የዩኒቨርስቲዎች ሃይማኖታዊ ስነስርአትና አለባበስ ደንብን በመቃወም በሽብር የተሳተፉ ግለሰቦች ጥፋተኛ ተባሉ

(በጥላሁን ካሳ)

የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ሃይማኖታዊ ስነስርአትና አለባበስን በሚመለከት ያወጡትን የስነምግባር ደንብ በመቃወም የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመፍጠር በሽብር ድርጊት ውስጥ የተሳተፉ 13 ግለሰቦች የጥፋተኝነት ፍርድ ተላለፈባቸው።

ተከሳሾቹ እስማኤል ኑር ሁሴን፣ ፈትያ መሃመድ፣ ኑርዬ ቃሲም፣ ያሲን ፈያሞ፣ መሃመድ አሚን፣ መሃመድ ሰይድ፣ የሱፍ ከድር፣ ጣሂር መሃመድ፣ መሃመድ ሰይድ፣ ሰይድ ኢብራሂም፣ አብደላ መሃመድ፣ አብዲ መሃመድ እና ኢብራሂም የሱፍ ኢብራሂም ናቸው።

የወንጀል አድማ ስምምነት በማድረግ የመንግስት ዩንቨርስቲዎች ሃይማኖታዊ ስነስርአትና አለባበስን በሚመለከት ያወጡትን የስነምግባር ደንብ በመቃወም የተለያዩ ምስጢራዊ  አደረጃጀቶችን በመጠቀም ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ የሽብር ድርጊት ፈጽመዋል በሚል ነው የፌደራል አቃቤህግ የከሰሳቸው።

ተከሳሾቹ በ2005 ዓ.ም በባህርዳር ዩንቨርሲቲ ሃይማኖታዊ አለባበስን በሚመለከት የወጣውን ደንብ ተከትሎ በጥቂት ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች የተጀመረው አመጽና አድማ በተናጠል ከሚሆን ሃገር አቀፍ መሆን አለበት በማለት በየዩኒቨርስቲዎች በስልክ፣ በማህበራዊ ድረ ገጾችና በአካል በመንቀሳቀስ ቀስቅሰዋል።

በሽብር ተከሰው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙ ራሳቸውን የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ እያሉ የሚጠሩ 17 ግለሰቦች ከህግ ውጭ ከእስር እንዲፈቱም ተንቀሳቅሰዋል።

ከእንግዲህ በኋላ ሰላማዊ ትግል አብቅቷል፤ መላው ሙስሊም ለመረጃ  ቅርብ መሆን አለበት፤ ለሚፈጠረው ነገር ሁሉ ራሱን ማዘጋጀት አለበት በማለት ግልጽ የአመጽ ጥሪ አድርገዋል ነው የሚለው ክሱ።

ክሱን ሲመረምር የቆየው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድቤት የአቃቤ ህግን ምስክር እና የተከሳሾችን የመከላከያ ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ሁሉም ተከሳሾች ክሱን ማስተባበል ባለመቻላቸው ጥፋተኞች ናቸሁ ሲል ፈርዶባቸዋል።

ችሎቱ የቅጣት ውሳኔ ለማስተላለፍ ለጥቅምት 4 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።
*******
ፋና፡- መስከረም 26፣ 2007

Curated Content

Content gathered and compiled from online and offline media by Hornaffairs staff based on relevance and interest to the Horn of Africa.

Recent Posts

ኪዳነ ኣመነ – እንደህዝብ አንድ ሆነናል ያስቸገረን የህወሓት አስተሳሰብ ነው

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 2 - ለውጥ…

5 years ago

ኪዳነ አመነ – ለትግራይ ታላቅነት ሼምለስ ሆነን እንሰራለን

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 1 - ለትግራይ…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ትዴት ኢትዮጲያዊ ማንነት ብቻ እንዳለ ነው የሚያምነው (video)

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ (ክፍል 2)- ስለትዴት…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ኢሳት የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ ነው የሰራው (Video)u

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ (ክፍል 1) -…

5 years ago

የበረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ መታሰር -ሕጋዊ ወይስ ፖለቲካዊ እርምጃ?

(የማነ ካሣ) እንደሚታወቀው አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከጥረት ኮርፖሬሽን ጋር በተያያዘ…

5 years ago

ኣስተያየት በ’ኣብራክ’ ልብወለድ ድርሰት ላይ

(መርስዔ ኪዳን - ሚኔሶታ) ኣብራክ የተባለውን የሙሉጌታ ኣረጋዊ መጽሓፍ ኣነበብኩት። ኣገራችን ከሊቅ አስከደቂቅ በዘውጌ ብሄርተኝነት…

5 years ago