Category Archives: Grand Ethiopian Renaissance Dam

ተቃዋሚዎችና የህዳሴ ግድብ፡- ቅብብሎሹ ከየት ወዴት ነው?

(By እናት ከመሳለሚያ) ዘንድሮ 22ኛው የግንቦት 20 በዓል የተከበረው የህዳሴ ግድቡ ከደረሰበት የላቀ ደረጃ ጋር በማስተሳሰር ነበር፡፡ የግድቡን ግንባታ ወደ አንድ ደረጃ ከፍ ያደረገው በተወሰነ ኪሎ ሜትር ውስጥ የውሃውን ፍሰት የማስቀየስ ሥራ በእዚሁ የድል በዓል ወቅት መከናወኑ ዕለቱን ልዩ ትርጉም አሰጥቶቷል፡፡ ኢትዮጵያ የግድቡ ግንባታ ሥራ አመቺነትን ለማረጋገጥ ያከናወነችውን ተግባር ተከትሎ የግብፅ መንግሥት እና አንዳንድ የሀገር … Continue reading ተቃዋሚዎችና የህዳሴ ግድብ፡- ቅብብሎሹ ከየት ወዴት ነው?

ታላቁ የህዳሴ ግድብ በቀን 2 ሚ. ዩሮ ገቢ ያስገኛል

(ናፍቆት ዮሴፍ) ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታው ተጠናቆ በሙሉ አቅሙ ስራ ሲጀምር ለመቶ አመታት በየቀኑ 2 ሚሊዮን ዩሮ ከኤሌክትሪክ ሽያጭ እንደሚያስገባ ተገለፀ፡፡ ገቢው የኢትዮጵያዊያንን ህይወትና ኢኮኖሚ መልክ ይቀይራልም ተብሏል፡፡ ትላንት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ላይ ማንዴላ የስብሰባ አዳራሽ በተካሄደው ሲምፖዚየም ላይ በቀረበው ጥናት፤ ግድቡ በየቀኑ የተጠቀሰውን ያህል ገቢ ከማስገኘቱም በላይ በጎርፍ አደጋ የሚጠቁትን እነ ሱዳንን ከጎርፍ … Continue reading ታላቁ የህዳሴ ግድብ በቀን 2 ሚ. ዩሮ ገቢ ያስገኛል

ኢህአዴግ:- መድረክና አንድነት መቼም ከግድቡ ጎን አይቆሙም

Highlights: * መድረክ ዘንድሮም እንደተለመደው የነገሮችን አወዳደቅ ካየ በኋላ ባወጣው መግለጫ ከዚህ በፊት አላምንበትም ያለውን ግድብ ግንባታ ለማሳካት ከኢህአዴግ ጋር መደራደር አለብኝ፤ ከግብፅ ወገን የሚመጣ ስጋትን ለመመከት ከኔ ጋር መደራደር የግድ ነው ብሎ ተነስቷል፡፡ * የአገራችን ህዝቦች ግድቡን የማንንም እጅ ሳያዩ ለመገንባት ቆርጠው እንደተነሱ ሁሉ ለግድቡ ግንባታ በኩርፍያ ጥግ ይዘው የቆሙ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ይሁንታ ማግኘትም አያስፈልጋቸውም፡፡ … Continue reading ኢህአዴግ:- መድረክና አንድነት መቼም ከግድቡ ጎን አይቆሙም

ስለሕዳሴ ግድብ፡- የ‹አንድነት› ፓርቲ መግለጫ [ሙሉ ቃል]

ባለፈው ዓርብ ‹አንድነት› ፓርቲ ስለሕዳሴ ግድብ የሰጠውን መግለጫ አስመልክቶ ኢቲቪ ያተመውን ዜና እዚህ ብሎግ ላይ ደግመን ማተማችን ይታወሳል፡፡ የፓርቲውን ሙሉ መግለጫ ዛሬ ያገኘን ሲሆን፣- ከኢቲቪ በወሰድነው ዜና ላይ ከቀረበው ጋር ትርጉም ያለው ልዩነት ባይኖረውም የ‹አንድነት› ፓርቲ ደጋፊ የሆኑ አንባቢዎቻችን ባቀረቡት ቅሬታ ምክንያት የመግለጫውን ሙሉ ቃል አትመነዋል፡፡ ለቀጣይ ግን እኛን ከመተቸት ይልቅ ፓርቲያቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ሲጠራ … Continue reading ስለሕዳሴ ግድብ፡- የ‹አንድነት› ፓርቲ መግለጫ [ሙሉ ቃል]

ኢሕአፓ፡- መንግሥት በህዳሴ ግድብ ሰበብ ‘ግብጽን እየተነኮሰ’ ነው

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሰኔ 4 ቀን 2005 ዓ.ም. የወያኔ አገዛዝ ሕዝብን ለጦርነት፤ ሀገርን ለጥቃት እያዘጋጀ ነው የወያኔ አገዛዝ የሕዝብን ትኩረት መደረግ ካለበት ወሳኝ ትግል ለመነጠል ሲያደርገው የነበረውን ሁሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ዛሬ በተመክሮ የተገነዘበው ነው። በቅርቡ ደግሞ ህዳሴ ግድብ በሚለው ማታለያ የለመደባቸውን ተላላዎች በዙሪያው እያሰለፈና ሕዝብንም እየዘረፈ ያለው አልበቃ ብሎት ግብጽን እየተነኮስና እየቀሰቀስ በመቀጠሉ … Continue reading ኢሕአፓ፡- መንግሥት በህዳሴ ግድብ ሰበብ ‘ግብጽን እየተነኮሰ’ ነው

ሰማያዊ ፓርቲ:- ግድቡ ‘ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የሚደለቅ ከበሮ’ ነው

በመሠረቱ በአባይ ወንዝ ላይ የተጀመረው ግድብ ከሐገራዊ ጠቀሜታው ይልቅ የገዥውን ፓርቲ የስልጣን እድሜ ለማራዘም የታለመና ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የሚደለቅ ከበሮ መሆኑን ፓርቲያችን ይገነዘባል፡፡ የግድቡ ሥራ የገዥውን ፓርቲ የተለየ አሣቢነትና ተቆርቋሪነት የሚያሳይ አድርጎ ለማቅረብ የሚደረገው ልፈፋ ከተራ ጩኸት በዘለለ የዜጎችን ልብ የሚያማልል አይደለም፡፡

‘አንድነት’ ፓርቲ፡- የሕዳሴ ግድብ ባለቤት አልተለየም (+video)

(ከበደ ካሳ) አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የኢትዮጵያ መንግስት የአባይን ጉዳይ የፖለቲካ መጠቀሚያ ማድረጉን እንዲያቆም አሳሰበ፡፡ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) “ሁሉንም ነገር ለፖለቲካ ፍጆታ ለማዋል የቆረጠ ፓርቲ የሀገርን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ መጣሉ የማይቀር ነው” በሚል ርዕስ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች እንደገለፁት አባይ ከመገደቡ በፊት መፈፀም የሚገባው የዲፕሎማሲ ስራዎች አልተሰሩም፡፡ “በአባይ … Continue reading ‘አንድነት’ ፓርቲ፡- የሕዳሴ ግድብ ባለቤት አልተለየም (+video)

መንግስት፡- “የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናክሮ ይቀጥላል”

* በግብፅም ሆነ በሌላ ማንኛውም ወገን የሚቀርብ የግድቡን ግንባታ የማዘግየት ወይንም ከነአካቴው የማቋረጥ ነገር ፈፅሞ ተቀባይነት የለውም * በሕዳሴው ግድብ ሽፋን የውስጥ ችግርን ለማቃለል የሚደረገው ጥረትም የግብፅን ዘላቂ ጥቅም አይጠብቅም — የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር “የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናክሮ ይቀጥላል” በሚል ርዕስ … Continue reading መንግስት፡- “የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናክሮ ይቀጥላል”

Brief | የፕ/ር መስፍን የ‹አባይ ጦርነት› ግልብ ትንተናና ምክር

(Daniel Berhane) ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም ባለፈው እሮብ ከአባይ ጉዳይ በተያያዘ የጦርነት ቅስቀሳን ለመገሰጽና የግብጽን የጦር ሀያልነት ‹ለማሳወቅ› አንድ ጽሑፍ አስነብበውናል፡፡ ጽሑፉ በጥድፊያ እና/ወይም እንደተለመደው የኢሕአዴግን ባለስልጣኖች ለማብሸቅ ተብሎ የቀረበ ስለመሰለኝ አላተኮርኩበትም ነበር፡፡ ነገር ግን እሳቸው የጽሑፋቸውን ግልብነት (shallowness) አስተውለው – ጠለቅ ያለ ማብራሪያ በመስጠት ለማጠናከር ወይም ለማስተባበል ይሞክራሉ ብዬ ስጠብቅ፣ ትችት የሰነዘሩባቸውን ሰዎች በመሀይምነት መፈረጅ ነው የመረጡት፡፡ ሰለሆነም እንደው ምናልባት … Continue reading Brief | የፕ/ር መስፍን የ‹አባይ ጦርነት› ግልብ ትንተናና ምክር

የውጭ ጉዳይ ሚ/ር የግብጽን አምባሳደር ጠርቶ ማብራሪያ ጠየቀ

ኢትዮጵያ በመከባበርና በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ እንደምታራምድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ ኢትዮጵያ ከጎረቤት እና ከሌሎችም አገሮች ጋር በመከባበርና በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ፖሊሲ በጽናት ስታራምድ መቆየቷ ሚኒስቴር መስርያ ቤቱ አስታውቋል፡፡ በመሆኑም በህዳሴ ግድብ ዙሪያ በግብጽ ዘንድ ሰፍኖ የቆየውን ጥርጣሬ ለማስወገድ ግድቡ ግብጽንም ሆነ ማንኛውንም የታችኛውን ተፋሰስ አገር እንዳይጎዳ የሚያረጋግጥ የግብጽ፣ የሱዳን፣ የኢትዮጵያ … Continue reading የውጭ ጉዳይ ሚ/ር የግብጽን አምባሳደር ጠርቶ ማብራሪያ ጠየቀ