All posts by Reagan Solomon

Reagan Solomon

ማዕተብ ከሂጃብ

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታዮች በአንገታቸው ላይ የሚያሥሩት ማዕተብ ወደፊት ይከለከላል የሚለውን ወሬ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ሺፈራው ተክለማርያም ከማስተባበላቸው ቀደም ብሎ የተጀመረ ክርክር ነበር:: ይህ ክርክር ‹‹ በሙስሊም ሴቶች የሚለበሰው ሂጃብ የሚከለከል ከሆነ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ማዕተብ በዚያ መልኩ ሊታይ ይገባዋል›› የሚል ነው;; ይህን አይነት ክርክር በተለያዩ ማህበራዊ አውታሮች በተለይም በፌስቡክ እየቀረበ ነው፡፡ በብዙዎች የማህበራዊ አውታር … Continue reading ማዕተብ ከሂጃብ

የአናርኪው ረሰፒ (recipe for anarchy) – በኢትዮጵያ

አናርኪ(anarchy) በርካታ ትርጉሞች አሉት:: ብዙዎች የሚስማሙበት ትርጉሙ ግን አስፈጻሚ መንግስት የሌለው ማህበረሰብ ማለት ነው:: አናርኪስት(anarchist) ማለት ደግሞ መንግስት ወይም ህግና ሥርዓት ለአንድ ማህበረሰብ አስፈላጊ አይደሉም ብሎ የሚያምን እና ለዚህም ዓይነት አጋጣሚ እውን መሆን ጠንክሮ የሚሰራ ግለሰብ ነው:: የአናርኪስትነትን አስተሳሰብ እንደሀሳብ መከተል ወንጀል አይደለም:: ልክ በስርዓትና በህግ እንደሚያምን ሁሉ አስተሳሰቡን መያዝና በብዙ ሀገሮችም የማሰራጨት መብት አለው:: … Continue reading የአናርኪው ረሰፒ (recipe for anarchy) – በኢትዮጵያ

የምግብ ዋስትና ፖለቲካ እና የኢትዮጵያ ሁኔታ

በብዙ ጉዳዮች የተቃዋሚው ጎራና የኢትዮጵያ ምሁራን ኋላ እንደሚቀሩ በግሌ ስገምት ነበር:: አንዱ ምክንያቴ የመንግስትና ህዝብ አስተዳደር ጉዳዮች በተለይም ህዝብ ከሚፈልጋቸው ፕሮግራሞችና ፅንሰ ሀሳቦች ጋር በቀጥታ ያለመገናኘታቸው ነው:: ሌላኛው ምክንያት የተቃዋሚው ጎራ እራሱን ከአዳዲስና አማራጭ የፖሊሲ ሀሳቦች ጋር ከማስተዋወቅ ይልቅ እንትን ይወድቅልኛል ብሎ የሚከተል አይነት በመሆኑ ነው:: ሀገር በብቃት ለመምራት የሀገሪቱን የተሳኩና ያልተሳኩ ትልሞችን፣ የፖሊሲና የህግ … Continue reading የምግብ ዋስትና ፖለቲካ እና የኢትዮጵያ ሁኔታ

የሂውማን ራይት ዎች የቴሌኮም መስመሮች ጠለፋ ክስና የተዓማኒነት ጥያቄ

የሰብአዊ መብት ጠበቃው ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዎች ከናይሮቢ ጽ/ቤቱ ያወጣው የዚህ ዓመት ሪፖርት በቴሌኮም መስመሮችና የመረጃ መረብ ጠለፋ ላይ ያተኩራል:: ሪፖርቱ በተዓማኒነቱ ላይ ጥያቄ በሚያስነሱ ጉዳዮችም ታጭቋል:: ለዛሬ የምንመለከተው ከዚህ በታች የተሰጠው አጠር ያለ የአንድ ተገልጋይ ምላሽ ይገኝበታል:: የዚህ ተገልጋይ ምላሽ ወደ መቶ ሰው ለተስተናገደበት ጥናት መደምደሚያ ጎላ ተደርጎ የሚጠቀስና አብዛኛውን ስለዚህ ጉዳይ ጥልቅ ዕውቀት … Continue reading የሂውማን ራይት ዎች የቴሌኮም መስመሮች ጠለፋ ክስና የተዓማኒነት ጥያቄ

ጥቂት ስለእንስትነት(Feminism) ጽንሰ ሀሳቦች

በዚህ ወር ለተከበረው ዓለም-አቀፍ የሴቶች ቀን ክብር ስል ስለእንስትነት(Feminism) ጽንሰ ሐሳቦችና ታሪካዊ አመጣጣቸው ማንበብ ተያይዣለሁ:: እኔ ራሴን የከተማ ሰውና ለሴቶች ክብር የምሰጥ አድርጌ አያለሁ:: በጣም የገረመኝ ታዲያ በዚህ ሰሞን ስለ እንስትነት ያነበብኩት እስከዛሬ ከማውቀው የተለየ በመሆኑ ነው:: መሠረታዊው ጽንሰ ሀሳብ የሚለው ዛሬ የጾታ (gender) ጽንሰ ሀሳብ ከሚገልፀው እምብዛም አይለይም:: የመጀመሪያዋ የእንስትነት (feminism) ጽንሰ ሀሳብ አቀንቃኝ … Continue reading ጥቂት ስለእንስትነት(Feminism) ጽንሰ ሀሳቦች