Category Archives: News

ኢሕአዴግ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆኑን ገለጸ

(የኢትዮጲያ ዜና አገልግሎት – ኢዜአ) የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) በአገር ውስጥ ዕውቅና ካገኙ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ለመከራከርና ለመደራደር ዝግጁ መሆኑን ገለጸ። ድርጅቱ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር የሚያደርገው ክርክርና ድርድር በቀጣዩ ሣምንት መካሄድ ይጀምራል። የኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የድርጅቱ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ድርጅቱ እንደ ገዢ ፓርቲ በጋራ ከመስራት አኳያ … Continue reading ኢሕአዴግ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆኑን ገለጸ

የኢትዮጵያ ልማት በዓለም አቀፍ ሚዲያ

(ስንታየሁ ግርማ) “የኢቫንካ ትራምፕ ጫማዎች ከቻይና ሥሪት ወደ ኢትዮጵያ ሥሪት እየተቀየሩ ነው ” – ኳርትዝ የተባለ ድረ-ገፅ፡፡ ኢቫንካ ትራምፕ የአሜሪካው ዕጩ ፕሬዚዳንት ተወዳዳሪ የዶናልድ ትራምፕ ልጅ ናት፡፡ ኢቫንካ በቻይና የተሠሩ ጫማዎች መሸጫ መደብር አሏት፡፡ ይሁንና የኢቫንካ ጫማ አቅራቢ ድርጅት የሆነው የቻይናው ሁጃን ፋብሪካ በዚህ ሣምንት ፋብሪካው መሠረቱን ከቻይና ጉልበት ርካሽ ወደ ሆነበት ኢትዮጵያ ለማድረግ መወሰኑን የፋብሪካው … Continue reading የኢትዮጵያ ልማት በዓለም አቀፍ ሚዲያ

ም/ጠ/ሚ ደብረጺዮን – የብሔር የበላይነት ስለሚባለውና በጎንደር ስለተከሰተው መፈናቀል [Video]

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የኢኮኖሚና ፋይናንስ ክላስተር አስተባባሪ ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ባለፈው አርብ ነሐሴ 27/2008 ለኦንላይን ሚዲያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በጋዜጣዊ መግለጫው ከዳሰሷቸው በርካታ ጉዳዮች መሀል፡- * በጎንደር መተማ-ዮሐንስ አካባቢ ስለተከሰተው መፈናቀል እና ስለአካባቢው ፀጥታ * ‹‹የአንድ ብሔር የበላይነት›› የሚባለውን አስመልከቶ የሰጡትን ማብራሪያዎች ቪዲዮ እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡ (ለድምጽ ጥራት ችግር ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡) —— Watch the video *************

ከኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ

ከኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ ነሐሴ 16/2008 የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከነሃሴ 10-15/2008 ዓ.ም ድረስ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ያለፉትን አስራ አምስት ዓመታት የለውጥ ጉዞ በመገምገም በአንድ በኩል በእስካሁኑ ትግል የተመዘገቡ ውጤቶችን አጠናክሮ ለመቀጠል፣ በሌላ በኩል ደግሞ ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱን የሚፈታተኑ ችግሮችን በመቅረፍ የህዝብ መብትና ተጠቃሚነትን ለማጎልበት የሚያስችሉ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በድርጅቱ … Continue reading ከኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ

Video | የመንግሥት ቃለ-አቀባይ ጋዜጣዊ መግለጫ

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ:- ከኤርትራ ጋር ስለነበረው ግጭት፣ ከአልሸባብ ጋር ስለነበረው ውጊያ፣ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ፕሮግራም እንደገና ስለመራዘሙ፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ስለኦሮሚያና ቅማንት ስላቀረበው ሪፖርት እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፡፡ ቪድዮውን ይመልከቱ፡፡ ***************

የአማራ ክልል መንግሥት የቅማንት ብሔረሰብንና የክልሉ ሕዝብን ይቅርታ እንዲጠይቅ ተወሰነ

(ዮሐንስ አንበርብር – ሪፖርተር ጋዜጣ) በኦሮሚያ ክልል ብጥብጥ የፀጥታ ኃይሎች ተመጣጣኝ ኃይል ተጠቅመዋል ተባለ ከፍተኛ ኃይል የተጠቀሙ የአማራ ክልል ልዩ ፖሊስ አባላት በሕግ እንዲጠየቁ ተወሰነ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በኦሮሚያ በርካታ ቦታዎች ተፈጥሮ የነበረውን ግጭትና ሁከት በራሱ አነሳሽነት እንዲሁም በአማራ ክልል በሰሜን ጐንደር ከቅማንት የማንነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ የቀረበለትን አቤቱታ መሠረት በማድረግ ያካሄደው የሰብዓዊ መብት … Continue reading የአማራ ክልል መንግሥት የቅማንት ብሔረሰብንና የክልሉ ሕዝብን ይቅርታ እንዲጠይቅ ተወሰነ

መግለጫ፡- “የፖትሪያርክ ጽ/ቤት ጋዜጠኞችን በማሳደድ ወደር አልተገኘለትም”

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፖትሪያርክ ጽ/ቤት ጋዜጠኞችን በማሳደድ ወደር አልተገኘለትም። መንግስት በጋዜጠኞች ላይ ማሳደዱንና ክስ መመስረቱን እያቋረጠ በሚገኝበት በዚህ ወቅት የቤተ ክርስቲያኒቷ አመራሮች ራሳቸውን ከሀገሪቱ ህግ የበላይ በማድረግ ማስተባበያ እና ምላሽ ለጋዜጠኞች ከመስጠት ይልቅ ምንም የህግ ጥሰት ያልፈጸመውን የሰንደቅ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ፍሬው አበበን ከሰው በማንገላታት ላይ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የጋዜጠኞች ህብረት ሪፖርት ተደርጎለታል። … Continue reading መግለጫ፡- “የፖትሪያርክ ጽ/ቤት ጋዜጠኞችን በማሳደድ ወደር አልተገኘለትም”

የኦሮሚያ ተቃውሞና ትምህርት፡ “መስከረም 3 እንገናኝ!”

የ17 ዓመት ገደማ ወጣት ነው። በወሊሶ ከተማ የገረሱ-ዱኪ የመሰናዶ ት/ት ቤት የ11ኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን ትክክለኛ ስሙን አላውቅም። ስም መያዝ ስለማይሆንልኝ ሁሌ “ቀዮ!” እያልኩ እጠራዋለሁ። እስከ የትምህርት ሰዓት ድረስ ሱቅ ውስጥ ይሰራል። የትምህርት ሰዓት ሲደርስ ታናሽ ወንድሙ ይተካውና እሱ ወደ ትምህርት ቤት ይሄዳል። ቀዮ ቀልጣፋና ጠንቃቃ ልጅ ነው። ትምህርቱ ላይም ጎበዝ እንደሆነ ታናሽ ወንድሙ ሲያወራ … Continue reading የኦሮሚያ ተቃውሞና ትምህርት፡ “መስከረም 3 እንገናኝ!”

ጦርነት የአቅም ማነስ ምልክት ነው

የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ተወልደ ሙልጌታ፣ የካቲት 18/2008 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ “የኢትዮጲያ መንግስት በታገቱት 80 ኢትዮጲያዊያን ምክንያት በኤርትራ ላይ ተመጣጣኝ ዕርምጃ እንደሚወስድ” ተናግረዋል። መግለጫውን ተከትሎ ከጋዜጠኞች፤ ታጋቾቹ ስለተያዙበት ሁኔታ፣ ማንነት እና መንግስት ሊወስደው ስላሰበው አፀፋዊ እርምጃ ዙሪያ ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት ምላሽ ግን በጣም የሚገርም ነው፦”ከዚህ በላይ ምንም ዝርዝር ማብራሪያ ልሰጥ አልችልም”። በእርግጥ ቃለ … Continue reading ጦርነት የአቅም ማነስ ምልክት ነው

ለሕገ መንግሥቱ ታማኝ አይደሉም የተባሉት ዳኛ ከኃላፊነታቸው ተነሱ

(ዮሐንስ አንበርብር – ሪፖርተር ጋዜጣ) ከ2006 ዓ.ም. ጀምሮ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዳኝነት ሲያገለግሉ የቆዩት ዳኛ ግዛቸው ምትኩ ለሕገ መንግሥቱ ታማኝ ሆነው አልተገኙም በሚል ምክንያት በፓርላማው ከኃላፊነታቸው ተነሱ፡፡ ፓርላማው ዳኛውን ከሹመታቸው ያነሳው፣ ጥር 28 ቀን 2008 ዓ.ም. የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ዳኛው ፈጽመውታል ያለውን የዲሲፕሊን ስህተት አዳምጦ ከተወያየ በኋላ ነው፡፡ በዳኛ ግዛቸው ላይ የቀረቡ የዲሲፕሊን … Continue reading ለሕገ መንግሥቱ ታማኝ አይደሉም የተባሉት ዳኛ ከኃላፊነታቸው ተነሱ