Category Archives: Social

ኢህአዴግን የጠለፈው “የአመራር ወጥመድ”

ከአስር ቀን በፊት አዲስ አድማስ ጋዜጣ በመንግስት አመታዊ ሪፖርቶች ዙሪያ ያቀረበውን ዘገባ ተመልክታችኋል? ነገሩ “ስህተትን መደባበቅና ማስመሰል መደበኛ የአሰራር ስልት ሆነ እንዴ?” ያስብላል። በእርግጥ ሁሉም ባለስልጣናት ያው እንደ እኔና እናንተ “ሰው” ናቸው። እንደ ማንኛውም ሰው ስህተት ሊሰሩ ይችላሉ። ችግሩ የእኛ ባለስልጣናት እንደ አምላክ ፍፁም መሆን ይቃጣቸዋል። በስህተት ላይ ስህተት እየሰሩ፤ “ተሳስታችኋል” ሲባሉ አይሰሙም፣ “ተሳስተናል” ብለው … Continue reading ኢህአዴግን የጠለፈው “የአመራር ወጥመድ”

የክብር ዶክትሬት ሸፍጥ እና መንደሬነት

በርግጥ የሰው ልጅ ለሚያበረክተው የላቀ አስተዋፅኦ እዉቅናና ክብር መሰጠቱ ይበል እሚያስብል ነገር ነው። በተለይ እንደኛ ዓይነት ባለ ሃገሩንና ህዝቡን ለዘመናት ሲያገለግል የኖረን ዜጋ በቀላሉ አሽቀንጥሮ በሚጥል ማሕበረሰብ እዉቅና መስጠት መጀመሩ መበረታታት አለበት። ሆኖም በየዓመቱ የክብር እየተባለ እየተሰጠ ያለው የክብር ዶክትሬት ግን በብዙዎች ዘንድ እየተወገዘ ቢሆንም ኣሁንም ዩኒቪርሲቲዎቻችን በተለመደው መንገድ እየነጎዱ ነው። ይሄ የክብር ዶክትሬት የሚባል … Continue reading የክብር ዶክትሬት ሸፍጥ እና መንደሬነት

የደሞወዝ እድገት ቀርቶብኝ የአካዳሚክ ነፃነቴን ስጡኝ

በከፍተኛ የትምህርት ተቋም ውስጥ የ10 ዓመት የማስተማር ልምድ አለኝ። ላለፉት ሁለት ዓመታት ደግሞ የአንድ ት/ት ክፍል ኃላፊ ሆኜ እየሰራሁ እገኛለሁ። የማስተማር ሥራውን በጣም እወደዋለሁ። ከተማሪዎቼ ጋርም ልዩ ፍቅርና ቀረቤታ እንዳለኝ አምናለሁ። በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ድግሪ አብረውኝ የተማሩ የክፍል ጓደኞቼ አብዛኞቹ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በመምህርነት በመቀጠር ነው ወደ ስራ አለም የገቡት። ሆኖም ግን፣ ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ … Continue reading የደሞወዝ እድገት ቀርቶብኝ የአካዳሚክ ነፃነቴን ስጡኝ

ኢትዩጲያ ውስጥ “ምሁር” አለ እንዴ?

በተለያዩ ሚዲያዎች፤ “አንዳንድ የዘርፉ ‘ምሁራን’ በሰጡት አስተያየት…፣ ‘ከምሁራን’ ጋር በተደረገ ውይይት…” ሲባል መስማት የተለመደ ሆኗል። እንደው በየቦታው “ምሁራን” ሲባል ስቅጥጥ ይለኛል። ምክንያቱም፣ ክብር ያለ ቦታው ሲሰጥ ትርጉም ያጣል። በዚህ ፅሁፍ፣ ከግል ሰብዕና፣ ሥራና ተግባር አንፃር “ማን ነው ‘ምሁር’ (Intellectual)?” የሚለውን በዝርዝር እንመለከታለን። የኣማርኛ መዝገበ ቃላት “ምሁር” የሚለውን ቃል “በትምህርት፥ በዕውቀት የበሰለ አዕምሮ ያለው ሰው” እንደሆነ … Continue reading ኢትዩጲያ ውስጥ “ምሁር” አለ እንዴ?

የአመራር ብቃት በዘበኛ ሰላምታና በፀኃፊ ፈገግታ ይለካል!

ሚያዚያ 26/2008 ዓ.ም እኔና ስድስት የሥራ ባልደረቦቼ ወደ ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለሥራ ተጉዘን ነበር። ጉዟችንን የጀመርነው ከሌሊቱ 11፡30 ላይ ሲሆን ከጠዋቱ 4፡30 አከባቢ ሃዋሳ ደረስን። ከዚያ በኋላ ባለው አንድ ሰዓት ውስጥ የታዘብኩት ነገር “ለካስ መልካም አስተዳደር ያለው ከኃላፊዎች ቢሮ ውስጥ ሳይሆን በር ላይ ነው፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ማለት የዘበኛ ሰላምታና የፀኃፊ ፈገግታ ነው!” እንድል አስገድዶኛል። በዩኒቨርሲቲው … Continue reading የአመራር ብቃት በዘበኛ ሰላምታና በፀኃፊ ፈገግታ ይለካል!

ከመወዳደር – አማራጭ ማሳጣት

እኛ እኮ ውድድር አንወድም፣ ፉክክር እንጠላለን! እኛ መወዳደር አያስደስተንም፣ መፎካከር ያስጠላናል። በሁሉም ዘርፍ፤ በፖለቲካ፥ በማህበራዊ ሆነ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴያችን ውድድር አንፈልግም፣ ፉክክር ያስጠላናል። በእርግጥ እኛ ኢትዮጲያዊያን ውድድር የማንወደው መወዳደር ስለማንፈልግ ነው። ተወዳዳሪ የማንወደው ለመወዳደር አቅም ስለሌለን ነው። ፉክክር የምንጠላው ለመፎካከር ብቃት ስለሌለን ነው። በውድድር ብንሳተፍ ከሌሎች ጋር ተፎካካሪ ለመሆን ስለማንችል ነው። በፉክክር ከሌሎች የተሻለ ነገር ለማቅረብ … Continue reading ከመወዳደር – አማራጭ ማሳጣት

ዝግመትና መንግስት፡ ነፃነትና ፍጥነት

በእርግጥ አነሳሴ፣ በሀገራችን ያለውን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ተደራሽነትና ሰሞኑን ኢትዮ-ቴሌኮም እየወሰዳቸው ባሉት እርምጃዎች ዙሪያ የዳሰሳ ፅሁፍ ለማቅረብ ነበር። የዓለም የቴሌኮምዩኒኬሽን ማህበር (ITU) በ2015 የፈረንጆች አመት ያወጣውን ሪፖርት በወፍ-በረር እያነበብኩ ነበር። የአለም ሀገራት በዘርፉ ያላቸውን የልማት ደረጃ ከሚያሳው ሰንጠረዥ ውስጥ ኢትዮጲያን ከላይ ወደ ታች እየወረድኩ ብፈልጋት አጣኋት። ፍለጋዬን ከታች ወደ ላይ አድረኩ። 167ኛ፡ ቻድ፣ 166ኛ፡ ኤርትራ፣ 165ኛ፡- … Continue reading ዝግመትና መንግስት፡ ነፃነትና ፍጥነት

ቴዲ አፍሮዎቻችን እና ‘ፍቅሮቻቸው’

ይህን ፅሑፍ ለመፃፍ መንስኤ የሆነኝ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጱያ የታሪክና የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ አንዳንድ የኪነጥበብ ሰዎችና የነሱ ‘ተከታይ’ አድናቂዎቻቸው የሚሰነዝሩት በስሜት የተሞላና በአብዛኛውም ከእዉነታ የራቀ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ሁኔታዎችን (ያሉትም ያለፉትም) አዛብቶ የማቅረብ አባዜ በብዛት በማስተዋሌ ነው፡፡ የዚህ ቁንጮ ተዋናይ ደግሞ ቴዲ አፍሮ ሲሆን በዚህ ፅሑፍ የዚህ ታዋቂ አቀንቃኝ አጠቃላይ ይዘትና እርስ በርሱ የሚጋጭ ፖለቲካዊ ተምኔትና … Continue reading ቴዲ አፍሮዎቻችን እና ‘ፍቅሮቻቸው’

ሀገር ማለት ነፃነት ነው!

ድሮ – ድሮ “ሀገር ማለት መሬት ነው” ይባል ነበር። ቀጠለና “ሀገር ማለት ሰው ነው” የሚለው መጣ። ባለፈው ሳምንት “ሀገር ማለት ትዝታ ነው” የሚል ፅሁፍ በወጣ በማግስቱ “ሀገር ማለት አስተሳሰብ ነው” የሚል ሌላ ፅሁፍ በማህበራዊ ድረገፅ ላይ ተለጥፎ አነበብኩኝ። ነገሩ ገርሞኝ ሌሎች ፅሁፎችን ሳፈላልግ፤ “ሀገር ማለት እናት ናት”፣ “ሀገር ማለት ሕገ-መንግስት ነው”፣ እና አንዳንድ ጭራሽ ግራ … Continue reading ሀገር ማለት ነፃነት ነው!

ቦጫቂና ወጋሚ ጋዜጠኞች – በሞላበትና በመሸበት…

ባለፉት አራት ወራት በኦሮሚያ ክልል የታየው የህዝብ ተቃውሞ ከብዙ ጋዜጠኞች ጋር ለመገናኘት አጋጣሚ ፈጥሮልኛል። በተለይ በታህሳስ ወር የመጀመሪያ ሳምንት በወሊሶ ከተማ ከፍተኛና ያልተጠበቀ የሕዝብ ተቀውሞ ተካሂዶ ስለነበር በዚያ ዙሪያ ወደ ዘጠኝ የሚጠጉ ጋዜጠኞች በስልክና በአካል አነጋግረውኛል። ከእነዚህ ውስጥ ሦስት ጋዜጠኞች ሁኔታውን ለመዘገብ ወደ ወሊሶ መጥተው የነበረ ሲሆን አንዱ ኢትዮጲያዊ፣ የተቀሩት የእንግሊዝ እና የአሜሪካ ዜጋ ነበሩ። … Continue reading ቦጫቂና ወጋሚ ጋዜጠኞች – በሞላበትና በመሸበት…