የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ም/ፕሬዝዳንትና ዋና ፀሐፊ ተነሱ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ በጠራው አስቸኳይ ስብሰባ የፌዴሬሽኑን ዋና ጸሀፊ አቶ አሸናፊ እጅጉ ከስልጣናቸው እንዲነሱ ወስኗል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድን በብራዚሉ የ2014ቱ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ላይ ከቦትስዋና ባደረገው ጨዋታ ላይ ሁለት ቢጫ እያለው በስህተት የተሰለፈውን ተጫዋች ምክንያት በማድረግ ሶስት ነጥብና ሶስት ጎል ተቀንሶበታል፡፡

ይህንንም ምክንያት በማድርግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በቅርቡ በሰጠው መግለጫ ችግሩን ለማጣራት እንደሚሰራ መግለጹን ተከትሎ በጠራው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ጸሀፊ አቶ አሸናፊ እጅጉን ከስልጣናቸው አንስቷል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ብርሃኑ ከበደ ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ ያቀረቡት ጥያቄ ስራ አስፈጻሚው አጽድቆታል፡፡

ጠቅላላ ጉባዔው እንደቀጠለ ነው፡፡

***********

Source: ERTA – June 24, 2013, titled “የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ጸሀፊ ከስልጣናቸው ተነሱ”.

Recommended: የፌዴሬሽኑ ቅሌት

9.14540.489673

View Comments (1)

Leave a Comment

This website uses cookies.