Category Archives: Railway

የቻይና ኤግዚም ባንክ ለመቐለ ወልዲያ ባቡር ፕሮጀክት ብድር ሊለቅ ነው

(ዮሐንስ አንበርብር) የቻይና ኤክስፖርትና ኢምፖርት (ኤግዚም) ባንክ ለመቐለ ወልዲያ የባቡር ፕሮጀክት 1.5 ቢሊዮን ዶላር ብድር ሊለቅ ነው፡፡ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ምንጮች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በሚኒስቴሩ ከፍተኛ ኃላፊዎችና የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ጌታቸው በትሩ የተገኙበት ቡድን በቅርቡ ወደ ቻይና ሄዶ ባንኩ ባስጠናው የአዋጭነት ጥናት ላይ ማብራርያ አቅርበዋል፡፡ የፕሮጀክቱ የአዋጭነት ጥናት በኢትዮጵያ በኩል ከዚህ … Continue reading የቻይና ኤግዚም ባንክ ለመቐለ ወልዲያ ባቡር ፕሮጀክት ብድር ሊለቅ ነው

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ፕሮጀክት 56 በመቶ ተጠናቀቀ

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ፕሮጀክት ግንባታ 56 በመቶ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አስታወቀ። የ7ኛው አገር አቀፍ የከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ጉባኤ ተሳታፊዎች ፕሮጀክቱን ጎብኝተዋል። በኮርፖሬሽኑ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር በሃይሉ ስንታየሁ እንደገለጹት የሰራው ዋና ዋና የሚባሉት ሰራዎች በመጠናቀቅ ላይ ሲሆኑ ግንባታውም በጥሩ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል። ከባድ ከሚባሉት ስራዎች ባቡሩ … Continue reading የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ፕሮጀክት 56 በመቶ ተጠናቀቀ

የታጁራ-አሳይታ-መቀለ የባቡር መስመር ግንባታ

(ጌትነት ምህረቴ) ባቡር ከየብስ የትራንስፖርት በዋጋ ርካሽ እንደሆነ ይነገራል። ፍጥነቱም ከተሽከርካሪ ይበልጣል። በአንድ ጊዜ ብዙ ሰዎችን ሆነ ሸቀጦችን በመጫን የማጓጓዝ አቅም አለው። በተለይ የባቡር ትራንስፖርት ለታዳጊ ሀገሮች የመገንቢያው ወጪ ከፍተኛ ቢሆንም ተመራጭ የትራንስፖርት ዘርፍ እንደሆነ የሚታወቅ ነው። የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ዕድገት ተከትሎ ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ የሚገቡ ሸቀጦች በእጅጉ እየጨመሩ ይገኛሉ። የማዕድን ምርቶችን በተሽከርካሪዎች ብቻ ማጓጓዝ … Continue reading የታጁራ-አሳይታ-መቀለ የባቡር መስመር ግንባታ

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ግንባታ 34 ከመቶ ደርሷል

(ጥላሁን ካሳ) የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ግንባታ ፕሮጀክት ዋና ዋና ስራዎች ክረምቱ ከመጠናከሩ በፊት ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው አለ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን። ኮርፖሬሽኑ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገረው በዚህ አመት ይጠናቀቃል ከተባለው 40 በመቶ ስራ እስከ ግንቦት መጨረሻ 34 ከመቶ በላይ የሚሆነው ተከናውኗል። የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ፕሮጀክት ከሚያልፍባቸው ቦታዎች መካከል በዋነኛነት ጊዮርጊስ አካባቢ በሚገኘውን … Continue reading የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ግንባታ 34 ከመቶ ደርሷል

በባቡር ግንባታ የተነሳ የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ወደ ብሄራዊ ሙዚየም ተዛወረ

በአዲስ አበባ የቀላል ባቡር ግንባታ የተነሳ የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት በግዜያዊነት ወደሚቆይበት ብሄራዊ ሙዚየም ዛሬ ሚያዚያ 25/2005 ተዛውሯል፡፡ ሃዉልቱ በነበረበት ቦታ የመሬት ዉስጥ የባቡር መስመር ይዘረጋል፡፡ የአዲስ አበባ የቀላል ባቡር ግንባታ ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር በሃይሉ ስንታየሁ እንዳሉት ሀዉልቱ አስካሁን በነበረበት መሬት ዉስጥ እስከ 20 ሜትር ጥልቀት በመቆፈር ስራዉ ይከናወናል፡፡ የዉስጥ ለዉስጥ ስራው እስከ መጭው ክረምት አጋማሽ … Continue reading በባቡር ግንባታ የተነሳ የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ወደ ብሄራዊ ሙዚየም ተዛወረ