All posts by Kebede Kassa

Kebede Kassa

የተክሌ በቀለ የትግል ጥሪ እና የአንድነት ፓርቲ ዕጣ

የፓርላማ አባሉና የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ /አንድነት/ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ የልማት ሰራዊት ግንባታ ላይ እየተረባረብኩ ነው የሚለውን መንግስት ለመገዳደር የትግል ሰራዊት መገንባት እንደሚገባ ከአንድ ቀን በፊት እንዲህ ሲሉ በብሎጋቸው ላይ አስፍረው ነበር፡፡ “የሰላማዊ ትግል ሰራዊት እንዴት እንገንባ ለሚለው ጥያቄ አፋጣኝ ምለሽ ካልሰጠን በስተቀር መንግሰት በግልፅ እየደገፈ ያለው በጠብመንጃ ሊገዳደሩ የፈለጉትን ነው” … Continue reading የተክሌ በቀለ የትግል ጥሪ እና የአንድነት ፓርቲ ዕጣ

የአንድነቶች የእርስ-በርስ የፌስቡክ ጦርነት

ሰሞኑን ዘና ከምልባቸው ነገሮች አንዱ በአንድነት አመራሮችና አባላት መካከል ያለው የቃላት ጦርነት ነው፡፡ በተለይ በኢንጅነር ዘለቀ ረዲና በአቶ ግርማ ካሳ መካከል፡፡ እንደሚታወቀው አንድነት አሁን ‘የኢንጂነር ግዛቸዉ አንድነት’ እና ‘የበላይ ፍቃዱዉ አንድነት’ በሚል ለሁለት ተከፍሏል፡፡ ተክሌ በቀለ ለጊዜው ‘ሶስተኛውን አንድነት’ ለመመስረት የሚያስችል በቂ ድጋፍ ስለሌላቸው ‘ከሁለተኛው አንድነት’ ጋር ተዳምረው ያሉበት ሁኔታ ነው ያለው /ሁ.ነ.ያ/፡፡ እኔ እንደታየኝ … Continue reading የአንድነቶች የእርስ-በርስ የፌስቡክ ጦርነት

የደመወዝ ጭማሪ እንደአጀንዳ | አህያውን ፈርቶ …

የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሩ አቶ ሱፊያን አህመድ ስለመንግስት ሰራተኞችና ጡረተኞች የደመወዝ ጭማሪ ሐምሌ 26/2006 በሰጡት መግለጫ እንደታወቀው የመንግስት ሰራተኞች ዝቅተኛ የደመወዝ መጠን በፊት ከነበረበት 420ብር ወደ 615ብር አድጓል፡፡ ከፍተኛው የደመወዝ መጠን ደግሞ በፊት ከነበረበት 4,434ብር ወደ 5,897ብር አድጓል፡፡ ይህ እንግዲህ በቅደም ተከተሉ የ46በመቶና የ33በመቶ ጭማሪ ነው፡፡ ዝቅተኛ የጡረታ ክፍያ በፊት ከነበረበት 294ብር በ71በመቶ አድጎ 530ብር … Continue reading የደመወዝ ጭማሪ እንደአጀንዳ | አህያውን ፈርቶ …

በረከት ስምዖን በመልካም ጤንነት ላይ ነው – በቅርቡ ይመለሳል

ሰሞኑን በማህበራዊ ድረ ገፆች አቶ በረከት ስምኦን የጤንነት ሁኔታው ጥሩ አይደለም፤ ከዛም አልፎ በህይወት የለም የሚሉ አሉባልታዎች ሲናፈሱ ነበር፡፡ አንዳንዶቹ መሞቱንስ አረጋግጠናል፤ ይልቁንስ የቀብር ቀኑን ንገሩን ሲሉም ተዘባብተዋል፡፡ እነዚህ በጥላቻ ፖለቲካ የናወዙ ተቃዋሚዎች በአንድ በኩል የኢሕአዴግን ከፍተኛ አመራሮች በማጥላላት ተጠምደው እየዋሉ በሌላ በኩል ደግሞ እነዚህን ግለሰቦች ከሰብዓዊ ፍጡር በላይ አድርገው በማሰብ ልክ እንደማይታመሙ ብሎም ሊሞቱ … Continue reading በረከት ስምዖን በመልካም ጤንነት ላይ ነው – በቅርቡ ይመለሳል

የሰሞኑ የመርሃ-ቤቴ ዓለም-ከተማ የሁከት ሙከራና እውነታው

በሰሜን ሸዋ ዞን በመርሃ ቤቴ ወረዳ ዓለምከተማ ሰሞኑን በፅንፈኛ ተቃዋሚው አፍ ውስጥ ገብታለች፡፡ አንዱ የፅንፈኛ ዲያስፖራ ተቃዋሚ ድረ ገፅ “ቁስለኞች ሆስፒታሉን አጣብውታል። ቁስለኞቹ የሚታከሙት በፖሊስ ታጅበው ሲሆን ህክምናውን እንደጨረሱ ወደ እስር ቤት ይወሰዳሉ።” ሲለን፤ ሌላው ሀገር ውስጥ ያለ ደጋፊው ይነሳና ደግሞ “የሰሜን ሸዋን የመራቤቴን የእምቢተኝነት መንፈስ መላው የአማራ ህዝብ ሊላበሰው ይገባል” ይለናል፡፡ ሌላው ደግሞ “ከወያኔ … Continue reading የሰሞኑ የመርሃ-ቤቴ ዓለም-ከተማ የሁከት ሙከራና እውነታው

የትግራይ ክልል ሰንደቅ አላማና የተቃዋሚዎች ፖለቲካ

የግንቦት 7 አሸባሪ ቡድን ዋና ፀሃፊ የነበረው አንዳርጋቸው ፅጌ በኢትዮጵያ የደህንነት ሃይሎች ቁጥጥር ስር መዋሉ በአገርውስጥም በውጭም ያሉ ደጋፊዎቹን ሲበዛ አበሳጭቷቸዋል፡፡ ይህ በኢትዮጵያ ሕግ በተደጋጋሚ ወንጀለኛ ተብሎየተፈረደበትና በፓርላማውም ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀ ድርጅት አመራር ልክ እንደ ነፃነት ታጋይ ተቆጥሮ “አንዳርጋቸውይፈታ” እየተባለለት በአንዳንድ የውጭ አገር ከተሞችም ሰልፍ እየተወጣለት ነው፡፡ በስዊዘርላንድ ከተማ በተካሄደውሰልፍ ላይ ታዲያ ሰልፈኞቹ የትግራይ ብሔራዊ … Continue reading የትግራይ ክልል ሰንደቅ አላማና የተቃዋሚዎች ፖለቲካ

ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ በፓርላማ ተገኝተው ማብራሪያ የሰጡባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች

የኢፌዴሪ 4ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ ባካሂደው ስብሰባ በፌዴራል መንግስት የ2007 ረቂቅ በጀት ላይ ዝርዝር ውይይት በማካሄድ የበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ረቂቅ በጀቱን አስመልከቶ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ የበጀት አዋጁን አፅድቋል፡፡ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በጀቱን በተመለከተና ከም/ቤቱ አባላት ለሚነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ ከሰጡባቸው ጉዳዮች ውስጥ፤ የ2007 … Continue reading ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ በፓርላማ ተገኝተው ማብራሪያ የሰጡባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች

የግብፅ ‘ክስ’ – ቂም ነው ትርፉ!

ግብፅ <ከኢትዮጵያ ጋር ያለኝን አለመግባባት ወደ አለም አቀፍ ገላጋዮች እወስደዋለሁ> ስትል እንደፎከረችው አሁን ተግባራዊ ለማድረግ ጫፍ ላይ የደረሰች ትመስላለች፡፡ በሙባረክ ዘመነ ስልጣን የህግና ፓርላማ ጉዳዮች ሚኒስትር የነበሩትና የአረብ ሊግን ዋና ፀሃፊነት ስልጣን ከአሚር ሙሳ እንዲረከቡ በሙባረክ እጩ ሆነው ተመርጠው የነበሩት ሙፊድ ሼሃብ <<የህዳሴውን ግድብ ጉዳይ ለአለም አቀፍ አካል ለማቅረብ የሚያስችለኝን ሁሉን አቀፍ ጥናት አጠናቅቄ ለፕሬዝዳንቱ … Continue reading የግብፅ ‘ክስ’ – ቂም ነው ትርፉ!

ኢቴቪ የአልጀዚራን ግብፃዊ ፕሮፓጋንዳ ሲያስተጋባ

በኳታር መንግስት ሃብት የተቋቋመውና ስነ አፈጣጠሩ ሲጠናም የምዕራቡን አለምና የእስራኤል ሚዲያን የአረብ ሀገራት ጉዳይ አዘጋገብ ለመገዳደር የተፈጠረው የአልጀዚራ ቴሌቪዥን ጣቢያ ስትራግል ኦቨር ናይል በሚል ርዕስ አንድ ዘጋቢ ፊልም አዘጋጅቶ ነበር። ጣቢያው ይህን ፊልም በቴሌቪዥኑ ያስተላለፈው ሲሆን በድረ ገፁ ላይ ስለጫነውም በርካቶች ተመልክተውታል። የዘጋቢ ፊልሙ ይዘት በናይል ወንዝ የተነሳ በላይኛውና በታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት መካከል ስለነገሰ ውጥረት … Continue reading ኢቴቪ የአልጀዚራን ግብፃዊ ፕሮፓጋንዳ ሲያስተጋባ

ኦሮሞ የUN አባል አይደለም እንዴ? ትግራይስ፤ ወላይታስ?

(ከበደ ካሣ) ከሰሞኑ የፌስ ቡክ ጓደኛችን እንደርታ መስፍን <የሀገር ፍቅር> በሚል ርዕስ መጣጥፍ አቅርቦ ነበር፡፡ እኔም ፅሁፉን ስለወደድኩት ሼር አደረግሁት፡፡ ታዲያ የፌስቡክ አለምን ከተቀላቀለ 5 አመት ከ4 ወር ቢሆነውም እስካሁን <ለአቅመ ሼርንና ፖስትን ልየታ> ያልደረሰ አንድ ፀሃፊ /ግርማ ካሳ ይባላል/ ፀሃፊው እኔ መስዬው እንዲህ ሲል ትችቱን ጀመረ፡፡ <<ከበደ ካሳ የሚባሉ አፍቃሪ ኢሕአዴግ ግለሰብ “አንዳንድ ሰዎች … Continue reading ኦሮሞ የUN አባል አይደለም እንዴ? ትግራይስ፤ ወላይታስ?