Category Archives: History

የወልቃይት የማንነት ጥያቄ – በታሪክና በህገ መንግስቱ

(ዘርአይ ወልደሰንበት) 1. የማንነት ጥያቄ ባሕርይና ስለሚያስገኚው መብት 1.1. የማንነት ጥያቄ ባሕርይ ና ጥያቄውን የማቅረብ መብት 1.2 ስለ ብሄር ማንነት ዕውቅና ውጤት 1.3 ስለብሄር ማህበረሰብ አባልነት 2. የክልሎች ወሰን ለውጥ ጥያቄ 2.1 የክልሎች ወሰን ለውጥ ጥያቄ ባህርይና ጥያቄውን የማቅረብ መብት 2.2 የክልሎች ወሰን ለውጥ ጥያቄ (የድንበር ዉዝግብ) የሚፈታበት መንገድ 2.3 የድንበር ውዝግብ መወስኛ መስፈርት 3.ታሪክ ቀመስ … Continue reading የወልቃይት የማንነት ጥያቄ – በታሪክና በህገ መንግስቱ

ከመወዳደር – አማራጭ ማሳጣት

እኛ እኮ ውድድር አንወድም፣ ፉክክር እንጠላለን! እኛ መወዳደር አያስደስተንም፣ መፎካከር ያስጠላናል። በሁሉም ዘርፍ፤ በፖለቲካ፥ በማህበራዊ ሆነ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴያችን ውድድር አንፈልግም፣ ፉክክር ያስጠላናል። በእርግጥ እኛ ኢትዮጲያዊያን ውድድር የማንወደው መወዳደር ስለማንፈልግ ነው። ተወዳዳሪ የማንወደው ለመወዳደር አቅም ስለሌለን ነው። ፉክክር የምንጠላው ለመፎካከር ብቃት ስለሌለን ነው። በውድድር ብንሳተፍ ከሌሎች ጋር ተፎካካሪ ለመሆን ስለማንችል ነው። በፉክክር ከሌሎች የተሻለ ነገር ለማቅረብ … Continue reading ከመወዳደር – አማራጭ ማሳጣት

ጋምቤላ ክልል እና ብሄራዊ የፀጥታ ስጋት – ኣጭር ቅኝት

በደርግ ዘመነ መንግስት በጆን ጋራንግ የሚመራው የደቡብ ሱዳን ነፃ ኣውጪ (SPLM) በጋምቤላ ክልል ወታደራዊ ካምፖች ነበሩት። ኢህኣደግ ደርግን ላይመለስ ሲገረስስ የSPLM እጣ ፈንታ ኣገር ለቆ መውጣት ወይ ድግሞ ትጥቁን ኣራግፎ ስደተኛ ካምፕ ገብቶ መኖር ነበር። በወቅቱ ሁለቱም ኣማራጮች የሚዋጡለት ስላልነበሩ ከባሮ ወንዝ ወዲያ ያለው የጋምቤላ (የኢትዮጵያ) ግዛት የራሴ ነው በማለት በቁጥጥሩ ስራ ማዋልን መረጠ። ደርግ … Continue reading ጋምቤላ ክልል እና ብሄራዊ የፀጥታ ስጋት – ኣጭር ቅኝት

ዝግመትና መንግስት፡ ነፃነትና ፍጥነት

በእርግጥ አነሳሴ፣ በሀገራችን ያለውን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ተደራሽነትና ሰሞኑን ኢትዮ-ቴሌኮም እየወሰዳቸው ባሉት እርምጃዎች ዙሪያ የዳሰሳ ፅሁፍ ለማቅረብ ነበር። የዓለም የቴሌኮምዩኒኬሽን ማህበር (ITU) በ2015 የፈረንጆች አመት ያወጣውን ሪፖርት በወፍ-በረር እያነበብኩ ነበር። የአለም ሀገራት በዘርፉ ያላቸውን የልማት ደረጃ ከሚያሳው ሰንጠረዥ ውስጥ ኢትዮጲያን ከላይ ወደ ታች እየወረድኩ ብፈልጋት አጣኋት። ፍለጋዬን ከታች ወደ ላይ አድረኩ። 167ኛ፡ ቻድ፣ 166ኛ፡ ኤርትራ፣ 165ኛ፡- … Continue reading ዝግመትና መንግስት፡ ነፃነትና ፍጥነት

ቴዲ አፍሮዎቻችን እና ‘ፍቅሮቻቸው’

ይህን ፅሑፍ ለመፃፍ መንስኤ የሆነኝ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጱያ የታሪክና የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ አንዳንድ የኪነጥበብ ሰዎችና የነሱ ‘ተከታይ’ አድናቂዎቻቸው የሚሰነዝሩት በስሜት የተሞላና በአብዛኛውም ከእዉነታ የራቀ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ሁኔታዎችን (ያሉትም ያለፉትም) አዛብቶ የማቅረብ አባዜ በብዛት በማስተዋሌ ነው፡፡ የዚህ ቁንጮ ተዋናይ ደግሞ ቴዲ አፍሮ ሲሆን በዚህ ፅሑፍ የዚህ ታዋቂ አቀንቃኝ አጠቃላይ ይዘትና እርስ በርሱ የሚጋጭ ፖለቲካዊ ተምኔትና … Continue reading ቴዲ አፍሮዎቻችን እና ‘ፍቅሮቻቸው’

የተገኘዉን ሰላምና እድገት የሚንድ የአመራር ዘይቤ ባስቸዃይ ይታረም!(ሜ/ጄ አበበ ተ/ሃይማኖት)

አበበ ተክለሃይማኖት(“ጆቤ”) (ሜጀር ጄኔራል፣ PhD Candidate) ታላቁ የሰላምና ደህንነት ሙሁሩ ጆሃን ጋልቱንግ ስለ ሰላም እሚከተለዉን ይላል “Peace is a revolutionary idea; peace by peaceful means defines that revolution as nonviolent. That revolution is taking place all the time; our job is to expand it in scope and domain. The tasks are endless; the question is … Continue reading የተገኘዉን ሰላምና እድገት የሚንድ የአመራር ዘይቤ ባስቸዃይ ይታረም!(ሜ/ጄ አበበ ተ/ሃይማኖት)

ሀገር ማለት ነፃነት ነው!

ድሮ – ድሮ “ሀገር ማለት መሬት ነው” ይባል ነበር። ቀጠለና “ሀገር ማለት ሰው ነው” የሚለው መጣ። ባለፈው ሳምንት “ሀገር ማለት ትዝታ ነው” የሚል ፅሁፍ በወጣ በማግስቱ “ሀገር ማለት አስተሳሰብ ነው” የሚል ሌላ ፅሁፍ በማህበራዊ ድረገፅ ላይ ተለጥፎ አነበብኩኝ። ነገሩ ገርሞኝ ሌሎች ፅሁፎችን ሳፈላልግ፤ “ሀገር ማለት እናት ናት”፣ “ሀገር ማለት ሕገ-መንግስት ነው”፣ እና አንዳንድ ጭራሽ ግራ … Continue reading ሀገር ማለት ነፃነት ነው!

ጦርነት የአቅም ማነስ ምልክት ነው

የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ተወልደ ሙልጌታ፣ የካቲት 18/2008 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ “የኢትዮጲያ መንግስት በታገቱት 80 ኢትዮጲያዊያን ምክንያት በኤርትራ ላይ ተመጣጣኝ ዕርምጃ እንደሚወስድ” ተናግረዋል። መግለጫውን ተከትሎ ከጋዜጠኞች፤ ታጋቾቹ ስለተያዙበት ሁኔታ፣ ማንነት እና መንግስት ሊወስደው ስላሰበው አፀፋዊ እርምጃ ዙሪያ ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት ምላሽ ግን በጣም የሚገርም ነው፦”ከዚህ በላይ ምንም ዝርዝር ማብራሪያ ልሰጥ አልችልም”። በእርግጥ ቃለ … Continue reading ጦርነት የአቅም ማነስ ምልክት ነው

ልማትና ዴሞክራሲ፡ የመለስ ዜናዊ ፍልስፍና – ክፍል 3

በ ባለፈው ክፍል ሀገራችን ኢትዮጲያ አሁን ካለችበት ዝቅተኛ የእድገት ደረጃ ለመውጣት የምታደርገው ጥረት በዋናነት በማህበራዊ ልማት ላይ የተመሰረተ እንደሆነ አይተናል፡፡ ለዚህም በአብዛኛው የሕብረተሰብ ክፍል ዘንድ ያሉና ለተፋጠነ ልማትና እድገት ምቹ “ያልሆኑ” ማህበራዊ እሴቶችን፣ ልማዶችንና ደንቦችን መቀየር ወይም መለወጥ እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡ ስለዚህ በቀጣይ መታየት ያለበት ነገር፣ “እንደ ኢትዮጲያ ባለ ሀገር ውስጥ፤ የእርስ-በእርስ ጦርነት ለረጅም ግዜ ሲያምሳት በቆየች፣ በድንቁርና ክፉኛ በተጎዳች ሀገር፣ ህዝቡ ድህነትን እንደ ቋሚ ሁኔታ በተቀበለበት፣ እንዲሁም፣ እነዚህን ማህበራዊ እሴቶች ለማዳበር የካፒታል ሆነ የጥሬ-ዕቃ እጥረት ባለበት ሀገር፣ እንዴት ‘ማህበራዊ ልማት ግንባታን ማካሄድ ይቻላል?” የሚለው ነው፡፡ በዚህ ክፍል፣ የቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ በጉዳዩ ላይ የነበራቸውን አቋምና አመለካከት ለመዳሰስ እንሞክራለን፡፡

በመሰረቱ፣ ማህበራዊ ዕሴቶች፣ ልማዶችና ደንቦች እንደ ሁኔታው የሚቀያየሩ እንጂ ቋሚ ውርሶች አይደሉም፡፡ እንደ ጠ/ሚ መለስ አገላለፅ “በሕይወት ውስጥ በሚያጋጥመው የነገሮች መለዋወጥ ምክኒያት ማህበራዊ እሴቶች፣ ልማዶች እና ደንቦች እንደ አዲስ የሚፈጠሩ፣ የሚቀረፁ፣ እንዲሁም በድጋሜ ሊፈጠሩ እና ሊቀረፁ የሚችሉ እንጂ ቋሚና የማይለወጡ የማህብረሰብ ውርሶች አይደሉም፡፡ ነገር ግን፣ በተለያዩ የሕይወት አጋጣሚዎች ምክንያት እንደ አዲስ ሊፈጠሩና ሊቀየሩ የሚችሉ ከሆነ ከድህነትና ረሃብ በላይ አስከፊ የሆነ ነገር ከቶ ምን አለ? ለዘመናት እድገት-አልባ ጉዞ ስንጓዝ፣ በድህነት አረንቋ ውስጥ ስንዳክር…፣ እንዴት ድህነትና ኋላ-ቀርነትን የሚጠየፍ ትውልድ መፍጠር ተሳነን? እንዴት ከድህነትና ኋላ-ቀርነት ለመውጣት የሚያስችሉ ለውጥና መሻሻልን የሚያበረታቱ፣ ለልማትና እድገት ምቹ የሆኑ ማህበራዊ ዕሴቶችን ሳይፈጠሩ ቀሩ?

አቶ መለስ፣ ማህበራዊ ልማትን እንዴት መገንባት እንደሚቻል፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ታይዋን እና ኢጣሊያን እንደ ማሳያ በመውሰድ አብራርተዋል። እንደ እሳቸው አገላለፅ፣ ማህበራዊ ልማትን መገንባት የሚቻለው ሕብረተሰቡን እርስ-በእርስ በማደራጀት እና የጠበቀ የግንኙነት መረብን በመፍጠር፣ በተለያዩ ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በመሳተፍ ለእድገቱ ምቹ የሆኑ ማህበራዊ እሴቶች እንዲፈጠሩና እንዲሰርፁ በማድረግ ነው፡፡ ነገር ግን፣ ታዋቂው ጀርመናዊው ፈላስፋ ፍሬድሪክ ኒቼ (Friedrich Nietzsche) “Thus Spake Zarathustra” በሚለው መፅሃፉ፣ እሴት የሚፈጠረው በመጀመሪያ በግለሰብ ደረጃ እንደሆነ፣ በመጨረሻ ግን ግለሰብ ራሱ የፈጠራ ውጤት እንደሚሆን ይገልፃል፡፡ የሌሎች ሀገራትን ልምድና ተሞክሮ መውሰድ ጠቃሚነቱ ባያጠራጥርም፣ በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን የሚገኘው የአውራ አምባ ማህብረሰብ፣ አቶ መለስ ከጠቀሷቸው ምሳሌዎች በተሻለ ሁኔታ በሀገራችን የሚያስፈልገውን ማህበራዊ ልማት፣ እንዲሁም የፍሬድሪክ ኒቼን የዕሴት አፈጣጠር ሂደት በተግባር የሚያሳይ ነው።

Photo - Zumra Nuru founder of Awra amba community
Photo – Zumra Nuru founder of Awra amba community

የአውራ አምባ ማህብረሰብ ማህበራዊ ዕሴቶች፣ ልማዶችና ደንቦች ለልማትና ዕድገት ምቹ ከመሆናቸው በተጨማሪ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ፍትህና እኩልነትን የሚያረጋግጡ ናቸው። ነገር ግን፣ የማህብረሰቡ የጋራ መገለጫ እሴቶች፣ ልማዶችና ደንቦች ከመሆናቸው በፊት፣ በመጀመሪያ የማህብረሰቡ መስራች የክቡር ዶ/ር ዙምራ ኑሩ የግል እምነት፣ መርህና መመሪያ ነበሩ። በ1972 ዓ.ም እነዚህ የግለሰቡ የሞራልና የዕውቀት ስብዕና ውጤቶች በ19 የአከባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ተቀባይነት በማግኘታቸው የቡድን የጋራ እምነት፣ መርህና መመሪያ ሆኑ። በመቀጠል፣ በሁሉም የማህብረሰቡ አባላት ዘንድ እንዲሰርፁና ተቀባይነት እንዲያገኙ በማድረግ፣ በአሁን ሰዓት ከ400 በላይ የሚሆኑ የማህብረሰቡ አባላት የጋራ መገለጫ ለመሆን በቁ፡፡ የመስራቹ ዶ/ር የዙምራ የግል ስብዕና በአብዛኛው የማህብረሰቡ አባላት ዘንድ ተቀባይነት ካገኘ በኋላ ሌሎች አባላት፣ በተለይ ወጣትና ህፃናት በተጠቀሱት ማህበራዊ ዕሴቶች፣ ልማዶችና ደንቦች ታንፀው የሚያድጉ ይሆናል። በዚህም የግለሰቡ የግል ስብዕና፤ በመጀመሪያ የቡድን፣ ቀጥሎ የማህብረሰብ የጋራ መገለጫ እየሆነ ከሄደ በኋላ፣ ኒቼ እንዳለው፣ በመጨረሻ “ግለሰብ ራሱ የፈጠራ ውጤት እንደሚሆን በግልፅ ያሳያል።

አቶ መለስ ዜናዊ በፅሁፋቸው እንደ ምሳሌ ካነሷቸው አንዱ የደቡብ ኮሪያ የማህበራዊ ልማት ግንባታ ሂደት ነው። በዚህ ረገድ፣ ደቡብ ኮሪያኖች አሁን ለደረሱበት የዕድገት ደረጃ ከፍተኛ አስተዋፆ ያለው የሥራ ባህላቸው እንደሆነ በመጥቀስ ይህንንም ከጃፓን ኢምፔሪያሊዝም አገዛዝ እንደወረሱት ይጠቅሳል። በዚህ ረገድ፣ የአቶ መለስ ዜናዊ ፅሁፍ፣ ለልማትና እድገት ምቹ የሆኑ የማህበራዊ ዕሴቶች፣ ልማዶችና ደንቦች በአስተዳደራዊ መዋቅር እንጂ፣ በግለሰብ ደረጃ፥ በግል የሞራል ስብዕና እና ግንዛቤ ላይ ተመስርተው የሚፈጠሩ እንደሆነ አያሳይም። ከዚህ በተጨማሪ፣ ለብዙ ዘመናት በኢትዮጲያ ውስጥ አስፈላጊውን የማህበራዊ ልማት እንዳይገነባ ማነቆ የሆኑ ችግሮችን ለይቶ ለማውጣት የሚያስችል ጥልቀትና ድፍረት የለውም።

በቀጣዩ ክፍል-4፣ የአውራ አምባ ማህብረሰብን የተግባር ተሞክሮ ከአውሮፓ የህዳሴ ዘመን እንቅስቃሴ እና ከጃፓን ሥልጣኔ ጋር በማቀናጀት በኢትዮጲያ ማህበራዊ ልማት ግንባታ ከየትና እንዴት መጀመር እንዳለበት በከፊል እንመለከታለን።    

ይቀጥላል…
***********

ልማትና ዴሞክራሲ፡ የመለስ ዜናዊ ፍልስፍና – ክፍል 2

በባለፈው ክፍል ለመግለፅ እንደሞከርኩት፣ ለልማትና እድገት ምቹ የሆኑ ማህበራዊ እሴቶች፣ ልማዶች እና ደንቦች ለአንድ ሀገር ብልፅግናና እድገት ወሳኝ የሆኑ ማህበራዊ ካፒታል (Social capital) ናቸው፡፡ እንደ ኢትዮጲያ ያሉ ሀገራት ዘላቂ ልማትና ፈጣን እድገት እንዲያስመዘግቡ በቅድሚያ እነዚህ ማህበራዊ ሃብቶች በሚፈለገው ደረጃ ሊኖሯቸው ይገባል፡፡ ይህ ክፍል በዋናነት በሁለት መሰረታዊ ጥያቄዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡ በቅድሚያ “እንደ ኢትዮጲያ ላሉ … Continue reading ልማትና ዴሞክራሲ፡ የመለስ ዜናዊ ፍልስፍና – ክፍል 2