All posts by Fetsum Berhane

Fetsum Berhane is an Ethiopian resident, economist researcher and a blogger on HornAffairs.

ወገን ተከበናል?

የኦባማ ቅልስልስ አስተዳደር ከኢራን ጋር ያደረገው ስምምነት የብዙ አረብ አገራትን ቀልብ የገፈፈ ነበር። በዚህም የተነሳ ረስተውት የቆዩትን ጦራቸውን ማጠናከር እና በጓደኛ ብዛት መፎካከሩን ተያይዘውታል። ብዙዎቹ (ሚጢጢዎቹ) ሀገራት ሳይቀሩ ጦራቸውን አፍሪካ ላይ ማስፈር አሜሪካ አሜሪካ መጫወት ጀምረዋል። ለዚህ ደግሞ ዋናው የትርኢቱ መድረክ ለመካከለኛው ምስራቅ ስትራቴጂካዊ ትርጉም ያለው ምስራቅ አፍሪካ ነው። ጅቡቲ ከፈረንሳይ ነፃ ወጥታ የማታውቀው ጅቡቲ … Continue reading ወገን ተከበናል?

ሕዝብ በእንጀራ ብቻ አይኖርም – በርዕዮተ ዓለም ጭምር እንጂ

አብዮታዊው ኢህአዴግ – ኢትዮጲያን በልል ፌዴራሊዝም (loose federalism) መንፈስ በተቀመረ ህገመንግስት አዲስ ስርአት የመሰረተ እና የመራ፤ ጠንካራ እና የጠራ ርዕዮተ ዓለም እና አባላት የነበረው፤ በዘረጋው ያልተማከለ የፌዴራል ስርአት የተነሳ አገር ሊበታትን እንደሆነ ይታማ የነበረ እና በብሄረተኞችና በግራ ዘመም የብዝኀነት (diversity) ኀይሎች የሚታመን ነበር፡፡ ድኅረ 97 ኢህአዴግ – በይደር ያቆያቸውን ህገመንግስታዊ ድንጋጌዎችን በቅድሚያ ሳይመልስ የመናገሻ ከተማ … Continue reading ሕዝብ በእንጀራ ብቻ አይኖርም – በርዕዮተ ዓለም ጭምር እንጂ

ም/ጠ/ሚ ደብረጺዮን – የብሔር የበላይነት ስለሚባለውና በጎንደር ስለተከሰተው መፈናቀል [Video]

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የኢኮኖሚና ፋይናንስ ክላስተር አስተባባሪ ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ባለፈው አርብ ነሐሴ 27/2008 ለኦንላይን ሚዲያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በጋዜጣዊ መግለጫው ከዳሰሷቸው በርካታ ጉዳዮች መሀል፡- * በጎንደር መተማ-ዮሐንስ አካባቢ ስለተከሰተው መፈናቀል እና ስለአካባቢው ፀጥታ * ‹‹የአንድ ብሔር የበላይነት›› የሚባለውን አስመልከቶ የሰጡትን ማብራሪያዎች ቪዲዮ እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡ (ለድምጽ ጥራት ችግር ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡) —— Watch the video *************

Video | የመንግሥት ቃለ-አቀባይ ጋዜጣዊ መግለጫ

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ:- ከኤርትራ ጋር ስለነበረው ግጭት፣ ከአልሸባብ ጋር ስለነበረው ውጊያ፣ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ፕሮግራም እንደገና ስለመራዘሙ፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ስለኦሮሚያና ቅማንት ስላቀረበው ሪፖርት እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፡፡ ቪድዮውን ይመልከቱ፡፡ ***************

የH1N1 ኢንፍሉዌንዛ ቫይረስ በአዲስ አበባ አራት ለሞት ዳረገ

የH1N1 ኢንፍሉዌንዛ ቫይረስ በአዲስ አበባ ያለውን ቀዝቃዛ አየር ተከትሎ መከሰቱን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በተለምዶ የአሳማ ጉንፋን በሚባለው የኢንፍሉዌንዛ ቫይረስ እስካሁን 32 ተጠቂዎች የተገኙ ሲሆን አራቱ ለሞት ተዳርገዋል፡፡ የኢፌዴሪ የጤና ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጠ ሲሆን በመግለጫው ላይ አቶ አህመድ ኢማኖ ፡ ዶ/ር ዳዲ ጂማ እና ዶ/ር መራዊ አራጋው በH1N1 ኢንፍሉዌንዛ ክስተት እና የመከላከል … Continue reading የH1N1 ኢንፍሉዌንዛ ቫይረስ በአዲስ አበባ አራት ለሞት ዳረገ

ጃዋርና የብሔር ግጭት ኢንጂነሪንግ

በአለም ላይ (በተለይም በአፍሪካ) የሚከሰቱ ግጭቶችን እንደ ወቅታዊ ክስተት በዜና ከመከታተል ባለፈ ጠለቅ ያለ የታሪክ ጥናት ያከሄደ ሰው አንድ ተመሳሳይ ሂደትን ማስተዋሉ አይቀርም፡፡ ይህም ሂደት ሁሉም የብሔር (የዘር) ግጭቶች ከፋ ደረጃ ከመድረሳቸው በፊት ጥቂት ልሂቃን ሆን ብለው ባቀናበሯቸው ደረጃዎች (steps) ውስጥ ማለፋቸው ነው፡፡ እነኝህ የጥላቻ/ግጭት መፍጠሪያ ደረጃዎች ከሞላ ጎደል በሁሉም ግጭቶች ውስጥ የሚተገበሩ ሲሆን የቆየ … Continue reading ጃዋርና የብሔር ግጭት ኢንጂነሪንግ

[Audio] ሚ/ር ጌታቸው ረዳ:- በተቃውሞና በሁከት የተሳተፉ ሁሉ በውጭ ሀይሎች ተገፍተው የገቡ ናቸው ማለት አይቻልም።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ ዛሬ ከሰዓት በኋላ የሰጡት ፕሬስ ኮንፈረንስ የድምጽ ቅጂ አትመናል፡፡ በፕሬስ ኮንፍረንሱ ወቅት በሰሞኑ በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሸዋ እና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞኖች እንዲሁም በአማራ ክልል አካባቢ ስላለው ሁኔታ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፤ በኦሮሚያ ክልል ያለውን ሁኔታ አስመልክቶ ከተናገሯቸው ነጥቦች ጥቂቱን እነሆ፡- *በተቃውሞና ተከትሎ በመጣው ሁከት የተሳተፉ ሁሉ በውጭ ሀይሎች ተገፍተው … Continue reading [Audio] ሚ/ር ጌታቸው ረዳ:- በተቃውሞና በሁከት የተሳተፉ ሁሉ በውጭ ሀይሎች ተገፍተው የገቡ ናቸው ማለት አይቻልም።

የምርጫ 2007 የህዝብ ተወካዮችና የክልል ምክር ቤቶች ጊዜያዊ ዉጤት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ግንቦት 19/2007 የ5ኛውን አገራዊ ምርጫ ጊዜያዊ ዉጤት ገለፀ፡፡ የመጨረሻዉ ዉጤት ሰኔ 15/2007 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሚገለጽ መሆኑን እንደተጠበቀ ሆኖ ጊዜያዊ የምርጫው ዉጤት ‹‹እስካሁን በደረሰን ሪፖርት መሰረት ብቻ›› በማለት ቦርዱ ገልጿል፡፡ በቦርዱ ዛሬ የተገለፀው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የክልል ምክር ቤቶች ግዜያዊ ውጤት እንደሚከተለው ነው፡፡ 1. የህዝብ ተወካዮች ምክር … Continue reading የምርጫ 2007 የህዝብ ተወካዮችና የክልል ምክር ቤቶች ጊዜያዊ ዉጤት

ነውጠኛ ሄሊኮፕተር ያደመቀው በዐል (+video)

ዕለቱ 9ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን እና የሕገ-መንግስታችን 20ኛ የልደት በዓል የሚከበርበት ህዳር 29፤ ቦታው ደግሞ ለዚሁ በዓል ተብሎ በፍጥነት እንዲደርስ የተደረገው የአሶሳ ከተማ ስቴድየም ነው፡፡ የኢ.ፌ.ድሪ ጠቅላላ ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ፣ የፌደሬሽን እና የሕዝብ ተወካዮችን ምክር ቤቶች አፈ ጉባኤዎች፣የጎረቤት ሀገራት መሪዎች፣ ሚኒስቴሮች፣ የውጭና የሀገር ውስጥ ጋዜጠኞች፣ የሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች የባህል ቡድኖች…ብቻ ምን አለፋችሁ ኢትዮጵያ … Continue reading ነውጠኛ ሄሊኮፕተር ያደመቀው በዐል (+video)

ፕ/ት ሙላቱ:- አንዳርጋቸው ‹ይቅርታ› ከጠየቀ በሕገ-መንግስቱ መሰረት ይስተናገዳል

ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ ዛሬ ጳጉሜ 5፣ 2006 በብሄራዊ ቤተ መንግስት ለመላው የኢትዮጽያ ብሔር/ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መልእክት አዲሱ አመት የጤና፤ የደስታና የብልጽግና እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ ብለዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ አዲሱ አመት የመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ማብቂያና የሁለተኛው ዘመን እቅድ ለመጀመር ከፍተኛ ዝግጅት የሚደረግበት ወሳኝ ምዕራፍ ነው ያሉ ሲሆን ሃገሪቱ በሁሉም ዘርፍ የደረሰችበትን የለውጥ ጎዳና ለማስቀጠልና የተገኘውን … Continue reading ፕ/ት ሙላቱ:- አንዳርጋቸው ‹ይቅርታ› ከጠየቀ በሕገ-መንግስቱ መሰረት ይስተናገዳል