጽሓፍ ኣነበብኩት። ኣገራችን ከሊቅ አስከደቂቅ በዘውጌ ብሄርተኝነት…

5 years ago