Category Archives: Opposition politics

መንግስትን ከማረም ለመንግስት ጥብቅና የሚቆም የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርት

የኢትዮጲያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት “ከሰኔ 2008 ዓ.ም እስከ መስከረም 2009 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ በነበሩት ወራት በኦሮሚያ፣ አማራና በደቡብ ብሔር ብሄረሰቦች እና ሕዝቦች ክልሎች ተፈጥረዋል ባላቸው ሁከትና ብጥብጥ 669 ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል፣ 1018 ሰዎች ላይ የተለያዩ የአካል ጉዳቶች ደርሶባቸዋል፣ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል” ብሏል። እስኪ ከላይ የቀረበውን ሪፖርት … Continue reading መንግስትን ከማረም ለመንግስት ጥብቅና የሚቆም የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርት

መንግስትን በእጅጉ የፈተነዉ ቀዉስና የተስተናገደበት አግባብ ሲፈተሽ

(አስጨናቂ ገ/ጻዲቅ ሺፈራዉ (ኮ/ል)) መግቢያ በሀገራችን ከጥቂት ወራት በፊት ተከስቶ ለነበረዉ ሁከት ዋነኛ መነሻ ምክንያት ህዝባዊ ቅሬታዎችን በአግባቡ ማስተናገድ አለመቻላችን እንደደሆነ ይታወቃል፡፡ የህዝቡን ብሶት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ህዝባዊ ቅሬታዉን ወደ አጠቃላይ ቀዉስ በመቀየር ረገድ ጸረ -ሰላም ኃይሎች የተጫወቱት አፍራሽ ሚና ክፍተኛ እንደነበርም የሚዘነጋ አይደለም፡፡ ተቃዉሞን በሰላማዊ መንገድ ማሰማት የዜጎች መብት ሆኖ እያለ መንግስት ይህን … Continue reading መንግስትን በእጅጉ የፈተነዉ ቀዉስና የተስተናገደበት አግባብ ሲፈተሽ

የኢህአዴግ ተሃድሶ መጀመሪያና መጨረሻ

በጦላይ የተሃድሶ ሥልጠና ማጠናቀቂያ ፕሮግራም ላይ በአካል ተገኝተው የነበሩት ጠ/ሚ ኃይለማሪያም ደሳለኝ እንዲህ ሲሉ ተናግረው ነበር፤ “እናንተ በዚህ የተሃድሶ ስልጠና ‘ታድሳችኋል’! አሁን የቀረው ደግሞ የመንግስት ተሃድሶ ነው። እኛም እንደ እናንተ ጥልቅ የሆነ ተሃድሶ ለማድረግ ተዘጋጅተናል!” አንዱ ከበስተኋላዬ አንዲህ ሲል ሰማሁት “ኧረ በለው…ምድረ ባለስልጣን እንደ እኛ በጦላይ ፍዳውን ሊቀምስ ነው!?” እንደው ግን ለመሆኑ ይኼ “ተሃድሶ” የሚባለው … Continue reading የኢህአዴግ ተሃድሶ መጀመሪያና መጨረሻ

ኢሕአዴግ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆኑን ገለጸ

(የኢትዮጲያ ዜና አገልግሎት – ኢዜአ) የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) በአገር ውስጥ ዕውቅና ካገኙ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ለመከራከርና ለመደራደር ዝግጁ መሆኑን ገለጸ። ድርጅቱ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር የሚያደርገው ክርክርና ድርድር በቀጣዩ ሣምንት መካሄድ ይጀምራል። የኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የድርጅቱ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ድርጅቱ እንደ ገዢ ፓርቲ በጋራ ከመስራት አኳያ … Continue reading ኢሕአዴግ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆኑን ገለጸ

አገራችን ኢትዮጵያ ያጠላባት አደጋና ስለ መውጫዋ አቅጣጫዎች

(በላይ ደርሸም) አጠቃላይ አገራችን ኢትዮጵያ ግዙፍ ፈተና ተደቅኖባታል፤ ዜጎችዋ ግዙፍ ፈተና ተደቅኖብናል፡፡ ከዚህ ፈተና ልንወጣ የምንችለው በራሳችን ጥረትና ብልህነት ብቻ ነው፡፡ እንባችንን ልናደርቅ የምንችለው እርስ በርሳችን ተመካክረን በምንደርስበት አግባቢ መንገድ ብቻ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ሁሉም በየራሱ ጉዳይ ተጠምዷል ወይም ቅድምያ የሚሰጣቸው ብሄራዊ ጥቅሞች አሉት፡፡ አጋር የሚባሉት ከጎናችን ይቆማሉ ወይም መፍትሄ እንዲመጣ ያደርጋሉ በሚል ተስፋና ስሌት … Continue reading አገራችን ኢትዮጵያ ያጠላባት አደጋና ስለ መውጫዋ አቅጣጫዎች

ለሀገሪቱም ለኢህአዴግም የሚበጀዉ ሀገር ወዳድ ምሁራንን ማዳመጡ ነዉ!

(ኮሎኔል አስጨናቂ ገ/ጻዲቅ ሺፈራዉ) መግቢያ በሃገራችን የተከሰተዉን አደገኛ ሁኔታ ስጋት የገባቸዉ ቅን የሆኑ ኢትዮጵያዉያን አገሪቱን ከአደጋ መታደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የበኩላቸዉን ምክረ ሃሳብ እያቀረቡ ባለበት ሰዓት አንዳችም ኃላፊነት የማይሰማቸዉ አንዳንድ ወገኖች ደግሞ አሁን ያለዉ ቀዉስ ተባብሶ  የበለጠ ምስቅልቅል ሁኔታ እንዲፈጠር ሆን ብለዉ መርዘኛ የሆነ ቀስቀሳ ከማድረግ አልተቆጠቡም:: መንግስት በሀገሪቱ የተከሰተዉ ሁኔታ አሳስቦት ራሱን በግልጽ ፈትሾና … Continue reading ለሀገሪቱም ለኢህአዴግም የሚበጀዉ ሀገር ወዳድ ምሁራንን ማዳመጡ ነዉ!

ኢህአዴግ – ከለውጥ እና ከሞት አንዱን ምረጥ

ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማህብረሰብ ሊሰጥ የታቀደው ስልጠና ዛሬ ላይ ተጀምሯል። ለስልጠናዉ ከተዘጋጁ ሰነዶች ውስጥ የመጀመሪያው “የሩብ ምዕተ ዓመታት የልማት፣ ሰላምና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ጉዞ…” የሚል ርዕስ ተሰጥቶታል። በመረሃ-ግብሩ መሰረት ጠዋት ላይ በአሰልጣኞቹ ገለፃ ሲሰጥ እንደተለመደው በአሰልጣኝነት የተመደቡት የመንግስት ኃላፊዎች ለታዳሚው የሚመጥን ስልጣና ለመስጠት የአቅምና ክህሎት ችግር እንዳለባቸው በግልፅ ያስታውቃል። ይህ ግን ላለፉት አስር አመታት የታዘብኩት … Continue reading ኢህአዴግ – ከለውጥ እና ከሞት አንዱን ምረጥ

የጎንደሩ ዓመፅ ለምን ኣሁን ሆነ? ዋና ዋና መነሻ ምክንያቶች

በ”ጥያቄ ኣለኝ ጓዶች”(የብዕር ስም) በቅርብ ግዝያቶች በተለያዩ አከባቢዎች መልካቸዉና ይዘታቸው የተለያየ ዓመፆች እየታዩ ነው፤ ለግዜው ግን ትኩረቴ የጎንደሩ ላይ ነው። በጎንደርና ኣካባቢው የተነሳው ላይ ያተኮርኩበት ምክንያት ጎንደር የዚህ ሁሉ ማእከል ስለነበረችና ሌሎቹ በዋናነት የዚህ ተቀጥያ ስለነበር ምንጩን መረዳት ሌላዉን መረዳት ያስችላል ከሚል እሳቤ ተነስቼ ነው። ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ከሌሎች ለየት ባለ መልኩ ዘር ተኮር ጥቃቶች … Continue reading የጎንደሩ ዓመፅ ለምን ኣሁን ሆነ? ዋና ዋና መነሻ ምክንያቶች

ከኢህአዴግ እና ከፌስቡክ ማን ያሸንፋል?

የገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ አመራሮችና ደጋፊዎች፤ “ከኢህአዴግ በስተቀር ኢትዮጲያን ለመምራት የሚያስችል አቅም ያለው ፓርቲ የለም”፣ እንዲሁም “በፌስቡክ (Facebook) የመንግስት ስልጣን መያዝ አይቻልም” የሚሉ አስተያየቶችን በተደጋጋሚ ሲሰጡ ይሰማል። ለምሳሌ፣ “ኢትዮጲያ የማን ናት፡ የወጣቶች ወይስ የባለስልጣናት” በሚል ርዕስ ባወጣሁት ፅሁፍ ላይ ከተሰጡ አስተያየቶች አንዱ እንዲህ ይላል፤ “Except EPRDF nobody is qualified to lead Ethiopia at this time. So … Continue reading ከኢህአዴግ እና ከፌስቡክ ማን ያሸንፋል?

የሀብታሙ አያሌው ጉዳይ፡- “ፈጣን ውሳኔ ባለመሰጠቱ የመዳን ተስፋው እየጨለመ ይገኛል”

(ማይክ መላከ) የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል አቶ ሀብታሙ አያሌው ከሃኪም ቤት ከወጣ እነሆ ዛሬ 12ኛ ቀኑ ነው። በካዲስኮ ሆስፒታል አስቸኳይ የህክምና እርዳታ ቢያገኘም ህመሙን ከማስታገስ በስተቀር ማዳን አልተቻለም። ብዙዎቻችን ኪንታሮት የተለመደና በቀላሉ የሚድን በሽታ መሆኑን እናውቃለን። ነገር ግን፣ የኪንታሮት ብሽታ አራት ደረጃዎች ያሉት ሲሆን፣ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ያሉት በቀላሉ ግን በሀገር ውስጥ ህክምና የሚድኑ ናቸው። … Continue reading የሀብታሙ አያሌው ጉዳይ፡- “ፈጣን ውሳኔ ባለመሰጠቱ የመዳን ተስፋው እየጨለመ ይገኛል”