የኢዴፓ መግለጫ – “በሽብርተኝነት ስም የሚወሰደው እርምጃ ግልጽነት ይኑረው!”

በሽብርተኝነት ስም የሚወሰደው እርምጃ ግልጽነት ይኑረው!
ከኢዴፓ የተሰጠ መግለጫ

በአገር ውስጥ በህጋዊ መንገድ ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም መንግስት በሽብር ጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ማዋሉ በሚዲያዎች ተገልጿል፡፡

እነዚህ አመራሮች ከ48 ሰዓታት በላይ ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውና የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በጉዳዩ ላይ ዝርዝር መረጃ አለማቅረባቸው አመራሮቹ የታሰሩት በሚያራምዱት የፖለቲካ አቋም እንዳይሆን ፓርቲያችን ስጋት አድሮበታል፡፡

የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በጉዳዩ ላይ ጥልቅ ውይይት ካደረገ በኋላ የሚከተለውን አቋም ወስዷል፡፡

1/ መንግስት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች የተያዙበትን ምክንያት ለህብረተሰቡ ዝርዝር እና ግልጽ መረጃ እንዲሰጥ፤

2/ የታሰሩት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 21 መሰረት ለዜጎች የተሰጠው መብት እንዲከበርላቸው፤

3/ በአስቸኳይ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ፤ የፍርድ ሂደታቸውም ተአማኒ፤ ግልጽ እና ፈጣን በሆነ መንገድ እንዲታይ እያሳሰብን

ይህ ሳይሆን ቢቀር ግን የአገሪቱን ህግ አክብረን በሰላማዊ ትግል ከምንንቀሳቀስ ፓርቲዎች ይልቅ ከዚህ በተቃራኒ የሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ ሀይሎችን የሚያጠናክር፤ ክርክራቸውንም ምክንያታዊ የሚያደርግ እና የዴሞክራሲያዊ ግንባታውን ወደኋላ የሚመልስ በመሆኑ ጉዳዩ እጅግ እንደሚያሳስበን እንገልጻለን፡፡

ስለዚህም መንግስት የጉዳዩን አሳሳቢነት ተገንዝቦ አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጥ ኢዴፓ ያሳስባል፡፡

የኢዴፓ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ
ሐምሌ 7 ቀን 2006 ዓ.ም
ሰላምና ህብረ-ብሔራዊነት አላማችን ነው!
**********
Source: የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ)

Curated Content

Content gathered and compiled from online and offline media by Hornaffairs staff based on relevance and interest to the Horn of Africa.

Recent Posts

ኪዳነ ኣመነ – እንደህዝብ አንድ ሆነናል ያስቸገረን የህወሓት አስተሳሰብ ነው

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 2 - ለውጥ…

5 years ago

ኪዳነ አመነ – ለትግራይ ታላቅነት ሼምለስ ሆነን እንሰራለን

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 1 - ለትግራይ…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ትዴት ኢትዮጲያዊ ማንነት ብቻ እንዳለ ነው የሚያምነው (video)

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ (ክፍል 2)- ስለትዴት…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ኢሳት የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ ነው የሰራው (Video)u

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ (ክፍል 1) -…

5 years ago

የበረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ መታሰር -ሕጋዊ ወይስ ፖለቲካዊ እርምጃ?

(የማነ ካሣ) እንደሚታወቀው አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከጥረት ኮርፖሬሽን ጋር በተያያዘ…

5 years ago

ኣስተያየት በ’ኣብራክ’ ልብወለድ ድርሰት ላይ

(መርስዔ ኪዳን - ሚኔሶታ) ኣብራክ የተባለውን የሙሉጌታ ኣረጋዊ መጽሓፍ ኣነበብኩት። ኣገራችን ከሊቅ አስከደቂቅ በዘውጌ ብሄርተኝነት…

5 years ago