Tag Archives: ኮ/ል አስጨናቂ ገ/ጻዲቅ ሺፈራዉ

ኮ/ል አስጨናቂ ገ/ጻዲቅ (Colonel Aschenaki Gebretsadik) በአየር ኃይል ዉስጥ ከ1970ዓ/ም ጀምሮ ሲያገለግሉ ቀይተዉ ከ2002 ዓ/ም ጀምሮ በጡረታ ላይ የሚገኙ ናቸዉ፡፡ በአየር ኃይል ዉስጥ በዘመቻና መረጃ መምሪያ ኃላፊነት፤ በአየር ምድብ አዛዥነትና በአይር መከላከያ ኃላፊነትና በሌሎች የሃላፊነት ቦታዎች ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ በኤርትራ ጦርነት ወቅት በሰሜን አየር ምድብ በምክትልነትነና የአየር መከላከያዉን ስራ በተለይ በሃላፊነት በማስተባበር ሲሰሩ ነበር፡፡ ኮ/ል አስጨናቂ ከቀድሞዋ ሶቭት ህብረት በወታደራዊ ሳይንስ የማስተርስ ድግሪ አላቸዉ፡፡

ቁርጠኛ የሆነ አመራርና ነጻ ሚዲያ በሌለበት ሙስናን መታገል ከቶ አይቻልም

(አስጨናቂ ገ/ጻዲቅ ሺፈራዉ (ኮ/ል)) በሀገራችን በየጊዘዉ ለሚከሰቱ ችግሮች ሁሉ በቀላሉ ተጋላጭ ለመሆን የተገደድነዉ ተአማኒነት ያለዉ አማራጭ ነጻ መረጃ ምንጭ እጦትና ቁርጠኛ የሆነ አመራር አለመኖር ነዉ፡፡ ዋስትናዉ የተጠበቀ የመረጃ ተደራሽነት መኖር ለአንድ ህዝብ እጅግ ጠቃሚ ነዉ፡፡ ዜጎች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ በነጻነት የመወያየት፤ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ፤ ነጻ በሆኑ ሚዲያዎችን ተጠቅመዉ ያለመሸማቀቅ መንግስትን የመተቸትና አስፈላጊ ሆኖ ባገኙ … Continue reading ቁርጠኛ የሆነ አመራርና ነጻ ሚዲያ በሌለበት ሙስናን መታገል ከቶ አይቻልም

የህዝብ አመኔታን እያተረፈለት የመጣዉ የኢህአዴግ ጥልቅ ተሃድሶ

(አስጨናቂ ገ/ጻዲቅ ሺፈራዉ (ኮ/ል)) ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በሀገራችን እጅግ አስፈሪ በሆነ ሁኔታ ከዳር አስከ ዳር አዳርሶ ከነበረዉ ቀዉስ በመንግስት ትእግስት የተሞላበት አመራር ሰጭነት ወደ ቀልባችን ከተመለስን በኋላ ገዥዉ ፓርቲና መንግስት “ጥልቅ መታደስ ” በሚል የለዉጥና የመታደስ ሂዴት ዉስጥ እንገኛለን፡፡ በከፍተኛ መነሳሳትና የቁጭት ስሜት የተጀመረዉ ይህ የለዉጥና የመታደስ እርምጃ ለዉጤት እንደሚበቃ ቅንጣት ጥርጣሬ የለኝም፡፡ ለዉጡ በመንግስትና … Continue reading የህዝብ አመኔታን እያተረፈለት የመጣዉ የኢህአዴግ ጥልቅ ተሃድሶ

በመከላከያ ሰራዊታችን የፖርቲ ፖለቲካ ገለልተኝነትና ተያያዥ ጉዳዮች [ክፍል 2]

(ኮ/ል አስጨናቂ ገ/ጻዲቅ ሽፈራው) (የዚህን ጽሑፍ የመጀመሪያ ክፍል ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ) 9/ በሰራዊቱ ዉስጥ ገለልተኝነትን የሚሸረሽርና ለኢህአዴግ የወገነ አሰራር አልነበረም፡፡ የመከላከያ ሰራዊት ግንባታ ሰነዱ የሰራዊቱን ገለልተኝነት የሚሸረሽር ስለመሆኑ በሰራዊት ግንባታ ሰነዱ ላይ ዉይይት በተደረገባቸዉ ጊዜያትም ሆነ  ከዚያ  በኋላ በሰራዊቱ ዉስጥ አንድም ጊዜ ቅሬታ ሲቀርብ  አልሰማሁም፡፡ በሰራዊቱ ዉስጥ በነበርኩበት ወቅት በመመሪያዉ ላይም ሆነ በአፈጻጸም ረገድ … Continue reading በመከላከያ ሰራዊታችን የፖርቲ ፖለቲካ ገለልተኝነትና ተያያዥ ጉዳዮች [ክፍል 2]

በመከላከያ ሰራዊታችን የፖርቲ ፖለቲካ ገለልተኝነትና ተያያዥ ጉዳዮች (ኮ/ል አስጨናቂ ገ/ጻዲቅ)

(ኮ/ል አስጨናቂ ገ/ጻዲቅ ሺፈራዉ) [ከአዘጋጁ፡- ኮ/ል አስጨናቂ ይህንን ጽሑፍ የላኩልን ከሳምንታት በፊት ቢሆንም የኢንተርኔት ተደራሽነት ለአብዛኛው የሀገር ውስጥ አንባቢ ውስን ስለነበረ እና በተያያዥ ምክንያቶች አዘግይተነዋል፡፡ ከጽሑፉ ርዝመት አንጻር በሁለት በመክፈል የመጀመሪያውን ክፍል እዚህ አትመነዋል፡፡] —— Highlights: * ከመከላከያ ሰራዊት ምስረታ አንድ ዓመት ቀደም ብሎ (1986 ላይ) ጂግጅጋ አካባቢ ለስራ ሄጄ ያገኙሁት አንድ ነባር ታጋይ እንደዚሁ … Continue reading በመከላከያ ሰራዊታችን የፖርቲ ፖለቲካ ገለልተኝነትና ተያያዥ ጉዳዮች (ኮ/ል አስጨናቂ ገ/ጻዲቅ)

የኮንሶ ህዝብ ጥያቄ ተገቢዉን ምላሽ ይሻል !

(ኮሎኔል አስጨናቂ ገ/ጻዲቅ ሺፈራዉ) በቅድሚያ በኮንሶ ህዝብ ላይ እየደረሰ ሲላለዉ በደል አንዳችም ትርፍ  ነገር ሳይጨምር ሳይቀንስና ሳይደባብቅ ሃቁን ለህዝብና ለሚመለከታቸዉ የመንግስት ባለስልጣና አካላት ሁሉ እንዲደርስ ባደረገዉ በአቶ ናሁሰናይ በላይ የተሰማኝን ኩራትና አድናቆት ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡ ናሁሰናይ አስታዋሽ ያጣዉና ትኩረት የተነፈገዉ  የኮንሶ ህዝብ  ብቻ  ሳይሆን  ጭቆናንና በደልን የሚጸየፉ የመላዉ የሀገራችን ህዝቦች ሁሉ እንደሚያሰግኑህ ቅንጣት ጥርጥር የለኝም፡፡ ሆርን … Continue reading የኮንሶ ህዝብ ጥያቄ ተገቢዉን ምላሽ ይሻል !

ለሀገሪቱም ለኢህአዴግም የሚበጀዉ ሀገር ወዳድ ምሁራንን ማዳመጡ ነዉ!

(ኮሎኔል አስጨናቂ ገ/ጻዲቅ ሺፈራዉ) መግቢያ በሃገራችን የተከሰተዉን አደገኛ ሁኔታ ስጋት የገባቸዉ ቅን የሆኑ ኢትዮጵያዉያን አገሪቱን ከአደጋ መታደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የበኩላቸዉን ምክረ ሃሳብ እያቀረቡ ባለበት ሰዓት አንዳችም ኃላፊነት የማይሰማቸዉ አንዳንድ ወገኖች ደግሞ አሁን ያለዉ ቀዉስ ተባብሶ  የበለጠ ምስቅልቅል ሁኔታ እንዲፈጠር ሆን ብለዉ መርዘኛ የሆነ ቀስቀሳ ከማድረግ አልተቆጠቡም:: መንግስት በሀገሪቱ የተከሰተዉ ሁኔታ አሳስቦት ራሱን በግልጽ ፈትሾና … Continue reading ለሀገሪቱም ለኢህአዴግም የሚበጀዉ ሀገር ወዳድ ምሁራንን ማዳመጡ ነዉ!

ዳግመኛ ለኤርትራ ጥቃት እንዳንጋለጥ ለማይቀረዉ ጦርነት ካሁኑ መዘጋጀት (ኮ/ል አስጨናቂ ገ/ጻዲቅ)

(ኮሎኔል አስጨናቂ ገ/ጻዲቅ ሺፈራዉ) መግቢያ ኤርትራ በግፍ ወረራ ፈጽማብን የተቀሰቀሰዉን ጦርነት በኛ አሸናፊነት ከተጠናቀቀ እነሆ ሁለት አስርተ ዓመታት ሊሞላዉ ትንሽ ቢቀረዉ ነዉ፡፡እስካሁንም ችግሩ መቋጫ ስላልተበጀለት ሰላምም ጦርነትም በለለበት ሁኔታ የሁለቱ አገሮች ወታደሮች በድንበር አካባቢ ተፋጠዉ ይገኛሉ፡፡ስለ ኢትዮ- ኤርትራ ጉዳይ አልፎ አልፎ በአጋጣሚ ካልሆነ በስተቀር ብዙም የማይነገር ሆኖ ቆይቶ ጭራሽ የተረሳ በመሰለበት ወቅት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደገና የብዙ … Continue reading ዳግመኛ ለኤርትራ ጥቃት እንዳንጋለጥ ለማይቀረዉ ጦርነት ካሁኑ መዘጋጀት (ኮ/ል አስጨናቂ ገ/ጻዲቅ)