Category Archives: Human Rights

ሰማያዊ ፓርቲ| አማራ ብሔር አይደለም፣ ለኦሮምኛ የግእዝ ፊደል ይሻላል

የ‹‹ሰማያዊ›› ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ከላይፍ መጽሔት ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ መጽሔቱ እንደሚከተለው አቅርቦታል፡፡ (ከላይ ያለው ርዕስ የኛ ነው) *********** ላይፍ ፡- ለፖለቲካ ስራ ሙሉ ጊዜን መስጠት በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ አስቸጋሪ አይሆንም? ኢንጅነር፡- መኖር ስላለብኝ ጥቂት ስራ እሰራለሁ፣ የሚበዛውን ጊዜዬን ግን የማሳልፈው ለፓርቲው ስራ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ነገሮች ለምርጫ አስቸጋሪ ሲሆኑ የምትወስደው ውሳኔ አንዱን በማጠፍ ለአንደኛው … Continue reading ሰማያዊ ፓርቲ| አማራ ብሔር አይደለም፣ ለኦሮምኛ የግእዝ ፊደል ይሻላል

ልማታዊ መንግስት ፓርቲዎችን አዳክሞ “ተወዳዳሪ ጠፋ” ማለት ልማዱ ነው

(ሙሼ ሰሙ – የኢዴፓ ፕሬዚደንት) “ምርጫዎች ቀን ቆጥረው ይመጣሉ፤ ውጤቱን እንዲለውጡ ግን አንፈልግም” ሶሻሊስቶች ለህዝብ ጥቅም በሚል ሰበብ በሥልጣን ላይ ለመቆየት የሚሹት በዲሞክራሲያዊ መንገድ አይደለም፡፡ በዚህም ሳቢያ ፍትሃዊ ምርጫ ማድረግ አይዋጥላቸውም፡፡ ተፈጥሯዊ ባህርያቸውም አይደለም፡፡ የእነሱ ዝነኛ ብሂል “የትም ፍጪው [ስልጣኑን] አምጭው” የሚል ነው፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ በአገራችን በሚካሄዱ ምርጫዎች፣ ምርጫ ቦርድና አስፈጻሚዎቹ ለምርጫ ሕጎችና አሰራሮች … Continue reading ልማታዊ መንግስት ፓርቲዎችን አዳክሞ “ተወዳዳሪ ጠፋ” ማለት ልማዱ ነው

የቤንሻንጉል ተፈናቃዮች እንዲመለሱ ተወሰነ | Sendek

(በዘሪሁን ሙሉጌታ) ባለፉት ሁለት ሳምንታት በሺህ የሚቆጠሩ የአማራ ክልል ተወላጆች ከቤንሻንጉል ክልል ተፈናቅለው በጎጃም ፍኖተሰላም አካባቢ እንዲሰፍሩ የተደረገው በስህተት መሆኑን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ገለፁ። የተፈናቀሉት በሙሉ ቀደም ሲል ወደነበሩበት እንዲመለሱ መወሰኑንም አስታወቁ። የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አህመድ ናስር በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት ሰሞኑን ከክልሉ እንዲፈናቀሉ የተደረጉ የአማራ ተወላጆች በሙሉ እንዲመለሱ መወሰኑን ገልፀዋል። … Continue reading የቤንሻንጉል ተፈናቃዮች እንዲመለሱ ተወሰነ | Sendek

የቤንሻንጉል ተፈናቃዮች ተመፅዋች ሆኑ | Addis Admass

“ከእነ ቤተሠቤ እዚህ ለመድረስ ያየሁትን ፈተና ፈጣሪ ያውቀዋል፡፡ ቤተሰቤ ከቁጥር ሳይጐድል ለአገሬ መሬት በቅቻለሁና ከእንግዲህ የፈለገው ይሁን” አሉኝ፤ ከቤኒሻንጉል ክልል ያሶ ወረዳ ተፈናቅለው በፍኖተ ሰላም ድንጋያማ መጠለያ ውስጥ ያገኘኋቸው አዛውንት፡፡ በአማራ ክልል የከሠላ ወረዳ ተወላጅ የኾኑት አዛውንት፤ ኑሮ አልቃና ቢላቸው በ1997 ዓ.ም ሦስት ልጆቻቸውን ከትዳር አጋራቸው ጋር ይዘው፣የትውልድ ቀያቸውን ለቀው የተሻለ ሥራ ይገኝበታል ወደ ተባሉበት … Continue reading የቤንሻንጉል ተፈናቃዮች ተመፅዋች ሆኑ | Addis Admass

የቤንሻንጉል ፕ/ት: ተፈናቃዮቹ ኦሮሞዎችም ናቸው – አጣርተን እርምጃ እንወስዳለን

ባለፈው ሳምንት አዲስ አድማስ ጋዜጣ የዘገበውና (እዚህ ብሎግ ላይም የወጣ) ዜና፤ በበቤንሻንጉል ክልል የሰፈሩ ዜጐች “ሕገወጥ” ተብለው እንደተባረሩ መዘገቡ ይታወሳል፡፡ ዜናው እንዳለው ከሆነ፡-  “በሚኖሩበት አካባቢ የእርሻ ቦታ በማጣታቸውና የተሻለ ሥራ ፍለጋ ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ ከአማራ ክልል ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያሶ ወረዳ ተዘዋውረው የከተሙ በርካታ ሰዎች በወረዳው ባለሥልጣናትና ፖሊሶች፤ ሰብአዊ መብታቸው ተጥሶ ከቀያቸው መፈናቀላቸውን…ገለፁ፡፡ የያሶ ወረዳ ዋና … Continue reading የቤንሻንጉል ፕ/ት: ተፈናቃዮቹ ኦሮሞዎችም ናቸው – አጣርተን እርምጃ እንወስዳለን

በቤንሻንጉል ክልል የሰፈሩ ዜጐች “ሕገወጥ” በሚል ተባረሩ | Addis Admass

* በከተማው የሠሩትን ቤት መላ እስኪያሲዙና ንብረታቸውን እስኪሰበስቡ ጊዜ እንዲሰጣቸው ቢጠይቁም ‹‹ቤትና ንብረቱ የሚገባው ለወረዳው ነው›› በሚል ወረዳውን ለቀው እንዲወጡ [መገደዳቸው]…. * [የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ] – ወደመጡበት እንዲመለሱ የተደረጉት ሕገወጥ የሆኑት እንጂ በሕጋዊ መንገድ የገቡት እንዳልሆኑ በመግለጽ ሕጋዊ የሚባሉት ከክልላቸው ከወንጀልና ከመንግሥት እዳ ነፃ ስለመሆናቸው…የመሸኛ ደብዳቤ የሚያመጡትን መሆኑን ተናግረዋል፡፡ —— በሚኖሩበት አካባቢ የእርሻ ቦታ በማጣታቸውና የተሻለ … Continue reading በቤንሻንጉል ክልል የሰፈሩ ዜጐች “ሕገወጥ” በሚል ተባረሩ | Addis Admass

መጅሊሱ እንዴት ሰነበተ? (Teshome Kemal)

መጅሊሱ በአዲስ መልክ ከተመረጠ ጥቂት ወራትን አስቆጥሯል፡፡ መጅሊሱ ሕዝበ ሙስሊሙን እንዲያገለግል፣ እንዲያረጋጋ፣ ወደተሻለ አቅጣጫም እንዲመራ፣ በመካከሉ ያሉ አለመግባባቶችን ለመቀነስ ብሎም ለማስወገድ እንዲችል ሙስሊሙ ኅብረተሰብ የልማቱ ግንባር ቀደም ተሰላፊና ተጠቃሚ እንዲሆን አመቺ ሁኔታን እንዲፈጥር ይጠበቃል፡፡ አብዛኛዎቹ አመራሮችም እንሞክረው፣ ኢስላማዊ ኃላፊነታችንን እንወጣ በሚል እንጅ የተሻለ ገቢ ለማስገኘት በሚችል ሥራ ላይ ለመሳተፍ የሚችሉ ናቸው፡፡ ሁሉም የየራሳቸው የሆነ የተረጋጋ … Continue reading መጅሊሱ እንዴት ሰነበተ? (Teshome Kemal)

Sendek | የጁነዲን ሳዶ ባለቤትን ጨምሮ 29 ሰዎች በሽበርተኝነት ተከሰሱ

* የጁነዲን ባለቤት በኦሮምያ ክልል አክራሪነት እንዲስፋፋ አድርገዋል – 1.5 ሚሊዮን ብር ከ27ኛ ተከሳሽ ተቀብለዋል (በዘሪሁን ሙሉጌታ) በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌድሪ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1) (ሀ)(ለ)፣ 38(1) እና የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀፅ 3(1) (2) (4) (6) እና 4 ስር የተመለከተውን ተላልፈዋል ያላቸውን 29 ሰዎችና ሁለት ድርጅቶች ላይ ዐቃቤ ሕግ ክስ መስርቷል። ዐቃቤ ሕግ ክሱን … Continue reading Sendek | የጁነዲን ሳዶ ባለቤትን ጨምሮ 29 ሰዎች በሽበርተኝነት ተከሰሱ

Sendek | አረና፣ ሕወሓት በትግራይ የመንግስት ሰራተኞች ላይ የፖለቲካ ሙስና እየፈፀመ ነው አለ

(በዘሪሁን ሙሉጌታ) የትግራይ ክልል ገዢ ፓርቲ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በትግራይ በሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ላይ የፖለቲካ ሙስና እየፈፀመ ነው ሲል አረና ትግራይ ለዲሞኪራሲና ለሉአላዊነት (አረና) አማረረ። የአረና ትግራይ በሉአላዊነት ፓርቲ (አረና) ለሰንደቅ በላከው መረጃ ህወሓት አቶ መለስ ዜናዊ በጠና ታመዋል እየተባለ በሰፊው መወራት ከጀመረበት የ2004 ዓ.ም የክረምት ወቅት ጀምሮ የትግራይ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ህወሓት … Continue reading Sendek | አረና፣ ሕወሓት በትግራይ የመንግስት ሰራተኞች ላይ የፖለቲካ ሙስና እየፈፀመ ነው አለ

ኢትዮጵያዊቷ በአቡዳቢ በወለደች በ1 ሰዓት ለፍርድ ቀረበች [Amharic]

(በመስከረም አያሌው) በአቡዳቢ በቤት ሰራተኛነት ትተዳደር የነበረችው ኢትዮጵያዊት ሴት ልጇን በተገላገለች አንድ ሰዓት ውስጥ ለፍርድ መቅረቧ እና በእስራት መቀጣቷ ተገልፀ። ሰቨን ደይስ ኢን አቡዳቢ ድረ ገፅ እንደዘገባው፤ ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ ከጋብቻ ውጪ ግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈፅማለች የተባለችው ይህች ኢትዮጵያዊት በወለደች በአንድ ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት የቀረበች ሲሆን ጥፋተኛ ሆና በመገኘቷ ከነ ልጇ እስር ቤት ገብታለች። … Continue reading ኢትዮጵያዊቷ በአቡዳቢ በወለደች በ1 ሰዓት ለፍርድ ቀረበች [Amharic]