Category Archives: Security

ከስምንት ሀገራት የመጡ 853 ሰልጣኞች በመከላከያ ተቋማት ሰልጥነዋል።

(ቤተልሄም ባህሩ) የመከላከያ ሰራዊት በአቅም ግንባታና ህብረተሰቡን በልማት በማገዝ በኩል ያደረገው አስተዋፅዖ የሚበረታታና ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባ እንደሆነ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገለፀ፡፡ ምክር ቤቱ ትናንት ባካሄደው አራተኛ የስራ ዘመን 21ኛ መደበኛ ስብሰባው የመከላከያ ሚኒስቴርን የግማሽ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት አድምጧል። የሚኒስቴሩ ሪፖርት እንደሚያመለክተው ሰራዊቱን በወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ እንዲሁም በአካዳሚክ ትምህርት የማብቃት ስራ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ … Continue reading ከስምንት ሀገራት የመጡ 853 ሰልጣኞች በመከላከያ ተቋማት ሰልጥነዋል።

በአሶሳ ዞን ታጣቂዎች ዘጠኝ ሰዎች ገደሉ

ትላንት ሚያዚያ 7/2006ዓ.ም ማለዳ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአሶሳ ዞን ሰዎችን ጭኖ ሲጓዝ በነበረ ፒካ አፕ መኪና ላይ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት በሰው ህይወትና አካል ላይ ጉዳት መድረሱን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ገለፀ፡፡ ጽ/ቤቱ ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች በተሽከርካሪው ላይ ጥቃቱን ያደረሱት ከንጋቱ 12 ሰዓት ተኩል አካባቢ፣ የክልሉ ርዕሰ መዲና ከሆነው ከአሶሳ ከተማ 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ … Continue reading በአሶሳ ዞን ታጣቂዎች ዘጠኝ ሰዎች ገደሉ

የተሳሳቱ ዘገባዎች በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዙሪያ (ዮናስ ቢራቱ)

የተጠለፈውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ (በረራ #ET_702) በተመለከተ ሰሞኑን እጅግ በርካታ የተምታቱ መረጃዎች ሲሰራጩ ሰንብተዋል። ከድጋፍ እና ተቃውሞ ባሻገር አንዳንድ ጉዳዩን እናውቃለን የሚሉ ሰዎች ስለ አየር መንገዱ የሚሰጡት አስተያየት ደግሞ ከመጋነን ባለፈ ስህተትም ጭምር ነው። መረጃ የሚፈልጉ ሚዲያዎች በቀጥታ የአየር መንገዱን ሃላፊዎች ማነጋገር ሲገባቸው በተቃራኒው ስዎችን በመጠየቅ ተጠምደው ከርመዋል። ይህንን ለማለት ያበቃኝ የኢሳት ጋዜጠኛ የሆነው ፋሲል … Continue reading የተሳሳቱ ዘገባዎች በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዙሪያ (ዮናስ ቢራቱ)

‹በኢሳት ላይ የቀረበው ዘገባ በጣም የተሳሳተ ነው› – የጠላፊው ታላቅ ወንድም

ኢሳት የተባለው የዲያስፖራ ሚዲያ የኢትዮጲያ አየር መንገድ አውሮፕላን በረራ ቁጥር 702ን ጠልፎ ጄኔቭ ያሳረፈው ኃይለመድህን አበራን አስመልክቶ ያስተላለፈው ዘገባ ከእውነት የራቀ መሆኑን ቤተሰቡ ገለጸ፡፡ በዶ/ር ብርሀኑ ፓርቲ ‹‹ግንቦት 7›› አመራር እና የገንዘብ ድጋፍ የሚንቀሳቀሰው ኢሳት በዛሬው ዕለት ባቀረበው ዘገባ፤ በውጭ ሀገር ነዋሪ የሆኑ የጠላፊውአክስት ነኝ ባይ ሴትዮ በማቅረብ ጉዳዩን ‹‹አማራን ነጻ የማውጣት›› ትግል አድርጎ አቅርቦታል፡፡ … Continue reading ‹በኢሳት ላይ የቀረበው ዘገባ በጣም የተሳሳተ ነው› – የጠላፊው ታላቅ ወንድም

የአውሮፕላን ጠላፊው ‹በታላቅ የመንፈስ ጭንቀት እየተሰቃየ› ነበር:- የጠላፊው እህት

ባለፈው እሁድ ሌሊት እኩለ ለሊት ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ጣሊያ ሮም ሲበር የነበረው የአትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የበረራ ቁጥር ኢት-702 ላይ ጠለፋ ሰኞ ጥዋት ሲውስዘርላድ ጀኔቭ አርፏል፡፡ ጠለፋ ያደረገው የአውሮፕላኑ ረዳት አብራሪ ኃይለመድህን አበራ ተገኝ ሲሆን፤ ጠለፋውን ያደረገው ዋና ፓይለቱ ለረፍት ወጣ ባለበት ቅፅበት የፓይለት መቀመጫ ክፍሉን በመቆለፍ መሆኑ የተዘገበ ሲሆን ጠላፊው ስዊዘርላንድ ፖሊስ ተይዞ … Continue reading የአውሮፕላን ጠላፊው ‹በታላቅ የመንፈስ ጭንቀት እየተሰቃየ› ነበር:- የጠላፊው እህት

Ethiopia:- ለ35 መኮንኖች የጄነራልነት ማዕረግ ተሰጠ

የኢትዮጵያ መንግስት አንድ የሌተናንት ጄነራል፣ 6 የሜጄር ጄነራል እና 28 የብርጋዴር ጄነራል ሹመት ሰጠ፡፡ በተሰጠው ሹመት መሰረት፡- ሌተናንት ጄነራል ሆነው የተሾሙት – ሜጄር ጄነራል ዮሀንስ ገ/መስቀል ተስፋማሪያም ሲሆኑ፤ ሜጄር ጄነራል ሆነው የተሾሙት፡- 1.ብ/ጀነራል ፍስሀ ኪዳኑ ፋንታ 2. ብ/ጀነራል ተስፋይ ግደይ ኃይለሚካኤል 3. ብ/ጀነራል ዮሀንስ ወ/ጀወርግስ ተስፋይ 4.ብ/ጀነራል ኢብራሂም አብዱልጀሊል መሀመድዜን 5. ብ/ጀነራል ገብረ አድሀና ወለዝጉ 6. ብ/ጀነራል … Continue reading Ethiopia:- ለ35 መኮንኖች የጄነራልነት ማዕረግ ተሰጠ

የሀይማኖቶቸ ጉባኤ የፀረ-አክራሪዎች ሰልፍ ሊያካሂድ ነው

(ፍቃዱ ፈንቴ) አክራሪዎች በእምነት ስም የህዝብን ሰላም ለማደፍረስ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በመቃወም እሁድ ነሃሴ 26/2005 ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርግ የአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ገለፀ፡፡ ሰልፉ ሁሉም የሀይማኖት ተከታዮች በሰላም አብሮ ለመኖር ያላቸውን ቁርጠኝነት ማሳያ ነው ተብሏል፡፡ ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ በእምነት ስም የሀገሪቱን ሰላም ለማደፍረስ ጥረት የሚያደርጉ አካላትን በመቃወም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተደጋጋሚ ሰላማዊ ሰልፍ መደረጉ የሚታወስ … Continue reading የሀይማኖቶቸ ጉባኤ የፀረ-አክራሪዎች ሰልፍ ሊያካሂድ ነው

ስለሕዳሴ ግድብ፡- የ‹አንድነት› ፓርቲ መግለጫ [ሙሉ ቃል]

ባለፈው ዓርብ ‹አንድነት› ፓርቲ ስለሕዳሴ ግድብ የሰጠውን መግለጫ አስመልክቶ ኢቲቪ ያተመውን ዜና እዚህ ብሎግ ላይ ደግመን ማተማችን ይታወሳል፡፡ የፓርቲውን ሙሉ መግለጫ ዛሬ ያገኘን ሲሆን፣- ከኢቲቪ በወሰድነው ዜና ላይ ከቀረበው ጋር ትርጉም ያለው ልዩነት ባይኖረውም የ‹አንድነት› ፓርቲ ደጋፊ የሆኑ አንባቢዎቻችን ባቀረቡት ቅሬታ ምክንያት የመግለጫውን ሙሉ ቃል አትመነዋል፡፡ ለቀጣይ ግን እኛን ከመተቸት ይልቅ ፓርቲያቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ሲጠራ … Continue reading ስለሕዳሴ ግድብ፡- የ‹አንድነት› ፓርቲ መግለጫ [ሙሉ ቃል]

Brief | የፕ/ር መስፍን የ‹አባይ ጦርነት› ግልብ ትንተናና ምክር

(Daniel Berhane) ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም ባለፈው እሮብ ከአባይ ጉዳይ በተያያዘ የጦርነት ቅስቀሳን ለመገሰጽና የግብጽን የጦር ሀያልነት ‹ለማሳወቅ› አንድ ጽሑፍ አስነብበውናል፡፡ ጽሑፉ በጥድፊያ እና/ወይም እንደተለመደው የኢሕአዴግን ባለስልጣኖች ለማብሸቅ ተብሎ የቀረበ ስለመሰለኝ አላተኮርኩበትም ነበር፡፡ ነገር ግን እሳቸው የጽሑፋቸውን ግልብነት (shallowness) አስተውለው – ጠለቅ ያለ ማብራሪያ በመስጠት ለማጠናከር ወይም ለማስተባበል ይሞክራሉ ብዬ ስጠብቅ፣ ትችት የሰነዘሩባቸውን ሰዎች በመሀይምነት መፈረጅ ነው የመረጡት፡፡ ሰለሆነም እንደው ምናልባት … Continue reading Brief | የፕ/ር መስፍን የ‹አባይ ጦርነት› ግልብ ትንተናና ምክር

የውጭ ጉዳይ ሚ/ር የግብጽን አምባሳደር ጠርቶ ማብራሪያ ጠየቀ

ኢትዮጵያ በመከባበርና በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ እንደምታራምድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ ኢትዮጵያ ከጎረቤት እና ከሌሎችም አገሮች ጋር በመከባበርና በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ፖሊሲ በጽናት ስታራምድ መቆየቷ ሚኒስቴር መስርያ ቤቱ አስታውቋል፡፡ በመሆኑም በህዳሴ ግድብ ዙሪያ በግብጽ ዘንድ ሰፍኖ የቆየውን ጥርጣሬ ለማስወገድ ግድቡ ግብጽንም ሆነ ማንኛውንም የታችኛውን ተፋሰስ አገር እንዳይጎዳ የሚያረጋግጥ የግብጽ፣ የሱዳን፣ የኢትዮጵያ … Continue reading የውጭ ጉዳይ ሚ/ር የግብጽን አምባሳደር ጠርቶ ማብራሪያ ጠየቀ