(ሰለሞን ፀጋየ)
ከአዲስ አበባ/ሰበታ-ጁቡቲ ወደብ ድረስ ለሚዘረጋው የ756 ኪሎ ሜትር የባቡር መስመር ግንባታ የሚውል 2ነጥብ 97ቢሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት ግንቦት 14/2005 ዓ.ም ተፈጸመ፡፡
የብድር ስምምነቱን የፈረሙት ዶ/ር ኢንጂነር ጌታቸው በትሩ የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፣ ሚስተር ኤልያስ ሙሳ ዳዋሌህ የጁቡቲ መንግስት የኢኮኖሚና ፋይናንስ ሚኒስትር እንዲሁም የቻይና ኤግዚም ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንት ሚስተር ዡ ዠንጂያንግ ናቸው፡፡
በስምምነቱ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ሚስተር ዡ ጂንግ ያንግ የኢትዮጵያና ቻይና ግንኙነት እየተጠናከረ መምጣቱን ገልጸው ይህ የብድር ስምምነትም የግንኙነት መጠናከር ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
በቀጣይ ኢትዮጵያ ለምታደርገው ማንኛውም የልማት ፕሮጀክት የቻይና መንግስት ድጋፍ እንደማይለያት አረጋግጠዋል፡፡
የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ኢንጂነር ጌታቸው በትሩ ይህ ስምምነት ታሪካዊ ነው የኢትዮጵያ ጅቡቲና ቻይና ጠንካራ ግንኙነት ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
የጁቡቲ የኢኮኖሚና ፋይናንስ ሚኒስት
የብድሩ መጠን 2.9 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ከዚህ ውስጥ 2.4 ቢሊዮን ዶላሩ በኢትዮጵያ በኩልለሚዘረጋው የባቡር መስመር ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ ይውላል፡፡ ይህም የፕሮጀክቱን 70 በመቶ ይሸፍናል፡፡ ቀሪው 30 በመቶ ደግሞ በኢትዮጵያ መንግስት ወጪ የሚሸፈን ይሆናል፡፡ 570 ሚለዮን ዶላር ብድሩ ደግሞ በጅቡቲ በኩል ለሚዘረጋው የባቡር መስመር ማስፈፀሚያ የሚውል ነው፡፡
ከቻይናው ኤግዚም ባንክ የተገኘው ብድር ከአዲስ አበባ/ሰበታ እስከ መኢሶን 317 ኪሎ ሜትር፣ ከመኢሶን ደዋሌ 339 ኪሎ ሜትር ከኢትዮጵያ ድንበር እስከ ዶራሌ/ጅቡቲ/ 100 ኪሎ ሜትር ላሉት የባቡር መስመር ፕሮጀክቶች ግንባታ እንዲሁም ለባቡር ተሸከርካሪዎች ግዥ ይውላል፡፡
ከአዲስ አበባ/ሰበታ – መኢሶን 317 ኪሎሜትር በቻይናው CREC እንዲሁም ቀሪው የፕሮጀክቱ ክፍል ደግሞ በቻይናው ኩባንያ CCECC ይገነባል፡፡
በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርም ደሳለኝና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ተገኝተዋል፡፡
የአዲስ አበባ/ሰበታ-መኢሶን-ደወሌ የባቡር መስመር ግንባታ 19 በመቶ ተጠናቋል፡፡
**********
Source: ERTA – May 23, 2013
Leave a Comment