Category Archives: Benshangul-Amhara eviction

ቤኒሻንጉል:- 28 ሀላፊዎች ዜጎችን በማፈናቀል ተጠርጥረው ታሠሩ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሽ ዞን ያሶ ወረዳ የሚኖሩ የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆችን ያለአግባብ አፈናቅለዋል ተብለው የተጠረጠሩ 28 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ፡፡ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ጋዎ ጃኔ ትናንት እንደገለጹት ተጠርጣሪዎቹ ካለፈው እሁድ ጀምሮ የተያዙት በቅርቡ በያሶ ወረዳ ለረጅም ዓመታት የኖሩ የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆችን በማፈናቀል ወንጀል ተጠርጥረው ነው፡፡ በቁጥጥር ሥር የዋሉት 28 … Continue reading ቤኒሻንጉል:- 28 ሀላፊዎች ዜጎችን በማፈናቀል ተጠርጥረው ታሠሩ

ቤኒሻንጉል:- በዜጎች መፈናቀል ሳቢያ የም/ቤት አባላት ታሠሩ

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ካማሽ ዞን በዜጎች መፈናቀል እጃቸው አለበት የተባሉ ኃላፊዎች ያለመከሰስ መብት መነሳቱን ፋና እና የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ገለጹ፡፡ ******* ፋና የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ምክር ቤት ትናት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ በክልሉ ነባር የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆች መፈናቀል ምክንያት ናቸው ያላቸውን 2 የምክር ቤት አባላትን ያለ መከሰስ መብት አነሳ። ያለ መከሰስ መብታቸው ተነስቶ በቁጥጥር ስር ውለው በህግ … Continue reading ቤኒሻንጉል:- በዜጎች መፈናቀል ሳቢያ የም/ቤት አባላት ታሠሩ

ከቤኒሻንጉል ክልል ዜጎችን ያፈናቀሉ ኃላፊዎች ተባረሩ | Reporter

(በታምሩ ጽጌ እና ውድነህ ዘነበ) Highlight: በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ካማሽ ዞን ያሶ ወረዳ ውስጥ ከአራት እስከ 28 ዓመታት የኖሩ የአማራ ብሔር ተወላጆችን እንዲፈናቀሉና እንግልት እንዲደርስባቸው አድርገዋል የተባሉ፣ የዞንና የወረዳ ኃላፊዎች ከኃላፊነታቸው ተነስተው መባረራቸው ታወቀ፡፡ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የካማሽ ዞን አስተዳዳሪ የሆኑትን አቶ መልከጅ ባጋሎንን ጨምሮ፣ ተፈናቃዮቹ ባሉበት የያሶ ወረዳ በአመራርነት የሚሠሩ አምስት ኃላፊዎች ከኃላፊነት መባረራቸውን … Continue reading ከቤኒሻንጉል ክልል ዜጎችን ያፈናቀሉ ኃላፊዎች ተባረሩ | Reporter

የቤንሻንጉል ተፈናቃዮች እንዲመለሱ ተወሰነ | Sendek

(በዘሪሁን ሙሉጌታ) ባለፉት ሁለት ሳምንታት በሺህ የሚቆጠሩ የአማራ ክልል ተወላጆች ከቤንሻንጉል ክልል ተፈናቅለው በጎጃም ፍኖተሰላም አካባቢ እንዲሰፍሩ የተደረገው በስህተት መሆኑን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ገለፁ። የተፈናቀሉት በሙሉ ቀደም ሲል ወደነበሩበት እንዲመለሱ መወሰኑንም አስታወቁ። የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አህመድ ናስር በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት ሰሞኑን ከክልሉ እንዲፈናቀሉ የተደረጉ የአማራ ተወላጆች በሙሉ እንዲመለሱ መወሰኑን ገልፀዋል። … Continue reading የቤንሻንጉል ተፈናቃዮች እንዲመለሱ ተወሰነ | Sendek

የቤንሻንጉል ተፈናቃዮች ተመፅዋች ሆኑ | Addis Admass

“ከእነ ቤተሠቤ እዚህ ለመድረስ ያየሁትን ፈተና ፈጣሪ ያውቀዋል፡፡ ቤተሰቤ ከቁጥር ሳይጐድል ለአገሬ መሬት በቅቻለሁና ከእንግዲህ የፈለገው ይሁን” አሉኝ፤ ከቤኒሻንጉል ክልል ያሶ ወረዳ ተፈናቅለው በፍኖተ ሰላም ድንጋያማ መጠለያ ውስጥ ያገኘኋቸው አዛውንት፡፡ በአማራ ክልል የከሠላ ወረዳ ተወላጅ የኾኑት አዛውንት፤ ኑሮ አልቃና ቢላቸው በ1997 ዓ.ም ሦስት ልጆቻቸውን ከትዳር አጋራቸው ጋር ይዘው፣የትውልድ ቀያቸውን ለቀው የተሻለ ሥራ ይገኝበታል ወደ ተባሉበት … Continue reading የቤንሻንጉል ተፈናቃዮች ተመፅዋች ሆኑ | Addis Admass

የቤንሻንጉል ፕ/ት: ተፈናቃዮቹ ኦሮሞዎችም ናቸው – አጣርተን እርምጃ እንወስዳለን

ባለፈው ሳምንት አዲስ አድማስ ጋዜጣ የዘገበውና (እዚህ ብሎግ ላይም የወጣ) ዜና፤ በበቤንሻንጉል ክልል የሰፈሩ ዜጐች “ሕገወጥ” ተብለው እንደተባረሩ መዘገቡ ይታወሳል፡፡ ዜናው እንዳለው ከሆነ፡-  “በሚኖሩበት አካባቢ የእርሻ ቦታ በማጣታቸውና የተሻለ ሥራ ፍለጋ ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ ከአማራ ክልል ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያሶ ወረዳ ተዘዋውረው የከተሙ በርካታ ሰዎች በወረዳው ባለሥልጣናትና ፖሊሶች፤ ሰብአዊ መብታቸው ተጥሶ ከቀያቸው መፈናቀላቸውን…ገለፁ፡፡ የያሶ ወረዳ ዋና … Continue reading የቤንሻንጉል ፕ/ት: ተፈናቃዮቹ ኦሮሞዎችም ናቸው – አጣርተን እርምጃ እንወስዳለን

በቤንሻንጉል ክልል የሰፈሩ ዜጐች “ሕገወጥ” በሚል ተባረሩ | Addis Admass

* በከተማው የሠሩትን ቤት መላ እስኪያሲዙና ንብረታቸውን እስኪሰበስቡ ጊዜ እንዲሰጣቸው ቢጠይቁም ‹‹ቤትና ንብረቱ የሚገባው ለወረዳው ነው›› በሚል ወረዳውን ለቀው እንዲወጡ [መገደዳቸው]…. * [የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ] – ወደመጡበት እንዲመለሱ የተደረጉት ሕገወጥ የሆኑት እንጂ በሕጋዊ መንገድ የገቡት እንዳልሆኑ በመግለጽ ሕጋዊ የሚባሉት ከክልላቸው ከወንጀልና ከመንግሥት እዳ ነፃ ስለመሆናቸው…የመሸኛ ደብዳቤ የሚያመጡትን መሆኑን ተናግረዋል፡፡ —— በሚኖሩበት አካባቢ የእርሻ ቦታ በማጣታቸውና የተሻለ … Continue reading በቤንሻንጉል ክልል የሰፈሩ ዜጐች “ሕገወጥ” በሚል ተባረሩ | Addis Admass