ነገረ «ኔት ወርክ»

(ሊዲያ ተስፋዬ)

ለዒድ በዓል እንኳን አደረሰሽ ያላልኳት ጓደኛዬ መቀየሟን ከነገረችኝ ቀናት አለፉ። በስራ ጉዳይ ከከተማ ራቅ ካለች ሰንብታለችና እንደልብ መገናኘት እንደማንችል ስናውቅ «ዕድሜ ለቴክኖሎጂ ስልክ አለ» ብለን ለመደዋወል ቃል ተገባብተን ነበር። ምን ያደርጋል ኔት ወርክ የሄደበት ሳይታወቅ ጥፍት ብሎ ጭራሽ አቀያየመን። እኔ ልነግራት ነበር «ይሄ የሀገር ጉዳይ ነው። የኔ ችግር አይደለም። ረስቼሽም አይደለም» ልላት። ግን በምን?

የኔትወርክ ነገር በጣም አስቸጋሪ ሆኗል። እንደ መብራቱ እሱም «እዚህ ነኝ…መጣሁ… ወጣ ልል ነው» ሳይል እልም ይላል። አሁን አሁንማ የሞባይሌ አገልግሎት ሬዲዮ ለማዳመጥና ሰዓት ለማየት ብቻ የሆነ ይመስላል። «ሞባይል አለሽ?» ካሉኝ «በውስጠ ታዋቂነት» እያልኩ ብመልስም ሁሉ ደስ ይለኛል። «ለምን?» ቢሉ የሞባይሌ መኖር ካለመኖር ባይጠቃለልም ኔትወርክ እንዲህ ደጅ በሚያስጠናበት ሁኔታ ከመኖር አይቆጠርምና ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደውም መጥሪያ ሞልቼ ካላስጮኳት በቀር የሞባይሌ ድምፅም ጠፍቶብኛል።

«በስልክ አነጋግሪኝ በቀጭኑ ሽቦ!» እየተባለ ተዘፍኖ፤ ከጎረቤት ስልክ ያለው «በዚህ ስልክ ደውሉልኝ ብሎ» በኩራት የተናገረበትም ጊዜ አልፎ አሁን አርሶ አደሩ የገበያውን ሁኔታ እንዲያውቅ፣ ከተሜው ክልል ያለ ቤተሰቡን እንዲጠይቅ፣ ባሕር ማዶ ያለውም የሀገሩን ዜና እንዲሰማ፣ እንደ እኔ ከጓደኛው የተራራቀ ደግሞ ተደዋውሎ እንዲጨዋ ወት የበቃበት ጊዜ ላይ ደርሰናል። ያም ብቻ ሳይሆን በአንድ ጊዜ የተለያየ ሰው ጋር ደውሎ በጋራ ማውጋትና መረጃ መለዋወጥ የሚቻልበትም መንገድ ተዋውቋል። ኔትወርክ የለም እንጂ።

«አሁን እንዲያው አያድርገውና» አልኩኝ በሃሳቤ የሆነ እሳት ተነስቶ ቤቴ ቢቃጠልና ወደ እሳት አደጋ መደወል ብፈልግ ሞባይሌ አፍ አውጥታ «ምን አደከመሽ ?ኔትወርክ እንደሆነ የለ» ትለኝ ይሆናል እንጂ አልድንም ማለት ነው እኮ ! ብቻ ይሰውረን… በተለይ አደጋዎች በሚከሰቱ ጊዜ በአጋጣሚ ኔትወርክ ካልተገኘ በቀር ዕርዳታ ለመጠየቅ ስልክ መጠቀም የሚቻል አይመስለኝም። ሃሳቤ ለራሴም አሳቀቀኝና እንዲርቀኝ አማተብ ኩበት!

እደውላለሁ ያለ ሰው ባይደውልላችሁ፣ ሞባይሏም ደውይ ስትሏት አሻፈረኝ ብትል ችግሩ እደውላለሁ ካለውም ሆነ አልደውልም ካለችውም ሞባይል ብቻ ያልሆን ይችላል። ኔትወርኩ «ኖ-ወርክ» ብሎ ይሆናልና ችግሩ ተፈትቶ እስኪስተ ካከል ድረስ እንዳትቀየሙ።

ይልቅስ የ«ኖ ወርክ» ጨዋታ ላቋድሳችሁ። ከአንድ ወዳጄ ጋር መንገድ ላይ ተገናኝተን «እንደዋወል፣ አንጠፋፋ» ስለው «እንዲህ በአጋጣሚ ያገናኘን እንጂ፤ እንደዋወል ብሎ አንጠፋፋ የለም። ኔትወርኩ ‹ኖ ወርክ› ብሏል» አለኝ። እኔም አሁን ኢትዮ ቴሌኮም ችግሩን ፈትቶ «ኖ-ወርክ» ጠፍቶ ኔትወርክ እስኪመጣ ምን ያህል እንደሚቆይ ስለማላውቅ ጓደኛዬን ሄጄ ልክሳት ወሰንኩና ለጉዞ ራሴን ለማዘጋጀት ተነሳሁ!

ባለፈው እንዲሁ ሞባይሌ በባንክ በኩል ገንዘብ እንድልክ ታዝዤ ብሄድ ሲስተም የለም አሉ። እኔም ላዘዙኝ ሰዎች ገንዘቡ እንደማይደርስ ለመናገር ልደውል ብል ኔትወርከ የለም ለካ። ተናደድኩ…በሰዓቱ አንድ አጠገቤ የነበረ ሰው ሳማርር ይሰማኝ ነበር «በታዳጊ ሀገር ውስጥ ሆነሽ ሁሉም የተሟላ እንዲሆን መጠበቅ የለብሽም»አለኝ «እሱ መች ጠፋኝና። አውቃለሁ። ግን ደግሞ የቴክኖሎጂ ምርቶች እየተዋወቁ፣ ሞባይሎችና ሲም ካርዶች በቅናሽ ዋጋ ገበያ ላይ ቀርበውና ስንት ማስታወቂያ እየያየን በአገልግሎ ታቸው ለመጠቀም ህዝቡ ከገዛ በኋላ ‹ኔትወርክ የለም› መባል ምን ማለት ነው? አያናድድም?» አልኳቸው።

«ቢሆንም መቻል ነው። ምን ማድረግ ይቻላል?» አሉኝ። «ግን በእርግጥ ማድረግ የሚቻል ነገር የለም ?» ብዬ አሰብኩ። አሁን በአብዛኛው ቦታ የቴክኖሎጂ ውጤቶች አገልግ ሎት ላይ እየዋሉ ነው። ከዛም አልፎ በቀጥታም በተዘዋዋሪም በሥራና በመሳሰሉት ዘርፎች በህይወታችን እየገቡ ነው። አብዛኞቹም የሥራ ዘርፎች እነዚህን የቴክኖሎጂ ምርቶችና ውጤቶች እየተጠቀሙ ነው። ለምሳሌ የሠራተኞች ደመወዝና የተማሪዎች የወጪ መጋራት ክፍያን መጥቀስ ይቻላል። እነ ኔትወርክ ግን አስቸገሩ። እና እንዴት ነው ወር ሙሉ ሰርቶ ደመወዙን ሊቀበል ሲሄድ ሲስተም የለም የሚባል ሠራተኛ «ቻለው» የሚባለው? አስቸጋሪ ነውና ይታሰብበት።

*********
ምንጭ፡- አዲስ ዘመን – ነሐሴ 2006

Curated Content

Content gathered and compiled from online and offline media by Hornaffairs staff based on relevance and interest to the Horn of Africa.

Recent Posts

ኪዳነ ኣመነ – እንደህዝብ አንድ ሆነናል ያስቸገረን የህወሓት አስተሳሰብ ነው

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 2 - ለውጥ…

5 years ago

ኪዳነ አመነ – ለትግራይ ታላቅነት ሼምለስ ሆነን እንሰራለን

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 1 - ለትግራይ…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ትዴት ኢትዮጲያዊ ማንነት ብቻ እንዳለ ነው የሚያምነው (video)

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ (ክፍል 2)- ስለትዴት…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ኢሳት የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ ነው የሰራው (Video)u

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ (ክፍል 1) -…

5 years ago

የበረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ መታሰር -ሕጋዊ ወይስ ፖለቲካዊ እርምጃ?

(የማነ ካሣ) እንደሚታወቀው አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከጥረት ኮርፖሬሽን ጋር በተያያዘ…

5 years ago

ኣስተያየት በ’ኣብራክ’ ልብወለድ ድርሰት ላይ

(መርስዔ ኪዳን - ሚኔሶታ) ኣብራክ የተባለውን የሙሉጌታ ኣረጋዊ መጽሓፍ ኣነበብኩት። ኣገራችን ከሊቅ አስከደቂቅ በዘውጌ ብሄርተኝነት…

5 years ago