Category Archives: Articles

Ethiopian Muslims: የ1966ቱ ሰልፍና 13ቱ ጥያቄዎች

አቶ መሐመድ ሀሰን የ1966ቱ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የተቃውሞ ሠላማዊ ሠልፍ አደራጅ የነበሩ ሲሆን፤ እንዲሁም በ1999(2007 እ.ኤ.አ) በሐጅ ነጂብ መሐመድ የተመራው የልዑካን ቡድን አባል እና ቡድኑ ለጠ/ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ያቀረበው ዶክመንት ዝግጅት ተሳታፊ ነበሩ፡፡ የበድር ፋውንዴሽን መጽሔት በነዚህ ጉዳዮች ዙሪያ በ2000 ዓመተ-ምህረት ከመሐመድ ሐሰን ጋር ያደረገውን ሙሉ ቃለ-ምልልስ ከታሪካዊ ፋይዳው አንጻር እዚህ አቅርበነዋል፡፡ Highlights:- * “የአሁኑ ጠቅላይ ሚንስትር [መለስ … Continue reading Ethiopian Muslims: የ1966ቱ ሰልፍና 13ቱ ጥያቄዎች

ኢትዮጵያዊነትና የኢህኣዴግ የብሄር ፖለቲካ

(ጆሲ ሮማናት) ኢህኣዴግ ስልጣን በያዘበት ሰኣት ኢትዮጵያ ውስጥ ብሄርን መሰረት ያደረገ ፖለቲካዊ መፍትሄ መስጠቱ ትክክል ነው ብቻ ሳይሆን ሌላ ኣማራጭ ኣልነበረም፡፡ የተለያዩ የኢትዮጵያ ህዝቦች ለዘመናት ሲደርስባቸው የነበረው ጭቆና ብሃራቸውንና ሃይማኖታቸውን መሰረት ያደረገ ነበር፡፡ የሃይማት ጭቆናው መንግስትና ሃይማኖት የተለያዩ እንዲሆኑ በማድረግ ሃገሪቱ ማንኛውን ሃይማኖት በእኩል ኣይን ማስተናገድ የምትችልበት ስርኣት በመፍጠር ተፈቷል፡፡ በተመሳሳይም ብሄሮችና ብሄረሰቦች ሁሉም በእኩል … Continue reading ኢትዮጵያዊነትና የኢህኣዴግ የብሄር ፖለቲካ

ለበእውቀቱ ስዩም:-እውን የድሮው ኢትዮጵያዊነት የመዋጮ ነበርን?

(ጆሲ ሮማናት) በእውቀቱ ስዩም ኢትዮጵያ የብሄርተኝነት ሃይማኖት ክፉኛ ያሰጋታል ይለናል፡፡ ሰሞኑን ጃዋር መሃመድንና ሌሎች “ብሄርተኛ” ብሎ የፈረጃቸውን መልሶ ለመሞገት “የዘመኑ መንፈስ” ብሎ በጻፈው ጽሁፍ የዘመኑ “ታሪክ ከላሾች” እንደሚሉት ኣሁን የምናያት ኢትዮጵያ “በኣማራ ባህላዊ ስርጭት እና በኣማራ ፖለቲካ የተገነባች” ሳትሆን የብዙ ብሄር ብሄረሰቦች ግንኙነት ስብጥር ነች ይከራከራል ፡፡ የኢትዮጵያ ኣገራዊ ማንነት መገለጫ የኣማራ ባህላዊ ማንነት ሳይሆን … Continue reading ለበእውቀቱ ስዩም:-እውን የድሮው ኢትዮጵያዊነት የመዋጮ ነበርን?

ግምገማ:- የግርማ ሰይፉ መጽሐፍ “የነፃነት ዋጋ ስንት ነው?”

(በየማነ ናግሽ) ፍርኃታችን ልክ አይደለም፡፡ ኢሕአዴግ ሁለትና ሦስት በመቶ እያስፈራራን እኛ ግን 95 እና 96 በመቶ እየፈራን ነው፤›› ሲሉ በደጋፊዎቻቸው ጭብጨባ ታጅበው ነበር፡፡ ‹‹አዎ ፈሪዎች ነን›› የሚለውን አባባላቸውን ማረጋገጥ እስኪመስል ድረስ ጭብጨባው ቀጥሎ ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ (መድረክ – አንድነት) የፓርላማ አባል አቶ ግርማ ሰይፉ ‹‹የነፃነት ዋጋ ስንት ነው?›› የሚለውን መጽሐፋቸውን ባስመረቁበት ጊዜ … Continue reading ግምገማ:- የግርማ ሰይፉ መጽሐፍ “የነፃነት ዋጋ ስንት ነው?”

የኢትዩጵያ ተቃዋሚ ፓለቲከኞችና ፓለቲካቸዉ

(አቢይ ጨልቀባ ወርቁ) መግቢያ፡- ይህ ፅሑፍ በተለያዩ ወቅቶች የተለያዩ የኢህአዴግ ተቃዋሚ ፓለቲካ ፓርቲዎች እና ፖለቲከኞች በተለያዩ መድረኮች እና ፎሮሞች ስለ ራሳቸዉ እና አማራጭ የሚላቸዉ “ፓሊሲዎች” በሚናገሩበት፣በሚፅፍበት፤ ቃለ-መጠይቅ በሚሰጡበት ወቅት እየወሰደ፣ እያጣቀሰ ከፓለቲካዊ ፍልስፍና እንዲሁም ከነባራዊ የአገራችን ሁኔታ እየመዘዘ የአመክንዮ ሕፀፅ የሚያሳይ ነዉ፡፡ ለዚህ ፅሑፍ ሲባል ብቻ የኢህአዴግን የተቃዋሚ ፓለቲካ ፓርቲዎች ማለት በሰላማዊ መንገድ በአገር ዉስጥ … Continue reading የኢትዩጵያ ተቃዋሚ ፓለቲከኞችና ፓለቲካቸዉ

የብርሃኑ ነጋ ሚስጥራዊ ንግግር (በፅሑፍ – እንደወረደ)

(አቢይ ጨልቀባ ወርቁ) የ‹ግንቦት 7› ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ ከባዕዳን ስለተቀበሉት ገንዘብ፣ የኢሳት ድርሻ እና ተያያዥ ጉዳዮች ለድርጅታቸው አመራሮች ገለፃ የሰጡበት ሚስጥራዊ ስብሰባዎች ሁለት የድምጽ ቅጂ ከጥቂት ሳምንታት በፊት አፈትልኮ ወጥቶ መሰራጨቱ ይታወሳል፡፡ በድምጽ ቅጂዎቹ ላይ ያለውን የብርሀኑን ንግግር በፅሑፍ በመገልበጥ እንደሚከተለዉ አቀርበዋለሁ፡፡ ——— የመጀመሪያው የድምጽ ቅጂ አራት ሆነን ሄደናል፡፡ አንድ ሙሉ ቀን የፈጀ ዉይይት አድርገናል፡፡ ዋናዉ ሰዉየ አልመጡም: … Continue reading የብርሃኑ ነጋ ሚስጥራዊ ንግግር (በፅሑፍ – እንደወረደ)

ተቃዋሚዎችና የህዳሴ ግድብ፡- ቅብብሎሹ ከየት ወዴት ነው?

(By እናት ከመሳለሚያ) ዘንድሮ 22ኛው የግንቦት 20 በዓል የተከበረው የህዳሴ ግድቡ ከደረሰበት የላቀ ደረጃ ጋር በማስተሳሰር ነበር፡፡ የግድቡን ግንባታ ወደ አንድ ደረጃ ከፍ ያደረገው በተወሰነ ኪሎ ሜትር ውስጥ የውሃውን ፍሰት የማስቀየስ ሥራ በእዚሁ የድል በዓል ወቅት መከናወኑ ዕለቱን ልዩ ትርጉም አሰጥቶቷል፡፡ ኢትዮጵያ የግድቡ ግንባታ ሥራ አመቺነትን ለማረጋገጥ ያከናወነችውን ተግባር ተከትሎ የግብፅ መንግሥት እና አንዳንድ የሀገር … Continue reading ተቃዋሚዎችና የህዳሴ ግድብ፡- ቅብብሎሹ ከየት ወዴት ነው?

ሙሼ ሰሙ፡- መንግስት የግል ባንኮችን ለማጥፋት ታጥቆ ተነስቷል

(አለማየሁ አንበሴ) የአዲስ አበባ የቤቶች ልማት የቁጠባ ፕሮግራም መንግስታዊ በሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ እንዲከናወን መደረጉ በግል ባንኮች ላይ ከፍተኛ ኪሣራ እያስከተለ እንደሆነና በአጭር ጊዜ የግል ባንክ ዘርፉን ህልውና አደጋ ላይ እንደሚጥል የባንክ ባለሙያዎች ለአዲስ አድማስ ገለፁ፡፡ እስካሁን ከ750ሺህ በላይ ግለሰቦች የቤቶች ልማት ቁጠባ ሂሣብ በንግድ ባንክ እንደከፈቱ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የግል … Continue reading ሙሼ ሰሙ፡- መንግስት የግል ባንኮችን ለማጥፋት ታጥቆ ተነስቷል

ኢህአዴግ:- መድረክና አንድነት መቼም ከግድቡ ጎን አይቆሙም

Highlights: * መድረክ ዘንድሮም እንደተለመደው የነገሮችን አወዳደቅ ካየ በኋላ ባወጣው መግለጫ ከዚህ በፊት አላምንበትም ያለውን ግድብ ግንባታ ለማሳካት ከኢህአዴግ ጋር መደራደር አለብኝ፤ ከግብፅ ወገን የሚመጣ ስጋትን ለመመከት ከኔ ጋር መደራደር የግድ ነው ብሎ ተነስቷል፡፡ * የአገራችን ህዝቦች ግድቡን የማንንም እጅ ሳያዩ ለመገንባት ቆርጠው እንደተነሱ ሁሉ ለግድቡ ግንባታ በኩርፍያ ጥግ ይዘው የቆሙ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ይሁንታ ማግኘትም አያስፈልጋቸውም፡፡ … Continue reading ኢህአዴግ:- መድረክና አንድነት መቼም ከግድቡ ጎን አይቆሙም

ኢሳትን ተው በሉት! (ወሰንሰገድ ገ/ኪዳን)

Highlight: ኢሳት (ESAT) እንደተቋምነቱ ዘገባውን ማስተላለፉ “ጤና-ቢስነቱ”ን የሚያሳይ ነው የሚመስለኝ፡፡ እኔ የማውቀው የኦሮሞ ህዝብ “ጉዲፈቻ” የሚባል እጅግ የረዥም ዘመን አዙሪ ባህል እንዳለው ነው፡፡ እንጂ ህፃናትን ለገደለ የነበዘ ወታደር “ሲያመልክ” አይደለም፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፡፡ የአማራ ሕዝብም ቢሆን ያኛው ብሄር ነፍሶ ገዳይ ያመልካል የሚል ዕምነት የለውም፡፡ ሊኖረውም አይችልም፡፡ —— (ከወሰንሰገድ ገ/ኪዳን) እውነት ቤት ስትሰራ ውሸት ላግዝ ካለች ጭቃ ከረገጠች ምስማር ካቀበለች ቤቱም … Continue reading ኢሳትን ተው በሉት! (ወሰንሰገድ ገ/ኪዳን)