Category Archives: Amharic

ስኬታማው የኢትዮጵያ ፕብሊክ ዲፕሎማሲ እና እያደገ የመጣው ተሰሚነት

(ስንታየሁ ግርማ) አዲሱ ዲፕሎማሲ ከሴፕተምበር 9/11 በኋላ በስፋት ተቀባይነት እያገኘ እንደመጣ አንዳንድ ምሁራን ያስረዳሉ፡፡ ለአዲሱ ዲፕሎማሲ መጠናከር ዋነኛ ምክንያቶች ተብለው የሚጠሩት ግሎባላይዜሽን (ሉላዊነት) እየተስፋፋ መምጣቱ እና ዓለም በኢንፎርሜሽን ኔትወርክ በጥብቅ መቆራኘት በዋነኝነት ይጠቀሳሉ፡፡ አዲሱ ዲፕሎማሲ ከመንግስት ለመንግስት ብቻ ያተኮር የነበረው “አሮጌውን ዲፕሎማሲ” በህዝብ ዲፕሎማሲ እንደተካው የሚያምኑ ብዙ ናቸው፡፡ አሁን ባለንበት ዘመን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ዓላማዎችንና … Continue reading ስኬታማው የኢትዮጵያ ፕብሊክ ዲፕሎማሲ እና እያደገ የመጣው ተሰሚነት

የኮንሶ ህዝብ ጥያቄ ተገቢዉን ምላሽ ይሻል !

(ኮሎኔል አስጨናቂ ገ/ጻዲቅ ሺፈራዉ) በቅድሚያ በኮንሶ ህዝብ ላይ እየደረሰ ሲላለዉ በደል አንዳችም ትርፍ  ነገር ሳይጨምር ሳይቀንስና ሳይደባብቅ ሃቁን ለህዝብና ለሚመለከታቸዉ የመንግስት ባለስልጣና አካላት ሁሉ እንዲደርስ ባደረገዉ በአቶ ናሁሰናይ በላይ የተሰማኝን ኩራትና አድናቆት ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡ ናሁሰናይ አስታዋሽ ያጣዉና ትኩረት የተነፈገዉ  የኮንሶ ህዝብ  ብቻ  ሳይሆን  ጭቆናንና በደልን የሚጸየፉ የመላዉ የሀገራችን ህዝቦች ሁሉ እንደሚያሰግኑህ ቅንጣት ጥርጥር የለኝም፡፡ ሆርን … Continue reading የኮንሶ ህዝብ ጥያቄ ተገቢዉን ምላሽ ይሻል !

የትግራይ ህዝብ የለውጡ አጋር እንጂ ተጠቂ ሊሆን ኣይገባም

(መርስዔ ኪዳን) ([email protected] – ሜኔሶታ፤ ሃገረ ኣሜሪካ) ሰሞኑን በሃገራችን ውስጥ እየተካሄደ ባለው ህዝባዊ አመፅ ምክኒያት ብዙ የሰው ህይወት፣ የአካል ጉዳትና የንብረት ውድመት እየደረሰ ነው። ይህ ሁኔታ እንዲፈጠር ያበቁ ብዙ ምክኒያቶች ቢኖሩትም አንዱና ዋነኛው ምክኒያት በሃገሪቱ ውስጥ ፍትሃዊ የሆነ የፖለቲካ ስርዓት አለመኖሩ ነው። ኢትዮጵያ ብዙ ብሄሮች ብቻ ሳይሆን ብዙ ፖለቲካዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አመለካከት ያለው ህዝብ የሚኖርባት አገር … Continue reading የትግራይ ህዝብ የለውጡ አጋር እንጂ ተጠቂ ሊሆን ኣይገባም

[Video]ም/ጠ/ሚ ደብረጺዮን – ወቅቱ ያናግራል፣ ‘ለምን ዓላማ ተናገሩ’ ወደሚል መሄዱ አይጠቅምም

ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚሰነዘሩ ሀሳቦችን በይዘታቸው በመመዘን ጠቃሚውን መውሰድ እንጂ ለምን ተባለ ወደሚለው መሄድ አይጠቅምም፤ ብለዋል በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የኢኮኖሚና ፋይናንስ ክላስተር አስተባባሪ ደብረጺዮን ገብረሚካኤል፡፡ ዶ/ር ደብረጺዮን ይህንን የተናገሩት ባለፈው ነሐሴ 27/2008 ለኦንላይን ሚዲያዎች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነበር፡፡ የቀድሞ የህወሓት ነባር አመራሮች (እነጄ/ል ጻድቃንና ጄ/ል አበበ) ከቅርብ ግዜ ወዲህ በስፋት ትችቶችን እየሰነዘሩ ስለመሆኑ በተጠየቁበት ወቅት … Continue reading [Video]ም/ጠ/ሚ ደብረጺዮን – ወቅቱ ያናግራል፣ ‘ለምን ዓላማ ተናገሩ’ ወደሚል መሄዱ አይጠቅምም

ለሀገሪቱም ለኢህአዴግም የሚበጀዉ ሀገር ወዳድ ምሁራንን ማዳመጡ ነዉ!

(ኮሎኔል አስጨናቂ ገ/ጻዲቅ ሺፈራዉ) መግቢያ በሃገራችን የተከሰተዉን አደገኛ ሁኔታ ስጋት የገባቸዉ ቅን የሆኑ ኢትዮጵያዉያን አገሪቱን ከአደጋ መታደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የበኩላቸዉን ምክረ ሃሳብ እያቀረቡ ባለበት ሰዓት አንዳችም ኃላፊነት የማይሰማቸዉ አንዳንድ ወገኖች ደግሞ አሁን ያለዉ ቀዉስ ተባብሶ  የበለጠ ምስቅልቅል ሁኔታ እንዲፈጠር ሆን ብለዉ መርዘኛ የሆነ ቀስቀሳ ከማድረግ አልተቆጠቡም:: መንግስት በሀገሪቱ የተከሰተዉ ሁኔታ አሳስቦት ራሱን በግልጽ ፈትሾና … Continue reading ለሀገሪቱም ለኢህአዴግም የሚበጀዉ ሀገር ወዳድ ምሁራንን ማዳመጡ ነዉ!

“አወቅሽ አወቅሽ ሲሏት…” (ለሜ/ጄኔራል አበበ ተ/ሃይማኖት ጽሑፍ የተሰጠ ምላሽ) (ክፍል 2)

(መሓሪ [email protected]) (ክፍል ሁለትና የመጨረሻው) ውድ አንባቢያን በክፍል አንድ ፅሑፌ ላይ “ጆቤ” በሰራዊቱ ግንባታ ሰነድ ላይ ያነሷቸውን ሃሳቦች ከተጨባጭ ሰነዱ ጋር በማመሳከር ነጥቦቹ ትክክል አለመሆናቸውን ለማሳየት ሞክሬያለሁ። ሰውዬው ለማንሳት የሞከሯቸው ሌሎች ጉዳዩችንም እንዲህ ተመልክቻቸዋለሁ። መልካም ንባብ።… ጡረተኛው ሜ/ጄኔራል ሰነዱን አስመልክተው ያነሷቸው ሃሳቦች ለእርሳቸው ፍጆታ በሚውል መልኩ ቀነጫጭበውና እውነት አስመስለው ለማቅረብ ሞክረዋል። ለዚህም “በእኛ ተጨባጭ ሁኔታ … Continue reading “አወቅሽ አወቅሽ ሲሏት…” (ለሜ/ጄኔራል አበበ ተ/ሃይማኖት ጽሑፍ የተሰጠ ምላሽ) (ክፍል 2)

Video | የመንግሥት ቃለ-አቀባይ ጋዜጣዊ መግለጫ

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ:- ከኤርትራ ጋር ስለነበረው ግጭት፣ ከአልሸባብ ጋር ስለነበረው ውጊያ፣ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ፕሮግራም እንደገና ስለመራዘሙ፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ስለኦሮሚያና ቅማንት ስላቀረበው ሪፖርት እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፡፡ ቪድዮውን ይመልከቱ፡፡ ***************

የአማራ ክልል መንግሥት የቅማንት ብሔረሰብንና የክልሉ ሕዝብን ይቅርታ እንዲጠይቅ ተወሰነ

(ዮሐንስ አንበርብር – ሪፖርተር ጋዜጣ) በኦሮሚያ ክልል ብጥብጥ የፀጥታ ኃይሎች ተመጣጣኝ ኃይል ተጠቅመዋል ተባለ ከፍተኛ ኃይል የተጠቀሙ የአማራ ክልል ልዩ ፖሊስ አባላት በሕግ እንዲጠየቁ ተወሰነ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በኦሮሚያ በርካታ ቦታዎች ተፈጥሮ የነበረውን ግጭትና ሁከት በራሱ አነሳሽነት እንዲሁም በአማራ ክልል በሰሜን ጐንደር ከቅማንት የማንነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ የቀረበለትን አቤቱታ መሠረት በማድረግ ያካሄደው የሰብዓዊ መብት … Continue reading የአማራ ክልል መንግሥት የቅማንት ብሔረሰብንና የክልሉ ሕዝብን ይቅርታ እንዲጠይቅ ተወሰነ

ጉንጭን ማልፋት ይሻላል ከጦርነት

የ2ኛው ዓለም ጦርነት ሲነሣ የአንድ ሰው ስም አብሮ ይነሳል። በወቅቱ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት የዊኒስተን ቸርችል ስም። ይህ ታላቅ መሪ በሀገሩ እንግሊዝ ሉዓላዊነት ላይ የተቃጣውን አደጋ በመመከት የቁርጥ ቀን መሪ መሆኑን አስመስክሯል። በዚህ ረገድ የዋለው ውለታ ለሀገሩ ብቻ አልነበረም። በተለይ በናዚ ጀርመን እና ፋሽስት ኢጣሊያ ቁጥጥር ስር ለወደቁት ሀገራት ጭምር ባለውለታ ነው። ከዚህ ውስጥ ሀገራችን … Continue reading ጉንጭን ማልፋት ይሻላል ከጦርነት

ነፃነት “የፈጣሪ”፣ ፍርሃት “የሰይጣን” ነው!

ነፃነት ለሰው ልጅ የተሰጠ ተፈጥሯዊ ፀጋ እንደመሆኑ፤ በነፃነት ማሰብ፣ መናገርና መፃፍ የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባህሪ ነው። ነፃነት ሰብዓዊ መብት ሳይሆን የሰብዓዊነት ተግባራዊ መገለጫ ነው። በመሆኑም፣ ነፃነት ከሌለው ሰው ሰብዓዊ ክብሩን ያጣል። ይህን ተፈጥሯዊ ባህሪ የመስጠትና የመግፈፍ ስልጣን ያለው ፈጣሪ ብቻ ነው። ምክንያቱም፣ በሕይወት የተሰጠኝ ነፃነት በሞት ይወሰዳል። ሞትን የደገሰልኝ ፈጣሪ ሕይወትን ጠንስሶልኛልና እሱ ብቻ የሰጠውን … Continue reading ነፃነት “የፈጣሪ”፣ ፍርሃት “የሰይጣን” ነው!