Category Archives: የኦሮሚያ ተቃውሞ – Oromo Protests

መንግስትን ከማረም ለመንግስት ጥብቅና የሚቆም የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርት

የኢትዮጲያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት “ከሰኔ 2008 ዓ.ም እስከ መስከረም 2009 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ በነበሩት ወራት በኦሮሚያ፣ አማራና በደቡብ ብሔር ብሄረሰቦች እና ሕዝቦች ክልሎች ተፈጥረዋል ባላቸው ሁከትና ብጥብጥ 669 ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል፣ 1018 ሰዎች ላይ የተለያዩ የአካል ጉዳቶች ደርሶባቸዋል፣ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል” ብሏል። እስኪ ከላይ የቀረበውን ሪፖርት … Continue reading መንግስትን ከማረም ለመንግስት ጥብቅና የሚቆም የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርት

መንግስት የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን ከማራዘም ሌላ አማራጭ የለውም

የኢህአዳግ መንግስት በየመድረኩ የሚናገረውን ሁሉ አምነው የሚቀበሉ፣ ችግሮቹን “በጥልቅ ተሃድሶ” ይፈታል የሚሉ አባላትና ደጋፊዎች አሉት። ነገር ግን፣ የኢትዮጲያን ፖለቲካ በቅርበት ለሚከታተል ሰው ኢህአዴግ የሚለውን ከማመን ይልቅ ቀጣይ ተግባሩን መገመት በጣም ይቀላል። ለቀጠይ አራት ወራት እንዲራዘም የተወሰነውን የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ እስኪ እንደ ማሳያ ወስደን በዝርዝር እንመልከት። የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ የታወጀው መስከረም 28/2009 ዓ.ም ነው። ነገር ግን፣ … Continue reading መንግስት የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን ከማራዘም ሌላ አማራጭ የለውም

ስለኦሮሞና ኦሮሞነት ማንሳት እንደወንጀል መታየት የለበትም – ፕሬዝዳንት ለማ መገርሳ

(አዲሱ አረጋ ቂጤሳ) 27ኛዉ የኦህዴድ ምስረታ በዓል በአዳማ ከተማ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት በፓናል ዉይይት ተከብሯል፡፡ በፓናል ዉይይቱ ወቅት በተነሱ ዋና ዋና ጥያቄዎች ላይ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕረዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ ምላሽና ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል፡፡ በፓናሉ ማጠቃለያ ፕረዝዳንቱ የደረጉትን ንግግር የተወሰነ ክፍል ዋና መልዕክት ተርጉሜ አቅርቤላችኋለሁ፡፡ መልካም ንባብ!  ———– “በዚህ ሥራ ውስጥ እስካለን ድረስ የህዝብ … Continue reading ስለኦሮሞና ኦሮሞነት ማንሳት እንደወንጀል መታየት የለበትም – ፕሬዝዳንት ለማ መገርሳ

የዴሞክራሲ አብዮትን “በኢኮኖሚ አብዮት” ማጨናገፍ አይቻልም!

ባለፈው ሳምንት “የኦሮሚያ የኢኮኖሚ አብዮት – በስህተት ላይ ስህተት በመድገም ስህተትን ማረም” በሚል ርዕስ አንድ ፅሁፍ አውጥቼ ነበር። በፅሁፉ ዙሪያ ከተሰጡኝ አስተያየቶች ውስጥ በአብዛኛው “ፅሁፉ የኢኮኖሚ አብዮቱን ዓላማና ግብ በትክክል አይገልፅም” የሚሉ ነበሩ። በመሆኑም ጉዳዩ በዝርዝር ለማብራራት እየተዘጋጀሁ ሳለ የአማራ ክልል ተመሣሣይ የኢኮኖሚ አብዮት ለመጀመር በዝግጅት ላይ መሆኑን የሚገልፁ ዘገባዎች ወጡ። በዘገባው መሰረት የአማራ ክልል … Continue reading የዴሞክራሲ አብዮትን “በኢኮኖሚ አብዮት” ማጨናገፍ አይቻልም!

የኦሮሚያ ኢኮኖሚ አብዮት – በስህተት ላይ ስህተት በመድገም ስህተትን ማረም!

በጦላይ የተሃድሶ ማዕከል በአንድ የማደሪያ ክፍል ውስጥ በአማካይ 100 ሰልጣኞች (እስረኞች) አብረው ያድራሉ። እኔ በነበርኩበት ክፍል ውስጥም 98 ሰልጣኞች (እስረኞች) ነበርን። የተሃድሶ ሥልጠናው ከቀኑ 11፡00 ላይ ይጠናቀቃል። ከምሽቱ 12፡30 በኋላ የመኝታ ቤቶቹ በሮች ከውጪ ይዘጋሉ። ከዚያ በኋላ እስከ ንጋቱ 12፡30 ድረስ በጣም አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረ በስተቀር የመኝታ ክፍሉ በር አይከፈትም። ማታ ማታ አብዛኛው ሰው ከአንዱ … Continue reading የኦሮሚያ ኢኮኖሚ አብዮት – በስህተት ላይ ስህተት በመድገም ስህተትን ማረም!

መንግስትን በእጅጉ የፈተነዉ ቀዉስና የተስተናገደበት አግባብ ሲፈተሽ

(አስጨናቂ ገ/ጻዲቅ ሺፈራዉ (ኮ/ል)) መግቢያ በሀገራችን ከጥቂት ወራት በፊት ተከስቶ ለነበረዉ ሁከት ዋነኛ መነሻ ምክንያት ህዝባዊ ቅሬታዎችን በአግባቡ ማስተናገድ አለመቻላችን እንደደሆነ ይታወቃል፡፡ የህዝቡን ብሶት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ህዝባዊ ቅሬታዉን ወደ አጠቃላይ ቀዉስ በመቀየር ረገድ ጸረ -ሰላም ኃይሎች የተጫወቱት አፍራሽ ሚና ክፍተኛ እንደነበርም የሚዘነጋ አይደለም፡፡ ተቃዉሞን በሰላማዊ መንገድ ማሰማት የዜጎች መብት ሆኖ እያለ መንግስት ይህን … Continue reading መንግስትን በእጅጉ የፈተነዉ ቀዉስና የተስተናገደበት አግባብ ሲፈተሽ

ሕዝብ በእንጀራ ብቻ አይኖርም – በርዕዮተ ዓለም ጭምር እንጂ

አብዮታዊው ኢህአዴግ – ኢትዮጲያን በልል ፌዴራሊዝም (loose federalism) መንፈስ በተቀመረ ህገመንግስት አዲስ ስርአት የመሰረተ እና የመራ፤ ጠንካራ እና የጠራ ርዕዮተ ዓለም እና አባላት የነበረው፤ በዘረጋው ያልተማከለ የፌዴራል ስርአት የተነሳ አገር ሊበታትን እንደሆነ ይታማ የነበረ እና በብሄረተኞችና በግራ ዘመም የብዝኀነት (diversity) ኀይሎች የሚታመን ነበር፡፡ ድኅረ 97 ኢህአዴግ – በይደር ያቆያቸውን ህገመንግስታዊ ድንጋጌዎችን በቅድሚያ ሳይመልስ የመናገሻ ከተማ … Continue reading ሕዝብ በእንጀራ ብቻ አይኖርም – በርዕዮተ ዓለም ጭምር እንጂ

ኢህአዴግ ቀባሪ እንጂ መካሪ አይሻም

በዘንድሮው ዓመት በተለያዩ የሀገራችን አከባቢዎች የፀጥታና አለመረጋጋት ችግር መከሰቱ ይታወቃል። የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች በተደጋጋሚ የተቃውሞ ሰልፍ በማድረግ ጥያቄዎቻቸውን አቅርበዋል። በዚህ አጋጣሚ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በተፈጠረው ግጭት ምክንያት በዜጎች ላይ የአካል ጉዳት፣ የሕይወት መጥፋት እና የንብረት ውድመት ደርሷል። በመሆኑም፣ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የሚከተሉትን የመፍትሄ ሃሳቦች ተግባራዊ ማድረግ ያሻል፡፡ 1ኛ፡- ነፃ ምርጫ በማካሄድ ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ማድረግ፣ … Continue reading ኢህአዴግ ቀባሪ እንጂ መካሪ አይሻም

ኢትዮጲያ የማን ናት:- የወጣቶች ወይስ የባለስልጣናት?

ባሳለፍነው ሳምንት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ተቃውሞ ሰልፍ በወጡ ዜጎች ላይ በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች የተወሰደው እርምጃ ከማሳሰብ አልፎ በጣም አስጨንቆኝ ነበር። እንደ ሀገርና ሕዝብ ሕልውናችን አደጋ ላይ እየወደቀ እንደሆነ ተሰምቶኛል። በአካል ሆነ በስልክ ያገኘኋቸውን ሰዎች ስጠይቅ የነበረው፤ “ሰላማዊ ሰልፍ ስለወጣን ለምን ይገድሉናል?” እና “ለምንድነው የመንግስት ባለስልጣናት የህዝቡን ጥያቄ የማይሰሙት?” የሚሉትን ነበር። ጥያቄዎቹ እንዳስጨነቁኝ አልቀሩም፣ መልስ አገኘሁላቸው። … Continue reading ኢትዮጲያ የማን ናት:- የወጣቶች ወይስ የባለስልጣናት?

ኦሮሚያን ለአመፅ፣ አዲስ አበባን ለቆሻሻ የዳረገች አንቀፅ

ባለፈው ሳምንት ሌ/ጄ ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ባወጡት ረጅም ፅሁፍ ስለሀገሪቱ ወቅታዊ ችግሮች መንስዔና መፍትሄ ስፊ ትንታኔ ሰጥተዋል። ፅሁፉ ለወቅታዊ ችግሮች መፍትሄውና መንስዔው ያለው ሕገ-መንግስቱን በአግባቡ በመተግበርና ባለመተግበር ላይ እንደሆነ ይጠቁማል፡፡ ይሄ ጽሑፍ ደግሞ እንዴት አንዲት አንቀፅ በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ክልል ለሚታዩ ወቅታዊ ችግሮች መንስዔና መፍትሄ እንደሆነች ለማሣየት ያለመ ነው፡፡ በዚህም የክልሉ ሕዝብና የከተማው ነዋሪ ብቻ … Continue reading ኦሮሚያን ለአመፅ፣ አዲስ አበባን ለቆሻሻ የዳረገች አንቀፅ