Category Archives: Security

ጽድቁ ቀርቶ በቅጡ በኮነነኝ – ለሜ/ጄነራል አበበ ተ/ሃይማኖት የተሰጠ ምላሽ

(እውነቱ አሸናፊ) እኔ ታጋይም የኢህአዴግ አባልም አልያም የሰራዊት አባልም አይደለሁም፤ የምኖረውም በስደት ምክንያት ኢትዮጵያ ውስጥ አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ ከአገሬ ብዙም ሩቅ አይደለሁም በተደጋጋሚም እመላለሳለሁ:: በአገራችን በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ምክንያት እየታየ ያለው የሰላም፣ የልማትና የዲሞክራሲ ግንባታ ሂደት ትክክለኛ በመሆኑ በፅኑ ደጋፊ ነኝ:: በዚህም ይህን ስርዓት እንድንገነባ መንገዱን ላሳዩን ለታላቁ መሪያችን ክቡር አቶ መለስ ያለኝ ክብርና ፍቅር ወሰን … Continue reading ጽድቁ ቀርቶ በቅጡ በኮነነኝ – ለሜ/ጄነራል አበበ ተ/ሃይማኖት የተሰጠ ምላሽ

የሃገራችን ፖለቲካዊ ሁኔታና የመፍትሔ ሃሳቦች (ሌ/ጄ ፃድቃን ገ/ትንሳኤ)

(ሌተናል ጄኔራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ) መግቢያ ከሃያ አምስት ዓመት ኢህአዴግ የደርግን መንግስት በጦርነት አሸንፎ የሀገራችንን ፖለቲካዊ ስልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ፤ ቀስ በቀስ እያደጉ የመጡ ፖለቲካዊ ችግሮች በግልፅ ጎልተው መታየት ጀምረዋል፡፡ አሁን ገዥው ፖርቲና ፖርቲው የሚመራው መንግስትም የችግሮቹን መኖር አምኖ ለመፍታት እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ መንገር ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ ይህ ሁኔታ ለማንኛውም የሀገሩን ደህንነትና ሰላም፤ ቀጣይነት ያለው ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ማህበራዊ ብልፅግና፤ … Continue reading የሃገራችን ፖለቲካዊ ሁኔታና የመፍትሔ ሃሳቦች (ሌ/ጄ ፃድቃን ገ/ትንሳኤ)

ከጓንታናሞ እስከ ማዕከላዊ፡ ክፍል 4 – “እውነትን በጉልበት”

“ከጓንታናሞ እስከ ማዕከላዊ” በሚለው ተከታታይ ፅሁፍ፤ በክፍል-1 “የፀረ-ሽብር ሽብር” – ሽብርተኝነትን በፀረ-ሽብር ዘመቻና ጦርነት/ዘመቻ መግታት እንደማይቻል፤ በክፍል-2 “ፍርሃትን በፍርሃት” – በፍርሃት የሚወሰዱ አብዛኞቹ የፖለቲካና ወታደራዊ እርምጃዎች ስህተት እንደሆኑ፤ እንዲሁም በክፍል-3 “የአሸባሪዎች ሕግ” – የሽብር ጥቃት በደረሰ ማግስት የሚወጡ አዋጆችና መመሪያዎች የዜጎችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ሊገድቡ እንደሚችሉ ተመልክተናል። በመጨረሻው ክፍል-4 ደግሞ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በታሰሩ እስረኞች … Continue reading ከጓንታናሞ እስከ ማዕከላዊ፡ ክፍል 4 – “እውነትን በጉልበት”

ከጓንታናሞ እስከ ማዕከላዊ፡ ክፍል 3 – “የአሸባሪዎች ሕግ”

በዚህ “ከጓንታናሞ እስከ ማዕከላዊ” በሚለው ተከታታይ ፅሁፍ፤ በክፍል-1 “የፀረ-ሽብር ሽብር” – የሽብር ጥቃትን በፀረ-ሸብር ጦርነት/ዘመቻ መፍትሄ ለመስጠት መሞክር በተሳሳተ እሳቤ ላይ የተመሰረተ ስለመሆኑ ተመልክተናል። በክፍል-2 ደግሞ “ፍርሃትን በፍርሃት” በሚል ርዕስ የአሸባሪዎችን ጥቃት በፈጠረው ፍርሃትና ስጋት ውስጥ ሆኖ የሚወሰድ የፖለቲካና ወታደራዊ እርምጃ ውጤቱ ሌላ ተጨማሪ ፍርሃትና ስጋት እንደሆነ አይተናል። የዚህ ክፍል ዋና ትኩረት ደግሞ “የሕዝብን ሰላምና … Continue reading ከጓንታናሞ እስከ ማዕከላዊ፡ ክፍል 3 – “የአሸባሪዎች ሕግ”

ጉንጭን ማልፋት ይሻላል ከጦርነት

የ2ኛው ዓለም ጦርነት ሲነሣ የአንድ ሰው ስም አብሮ ይነሳል። በወቅቱ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት የዊኒስተን ቸርችል ስም። ይህ ታላቅ መሪ በሀገሩ እንግሊዝ ሉዓላዊነት ላይ የተቃጣውን አደጋ በመመከት የቁርጥ ቀን መሪ መሆኑን አስመስክሯል። በዚህ ረገድ የዋለው ውለታ ለሀገሩ ብቻ አልነበረም። በተለይ በናዚ ጀርመን እና ፋሽስት ኢጣሊያ ቁጥጥር ስር ለወደቁት ሀገራት ጭምር ባለውለታ ነው። ከዚህ ውስጥ ሀገራችን … Continue reading ጉንጭን ማልፋት ይሻላል ከጦርነት

ደርግነት እያቆጠቆጠ – ዴሞክራሲው እየጨላለመ ነው – ህዝቦች ጠንቀቅ በሉ! (ሜ/ጄ አበበ ተክለሃይማኖት)

አበበ ተክለሃይማኖት(“ጆቤ”) (ሜጀር ጄኔራል፣ PhD Candidate) መግቢያ የሃገራችን መንግስትና የገዢው ፓርቲ አጠቃላይ ችግር ዉስጥ በመግባታቸው ምክንያት እዚህና እዝያ እሚታዩ ችግሮች እየተስተዋሉ ነው። ሰሞኑን እንዃ ብናይ ከኦሮሞ ህዝባዉ ዓመፅ፣ ሜቴክና ስዃር ፋብሪካ፣ ከጋምቤላ ጠለፋና ግድያ፣ በኤርትራ በኩል የሚመጣ ተከታታይነት ያለው ዜጎቻችንን የማበሳበስ ሁኔታ እያስተዋልን ነው። የድርቁና በየክልሉ የሚታዩ የህዝቦች መነሳሳት ተጠቓሽ ናቸው። እነዚህ የሚፈጠሩ ነገሮች ካጠቃላይ … Continue reading ደርግነት እያቆጠቆጠ – ዴሞክራሲው እየጨላለመ ነው – ህዝቦች ጠንቀቅ በሉ! (ሜ/ጄ አበበ ተክለሃይማኖት)

መንግስት ግዴታ እንጂ መብት የለውም!

ነፃነት የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባህሪ ስለሆነ እንቅስቃሴው በሙሉ ከዚያ ጋር የተቆራጀ ነው። መብትና ግዴታ፣ ሕገ-መንግስትና የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ፣ ሀገርና መንግስት፣… የሁሉም መሰረታዊ ዓላማ የሰው ልጅን ነፃነት ማክበርና ማስከበር ነው። ከሰው በስተቀር የሚከበር መብት ያለው ሌላ አካል የለም። ከቅርብ ግዜ ወዲህ ግን በሀገራችን እየወጡ ያሉ ሕጎችና አዋጆች መንግስትንና ባለስልጣናት “መብት እንዳላቸው” ታሳቤ ያደረጉ ናቸው። ነገር ግን፣ … Continue reading መንግስት ግዴታ እንጂ መብት የለውም!

ጋምቤላ ክልል እና ብሄራዊ የፀጥታ ስጋት – ኣጭር ቅኝት

በደርግ ዘመነ መንግስት በጆን ጋራንግ የሚመራው የደቡብ ሱዳን ነፃ ኣውጪ (SPLM) በጋምቤላ ክልል ወታደራዊ ካምፖች ነበሩት። ኢህኣደግ ደርግን ላይመለስ ሲገረስስ የSPLM እጣ ፈንታ ኣገር ለቆ መውጣት ወይ ድግሞ ትጥቁን ኣራግፎ ስደተኛ ካምፕ ገብቶ መኖር ነበር። በወቅቱ ሁለቱም ኣማራጮች የሚዋጡለት ስላልነበሩ ከባሮ ወንዝ ወዲያ ያለው የጋምቤላ (የኢትዮጵያ) ግዛት የራሴ ነው በማለት በቁጥጥሩ ስራ ማዋልን መረጠ። ደርግ … Continue reading ጋምቤላ ክልል እና ብሄራዊ የፀጥታ ስጋት – ኣጭር ቅኝት

የተገኘዉን ሰላምና እድገት የሚንድ የአመራር ዘይቤ ባስቸዃይ ይታረም!(ሜ/ጄ አበበ ተ/ሃይማኖት)

አበበ ተክለሃይማኖት(“ጆቤ”) (ሜጀር ጄኔራል፣ PhD Candidate) ታላቁ የሰላምና ደህንነት ሙሁሩ ጆሃን ጋልቱንግ ስለ ሰላም እሚከተለዉን ይላል “Peace is a revolutionary idea; peace by peaceful means defines that revolution as nonviolent. That revolution is taking place all the time; our job is to expand it in scope and domain. The tasks are endless; the question is … Continue reading የተገኘዉን ሰላምና እድገት የሚንድ የአመራር ዘይቤ ባስቸዃይ ይታረም!(ሜ/ጄ አበበ ተ/ሃይማኖት)

ጦርነት የአቅም ማነስ ምልክት ነው

የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ተወልደ ሙልጌታ፣ የካቲት 18/2008 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ “የኢትዮጲያ መንግስት በታገቱት 80 ኢትዮጲያዊያን ምክንያት በኤርትራ ላይ ተመጣጣኝ ዕርምጃ እንደሚወስድ” ተናግረዋል። መግለጫውን ተከትሎ ከጋዜጠኞች፤ ታጋቾቹ ስለተያዙበት ሁኔታ፣ ማንነት እና መንግስት ሊወስደው ስላሰበው አፀፋዊ እርምጃ ዙሪያ ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት ምላሽ ግን በጣም የሚገርም ነው፦”ከዚህ በላይ ምንም ዝርዝር ማብራሪያ ልሰጥ አልችልም”። በእርግጥ ቃለ … Continue reading ጦርነት የአቅም ማነስ ምልክት ነው