Category Archives: Social

የቋንቋ ፖሊሲ ለካቢኔ ሊቀርብ ነው | የአማርኛን ፋይዳ ለማሳደግ ተመከረ

በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስተባባሪነት የተዘጋጀው የቋንቋ ፖሊሲ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ሊቀርብ ነው። ረቂቅ ፖሊሲው ላለፉት ሁለት ዓመታት ሀገራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቋንቋዎችና ባህሎች አካዳሚ ጋር በመተባበር በባለድርሻ አካላት ሲገመገም ነው የቆየው። ትላንትና ከትናንት ወዲያ በተካሄደው የመጨረሻ ግብአት ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ ፥ የህዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላትን ጨምሮ ሌሎችም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት የተውጣጡ … Continue reading የቋንቋ ፖሊሲ ለካቢኔ ሊቀርብ ነው | የአማርኛን ፋይዳ ለማሳደግ ተመከረ

እግረኞችን ጭምር የሚቀጣው የትራፊክ ደንብ ተግባራዊ ሆነ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ትራፊክ ጽ/ቤት ከሁለት ዓመት በፊት የወጣውንና እስካሁን ያልተተገበረውን የፌደራል የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ አሽከርካሪዎች ላይ ተግባራዊ ማድረግ እንደጀመረ ተገለፀ፡፡ የእግረኞች እና “ሌሎች የደንብ መተላለፎች”ን የሚመለከተው የደንቡ ክፍል በቅርቡ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል፡፡ ከሚያዚያ 1 ቀን 2005 ጀምሮ አዲሱ የትራፊክ መቆጣጠርያ ደንብ በሥራ ላይ መዋሉን የገለጹት የትራፊክ ጽ/ቤት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ዋና … Continue reading እግረኞችን ጭምር የሚቀጣው የትራፊክ ደንብ ተግባራዊ ሆነ

መጅሊሱ እንዴት ሰነበተ? (Teshome Kemal)

መጅሊሱ በአዲስ መልክ ከተመረጠ ጥቂት ወራትን አስቆጥሯል፡፡ መጅሊሱ ሕዝበ ሙስሊሙን እንዲያገለግል፣ እንዲያረጋጋ፣ ወደተሻለ አቅጣጫም እንዲመራ፣ በመካከሉ ያሉ አለመግባባቶችን ለመቀነስ ብሎም ለማስወገድ እንዲችል ሙስሊሙ ኅብረተሰብ የልማቱ ግንባር ቀደም ተሰላፊና ተጠቃሚ እንዲሆን አመቺ ሁኔታን እንዲፈጥር ይጠበቃል፡፡ አብዛኛዎቹ አመራሮችም እንሞክረው፣ ኢስላማዊ ኃላፊነታችንን እንወጣ በሚል እንጅ የተሻለ ገቢ ለማስገኘት በሚችል ሥራ ላይ ለመሳተፍ የሚችሉ ናቸው፡፡ ሁሉም የየራሳቸው የሆነ የተረጋጋ … Continue reading መጅሊሱ እንዴት ሰነበተ? (Teshome Kemal)

Social | አድርባዮች አደጋዎች ናቸው

አድር–ባይ አድር ብሎ ያልሆነውን ነው የሚል የሆነውን ደግሞ የለም አልተደረግም ብሎ የሚክድ ነው። ይህን እንደ አስተዋጾ ቆጥሮም ለሞላጫ አድራጎቱ ዳረጎት ከአለቃው የሚጠብቅ መሰሪ ግን በራሱ መተማመን የማይችል ምስኪን ነው። አድርባይነት በየትኛውም ትግል እና ግንኙነት ውስጥ ብዙ ጊዜ ችላ የሚባል ግን ውስጥ ውስጡን ሰፊ ጉዳት የሚያደርስ ምግባረ ብልሹነት ነው። የገዥ ፓርቲም ይሁኑ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት አድርባዮች … Continue reading Social | አድርባዮች አደጋዎች ናቸው

የትራንስፖርት ሚኒስቴር የምሽት ጉዞዎችን ሊከለክል ነው

የመንገድ ትራፊክ አደጋዎችን ለመከላከል የምሽት ጉዞዎችን እንደሚከለክል የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የትራንስፖርት ሚኒስቴር የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ላይ የሚፈጠሩ አደጋዎችን ለመከላከል የአጭር ጊዜ የቁጥጥርና ክትትል ስራን ለመስራት የሚያስችለውን ዝግጅት አጠናቅቋል፡፡ ለመንገድ የትራፊክ ደህንነት አደጋ መንስኤዎች ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር፣ ህገወጥ የሌሊት ጉዞ ፣ ከተፈቀደ የሰው ቁጥር በላይ መጫን የመንገድ ህግና ስርአትን አለማክበር ዋነኞቹ ናቸው፡፡ በተለይ በህገወጥ የሌሊት ጉዞ … Continue reading የትራንስፖርት ሚኒስቴር የምሽት ጉዞዎችን ሊከለክል ነው

በፌስቡክ ሜዳ (በሰርካለም ቦጋለ) [Amharic]

ድንገት በጐዳና ላይ ሲሄዱ ከአሁን ቀደም በውል የማያውቁት ሰው አጥብቆ ሰላም ቢልዎትና ሊያወጋዎም ቢከጅል የት ታውቀኛለህ? ብሎ መደንፋትና ተገላምጦ መሄድ የለም። ምክንያቱም በማህበረሰቡ ድረገጽ ጐዳና እንተዋወቅ ብለው እራስዎን ይፋ አድርገው ቀርበዋልና ነው፡፡ የፌስቡክ ጓደኝነት ጅማሮው በአንድ የጽሑፍ መልእክት መነሻነት አልያም በድረ ገፁ ማህደር ባሉ ፎቶዎች መስህብነት ሊሆን ይችላል፡፡ «ወዳጅነቴን ተቀበለኝ» ብሎ ጥያቄ ያቀረበው ጠያቂ የይሁንታ … Continue reading በፌስቡክ ሜዳ (በሰርካለም ቦጋለ) [Amharic]