Category Archives: Country

ከኢትዮጵያዬ ወደ ኢትዮጵያችን

(ቴዎድሮስ ደረጄ (ዘበደሌ) ጠቅለል አድርጎ “የኢትዮጵያውያን እይታ” እያሉ ማተቱ ትንሽ ከባድ ቢሆንም ጎልተው በሚወጡ ነገራት ላይ ተነስቼ እይታዬን አቀርባለሁ ። በታሪክ ድርሳናት ኢትዮጵያ በውል መቼና እንዴት ተመሰረተች? ስሟስ እንዴት ኢትዮጵያ ተባለ? በሚለው ስምምነት ላይ ያልተደረሰ ቢሆንም እያንዳንዱ ኢትዮጵያ ከተመቸው የታሪክ ክምር እያፈሰ ኢትዮጵያዬ የሚለውን እየሳለ እዚህ ደርሷል። ይህ ኢትዮጵያችን ወደሚለው ከፍ ይል ዘንድ ግዜ እሚጠይቅ … Continue reading ከኢትዮጵያዬ ወደ ኢትዮጵያችን

ብሔራዊ ተዋጽኦን በመጠበቅ የሕዝቦች አምሳያ የሆነ ህብረ ብሔራዊ የመከላከያ ሰራዊት የመገንባት ጥረታችን

(ኮ/ል አስጨናቂ ገ/ፃድቅ) “የሀገሪቱ መከላከያ ሰራዊት የብሄሮች ፤የብሄረሴቦች እና የሕዝቦችን ሚዛናዊ ተዋጽኦ ያካተተ ይሆናል“- የኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 87 የመከላከያ መርሆዎች ተ.ቁ.1 መነሻ ጥያቄዎች የኢፌዲሪ መንግስት የሀገሪቱ መከላከያ ሰራዊት ተዋጽኦን የጠበቀ መሆን እንደሚገባዉ በህገመንግስቱ የተቀመጠዉን ደንጋጌ እንዴት ነዉ የተረዳዉና በተግባርም እየተገበረ ያለዉ? መከላከያ ሰራዊቱ በአዋጅ በይፋ ከተቋቋመ በኋላ ባሉት ሁለት አሰርተ ዓመታት ዉስጥ ተዋጽኦን በሚጠበቀዉ … Continue reading ብሔራዊ ተዋጽኦን በመጠበቅ የሕዝቦች አምሳያ የሆነ ህብረ ብሔራዊ የመከላከያ ሰራዊት የመገንባት ጥረታችን

ስኬታማው የኢትዮጵያ ፕብሊክ ዲፕሎማሲ እና እያደገ የመጣው ተሰሚነት

(ስንታየሁ ግርማ) አዲሱ ዲፕሎማሲ ከሴፕተምበር 9/11 በኋላ በስፋት ተቀባይነት እያገኘ እንደመጣ አንዳንድ ምሁራን ያስረዳሉ፡፡ ለአዲሱ ዲፕሎማሲ መጠናከር ዋነኛ ምክንያቶች ተብለው የሚጠሩት ግሎባላይዜሽን (ሉላዊነት) እየተስፋፋ መምጣቱ እና ዓለም በኢንፎርሜሽን ኔትወርክ በጥብቅ መቆራኘት በዋነኝነት ይጠቀሳሉ፡፡ አዲሱ ዲፕሎማሲ ከመንግስት ለመንግስት ብቻ ያተኮር የነበረው “አሮጌውን ዲፕሎማሲ” በህዝብ ዲፕሎማሲ እንደተካው የሚያምኑ ብዙ ናቸው፡፡ አሁን ባለንበት ዘመን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ዓላማዎችንና … Continue reading ስኬታማው የኢትዮጵያ ፕብሊክ ዲፕሎማሲ እና እያደገ የመጣው ተሰሚነት

መንግስትን ከማረም ለመንግስት ጥብቅና የሚቆም የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርት

የኢትዮጲያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት “ከሰኔ 2008 ዓ.ም እስከ መስከረም 2009 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ በነበሩት ወራት በኦሮሚያ፣ አማራና በደቡብ ብሔር ብሄረሰቦች እና ሕዝቦች ክልሎች ተፈጥረዋል ባላቸው ሁከትና ብጥብጥ 669 ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል፣ 1018 ሰዎች ላይ የተለያዩ የአካል ጉዳቶች ደርሶባቸዋል፣ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል” ብሏል። እስኪ ከላይ የቀረበውን ሪፖርት … Continue reading መንግስትን ከማረም ለመንግስት ጥብቅና የሚቆም የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርት

አስገደ እና የትግራይ ህዝብ ትግል ምን አገናኛቸው?

(ብሓቂ ተኸስተ (ሳዕሲዕ) አቶ አስገደ ከህወሓት ነባር ታጋዮች አንዱ ነበር። በሂደቱ መሳተፉ የሚቆጨው ቢሆንም በአኩሪ የትግል ሂደትም የራሱን ድርሻ የተወጣ ታጋይ ነበር። ትግሉ ለድል ከበቃ በኃላም ዓረናን ተቀላቅሎ በትግራይ የተፎካካሪ ፓርቲ በመሆን የራሱን ድርሻ ሲወጣ ነበር። ወደ መሃል ሀገርም በመሄድ ለመሳተፍ ሞክሮ ነበር። በቅርብ ግዜም የልብ ችግር ገጥሞት የእርዳታ ጥሪ ቀርቦ አሁን አሜሪካ ህክምና እያገኝ … Continue reading አስገደ እና የትግራይ ህዝብ ትግል ምን አገናኛቸው?

በቀውስ የሚታመሰው የአፍሪካ ቀንድ እና የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ

(ዮሐንስ ገበየሁ) የአፍሪካ ቀንድ ከሀብታሞቹ የነዳጅ ባለቤቶች የባህረ ሰላጤው አገሮች ጋር በቀይ ባህርና በባቤል መንደብ ወሽመጥ አማካይነት ይገናኛል፡፡ ሀብታሞቹ የባህረ ሰላጤው አገሮች ከምዕራቡ ዓለም ኢኮኖሚ ጋር በሆርሙዝና ባቤል መንደብ ወሽመጦች የሚያገናኝ ነው፡፡ የኤደን ሰላጤና ቀይ ባህር በተባሉ ስትራቴጂካዊ ቦታዎች በየዓመቱ 700 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የንግድ ልውውጥ የሚደረግበት ከመሆኑም በላይ ሜድትራኒያን ባህር፣ የስዊዝ ቦይና ቀይ ባህርን … Continue reading በቀውስ የሚታመሰው የአፍሪካ ቀንድ እና የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ

የብሔር ፖለቲካ፣ የኢትዮጲያ ታሪክና የመሪዎቿ ተጠያቂነት

“በአንድ ሀገራዊ ጀግና ላይ እንኳን መግባባት ያቅተን?!” ይህ ባለፈው ሳምንት በአንዱ የፌስቡክ ገፅ ላይ ያነበብኩት ነው። በእርግጥ ፅሁፏ አንድ ዓ.ነገር ናት። በጥያቄው ውስጥ የታጨቀው ሃሳብ ግን የአንድ ክፍለ ዘመን ታሪክ ያህል ረጅምና ውስብስብ ነው። ጉዳዩ ከጄ/ል ጃጋማ ኬሎ ሞት ጋር ተያይዞ እንደተነሳ መገመት ይቻላል። በተለይ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በአንዱ ወገን በጄ/ል ጃጋማ ሞት የተሰማን ሀዘን … Continue reading የብሔር ፖለቲካ፣ የኢትዮጲያ ታሪክና የመሪዎቿ ተጠያቂነት

የሻዕብያ ትንኮሳና ኣብዮታዊ ዴሞክራሲ

(ህዳሴ ኢትዮጵያ) መነሻ ሃሳብ እንደ ኣውሮፓውያን ኣቆጣጠር (እ.ኣ.ኣ) በ1960ዎች ኣብዛኛው የአፍሪካ ኣገራት ከቅኝ ኣገዛዝ ነፃ ሲወጡ፣ ቅኝ ገዢዎች የተዉላቸው መሰረተ ልማቶችና ኢንዱስትሪዎች የአፍሪካ መንግስታት ለአገር እድገታቸው እንደ መነሻ ሃብት ሲጠቀሙበት፤ በዛን ጊዜ አገራችን ይቅርና መነሻ ሃብት ሊኖረን ህዝባችን በድህነት ኣሮንቋና በረሃብ የሚያልቅበት ጊዜ ነበር፡፡ እ.ኣ.ኣ. በ1970ዎች መጀመሪያ የህዝቦች ቁጣ ጫፍ ደርሶ በመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች ዓመፅ … Continue reading የሻዕብያ ትንኮሳና ኣብዮታዊ ዴሞክራሲ

በኘሮፖጋንዳ ወፍጮ ሐቅ አይጨፈለቅም

(ሙርቲ ጉቶ – ከፊንፊኔ) 1/ እንደ መነሻ በሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አመራር ውስጥ የሚገኘው ተስፋፊ ቡድን ጊዜ ያለፈበትን ቅዠት ለማሳካት አጠናክሮ የተያያዘውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ለመደገፍ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሰፊ የአሉባልታ ዘመቻ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ተስፋፊው ቡድን ኘሮፖጋንዳሲቶችን በማሰማራት የጥላቻ መርዝ እየዘራ በኦሮሞ ሕዝብ፣ በክልሉ መንግስትና አመራር ላይ የጀመረው የስም ማጥፋት ዘመቻ ዋጋ የሌለው የፖለቲካ ብልግና … Continue reading በኘሮፖጋንዳ ወፍጮ ሐቅ አይጨፈለቅም

የበሬ ስጋ እየበላህ የአህያን ስጋ መከልከል አትችልም

“አህያ!” – “ደደብ፥ ደነዝ፥ የማይገባው” ለማለት፣ “በቅሎ አባትሽ ማን ነው ቢሏት አጎቴ ፈረስ ነው አለች” – ለአህያ ያለንን ዝግተኛ ግምት ያሳያል፣ “አህያ ሰባ ምን ሊረባ” – የአህያ ሥጋ እንደማይበላ ይጠቁማል፣ …ወዘተ። እድሜ ለአለም አቀፉ የገበያ ትስስር (Globalization)፣ በሀገራችን ክብር የተነፈጋት እና ዝቅተኛ ግምት የመሚሰጣትን አህያ የሚፈልግ እንግዳ ከሩቅ ምስራቅ ድረስ መጥቷል። የአህያን ሥጋ ቬትናሞች ለምግብ፣ … Continue reading የበሬ ስጋ እየበላህ የአህያን ስጋ መከልከል አትችልም