All posts by Daniel Berhane

Daniel Berhane

በኢትዮጵያ ኢምባሲ ላይ የተፈጠረውን ሁከት የሚያወግዝ ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲ ተካሄደ

በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ላይ የተፈጠረውን ሁከት የሚያወግዝ ሰልፍ እዚያው ከተማ ተካሄደ፡፡ ባለፈው ሳምንት ሰኞ ጥቂት የዳያስፖራ ተቃዋሚዎች የኢትዮጵያ ኤምባሲ በመግባት፣ “አምባሳደሩን እንፈልገዋለን” ሌባ ባንዳ ወዘተ በማለት ረብሻ ከማስነሳታቸው በተጨማሪ የኢትዮጲያን ባንዲራ በማውረድ እና አንድ የኤምባሲውን ቢሮ ለተወሰኑ ደቂቃዎች በመያዝ ከፍተኛ ግርግር መፈጠሩ ይታወሳል፡፡ ግለሰቦቹን ለመከላከል የሞከረ አንድ ዲፕሎማት ጥይት መተኮሱ እና ለጥቆም ወደሀገር ቤት … Continue reading በኢትዮጵያ ኢምባሲ ላይ የተፈጠረውን ሁከት የሚያወግዝ ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲ ተካሄደ

ማዕተብም መስቀልም በግለሰቦች ነፃነት ውስጥ የሚካተት ነው – ዶ/ር ሺፈራው ተክለማርያም

ማዕተብ ማሠር ይከለከላል የሚለው ወሬ መሠረተ-ቢስ ነው በማለት የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ሺፈራው ተክለማርያም አስተባበሉ፡፡ ሐራ ዘተዋሕዶ የተሰኘ ሃይማኖት-ተኮር ብሎግ ባለፈው ቅዳሜ፤ ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ በተካሔደ የፖሊሲና ስትራተጂ ሥልጠና ላይ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዕምነት ተከታዮች በአንገታቸው ላይ የሚያሥሩት ማዕተብ ወደፊት እንደሚከለከል ተናግረዋል የሚል ይዘት ያለው ዜና ካተመ በኋላ ርዕሰ-ጉዳዩ በተለያዩ ድረገጾች እና … Continue reading ማዕተብም መስቀልም በግለሰቦች ነፃነት ውስጥ የሚካተት ነው – ዶ/ር ሺፈራው ተክለማርያም

በ5 ዋነኛ መጽሔቶች እና አንድ ጋዜጣ ላይ የወንጀል ክስ ተመሠረተ

በስድስት የግል ፕሬስ ሕትመቶች እና አሳታሚዎቻቸው ላይ የወንጀል ክስ መመሥረቱን መንግስት አስታወቀ፡፡ ክስ የተመሠረተባቸው አምስት መጽሔቶች እና አንድ ጋዜጣ፤ በየጊዜው ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል ለመናድ የአመፅ ቅስቀሳና የሀሰት ወሬዎችን በመንዛት ህገ መንግስታዊ ስርዓቱ በሀይል እንዲፈረስ እና ህዝብ በመንግስት ላይ ያለአግባብ አመኔታ እንዲያጣ የሚያደርጉ የወንጀል ተግባራትን በመፈፀም እንደተጠረጠሩ የፍትህ ሚኒስቴር መግለጫ ጠቁሟል፡፡ መግለጫው አክሎ … Continue reading በ5 ዋነኛ መጽሔቶች እና አንድ ጋዜጣ ላይ የወንጀል ክስ ተመሠረተ

የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የጋራ ልማት ፕላን “ማስተር ፕላን” (2006-2030) [full text]

ለዓመታት ሲጠና ነበር የተባለለት ‹‹ማስተር ፕላን›› ወይም ‹‹የአዲስ አበባና ዙሪያዋ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ልማት ፕላን›› በቅርቡ ከፍተኛ ውዝግብ ማስነሳቱ እና ለተቃውሞ እንቅስቃሴዎች እና ብጥብጥ መነሻ ሆኖ የህይወትና ንብረት ጥፋት ማስከተሉ ይታወሳል፡፡ የፖለቲካ ውጥረቱ ረገብ ያለ ቢሆንም ገና ያልተቋጨ እና የዕቅዱም ዕጣ-ፈንታ ያልለየለት ስለሚመስል፤ እንዲሁም ለተመራማሪዎች እና ተንታኞች ሊጠቅም ስለሚችል ሰነዱን አትመነዋል፡፡ [የሰነዱን ገጾች … Continue reading የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የጋራ ልማት ፕላን “ማስተር ፕላን” (2006-2030) [full text]

ሰማያዊ ፓርቲ የአንዳርጋቸው ፅጌን እና የተቃዋሚ አመራሮችን መያዝ ተቃወመ [+የመግለጫው ሙሉ ቃል]

ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፤ በቅርቡ በየመን መንግስት ተይዘው ለኢትዮጲያ ተላልፈው የተሰጡትን የግንቦት-7 ሰባት ዋና ፀሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጉዳይ፤ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችንና ድንጋጌዎችን የጣሰና በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት ነው ሲል የየመንን መንግስት የኮነነ ሲሆን፤ አክሎም ክስተቱ ‹‹በሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት ላይ ከፍተኛ ጥላ የሚያጠላ›› ነው ብሎታል፡፡ መግለጫው ግንቦት 7ን ‹‹አማፂ ቡድን›› ብሎ የጠራው ቢሆንም፤ መለስ … Continue reading ሰማያዊ ፓርቲ የአንዳርጋቸው ፅጌን እና የተቃዋሚ አመራሮችን መያዝ ተቃወመ [+የመግለጫው ሙሉ ቃል]

ETV | የግንቦት 7ቱ አንዳርጋቸው ፅጌ በየመን ተይዞ ለኢትዮጵያ ተላልፎ ተሰጥቷል

በሸብር ወንጀል ተከሶ በተደጋጋሚ የተፈረደበትና በኢትዮጵያ መንግስት በጥብቅ ሲፈለግ የነበረው የግንቦት 7 አሸባሪ ድርጅት አመራር የሆነው አንዳርጋቸው ፅጌ በቁጥጥር ስር መዋሉን የብሔራዊ የመረጃና የደሀንነት አገልግሎት እና የፌዴራል ፖሊስ የጋራ ፀረ ሽብር ግብረ ሀይል አስታወቀ፡፡ በየመን እና በኢትዮጵያ የመረጃና ደህንነት ተቋማት ማዕከል በፀረ ሽበር ትግሉ ተቀናጅተው ለመስራት በተደረሰው ስምምነት ሁለቱም ተቋማት አሽከባሪዎችን በመያዝና በመለዋወጥ በጋራ እንደሚሰሩ … Continue reading ETV | የግንቦት 7ቱ አንዳርጋቸው ፅጌ በየመን ተይዞ ለኢትዮጵያ ተላልፎ ተሰጥቷል

ሰማያዊ ፓርቲ፡- የአንድነት አመራሮች ‘በእናንተ ምክንያት መታሰር አንፈልግም ሂዱ’ አሉን

አቶ ዳዊት አስራደ የሚባል የአንድነት ስራ አስፈፃሚ “አንድ ሰው የኢሕአዲግ ቲሸርት አድርጎ ቢመጣ ታባርረዋለህ ወይ?” ብለን ስንጠይቀው፤ “አላባርረውም፤ እንደውም እፈልገዋለሁ” አለን፡፡“ታዲያ ሰማያዊ ፓርቲ ቲሸርት አድርጎ ሲመጣ ለምንድነው የምታባርሩት” ተብሎ ሲጠየቅ፤ “ሰማያዊ ፓርቲ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች እውቅና አልሰጠም ‘የሉም ‘ብሎ ነው የሚያምነው፡፡ ኢህአዴግ ቢያንስ ሰርተፊኬት ሰጥቷል…” አለ፡፡ ቃል በቃል ያለው ይሄንን ነው፡፡ ሀብታሙ አያሌው ‹‹ከኢሕአዴግ ለቀቅኩ›› የሚለው … Continue reading ሰማያዊ ፓርቲ፡- የአንድነት አመራሮች ‘በእናንተ ምክንያት መታሰር አንፈልግም ሂዱ’ አሉን

አንድነት ፓርቲ፡- ሰማያዊ ፓርቲ የልጆች ክበብ ነው-በሰልፋቸው 114 ሰው አልተገኘም

ሰማያዊ ፓርቲ 114 አባላት አሉት ወይ የሚለው ላይ ጥርጣሬ አለኝ፡፡ ፓርቲ አይደለም እኮ! ትናንሽ ልጆች የተሰበሰቡት ክበብ ነው፡፡ ፖለቲካ ማለት ፌስቡክ ላይ ሄደህ መለጠፍ አይደለም፡፡ የሆኑ ሰዎች ስማቸውን ሳይናገሩ ምስላችውን የአንበሳ ወይም የነብር አድርገው ይለጥፉና ዘራፍ ሊሉ ይችላሉ፡፡ ባለፈው ወር አንድነት ፓርቲ ባዘጋጀው ሰልፍ ላይ ለመሳተፍ የሄዱ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት፣ በአንድነት ፓርቲ አመራሮች ተከልክለው ተመለሱ … Continue reading አንድነት ፓርቲ፡- ሰማያዊ ፓርቲ የልጆች ክበብ ነው-በሰልፋቸው 114 ሰው አልተገኘም

Video | “ሶሻል ሚዲያና የፕሬስ ነፃነት” – በዳንኤል ብርሃነ

ዓለም ዐቀፍ የፕሬስ ቀንን በማስመልከት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት ሚያዝያ 25/2006 በግዮን ሆቴል በተካሄደው ስብሰባ ላይ፤ ‹‹ሶሻል ሚዲያና የፕሬስ ነፃነት›› በሚል ርዕስ ዳንኤል ብርሃነ ያቀረበው ገለፃ፡፡ ******** ******** *የሆርን አፌይርስ ታዳሚዎች የአብዝሀው ፍላጎት ከሆነ – የተሻለ ጥራት ያለው ቪዲዮ በመፈለግ ወይም/እና በጽሑፍ ልናቀርብ እንችላለን፡፡ [በዚሁ አጋጣሚ ለመግለጽ የምንወደው፡- ባለፉት ዓመታት የሆርን አፌይርስ ፀሐፊዎች የተገኙባቸውን እና … Continue reading Video | “ሶሻል ሚዲያና የፕሬስ ነፃነት” – በዳንኤል ብርሃነ

ቃለ-መጠይቅ| ከኢትዮጲያዊ ጌይ እና የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ተከራካሪ ሮቤል ሀይሉ ጋር

– በአንድ ወይም በሌላ ምክንያት – ሰሞኑን የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ወይንም ጌይ(gay) ግለሰቦች ጉዳይ አጀንዳ ሆኗል፡፡ በጉዳዩ ላይ ከሁለቱም ወገን ያለውን አመለካከት እኩል ለማቅረብ የነበረን ዕቅድ አልተሳካም፡፡ መንግሰት በጌዮች ላይ ጠንካራ እርምጃ መውሰድ እንዳለበት ከሚወተውቱት ከዶ/ር ስዩም አንቶኒዮስ ጋር ያቀድነው ቃለ-መጠይቅ እሳቸው ለአንድ ሳምንት ከሀገር ውጭ በመሆናቸው ሊዘገይ ችሏል፡፡ ስለሆነም እንደተመለሱ በቪዲዮ የተደገፈ ቃለ-መጠይቅ የምናቀርብ … Continue reading ቃለ-መጠይቅ| ከኢትዮጲያዊ ጌይ እና የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ተከራካሪ ሮቤል ሀይሉ ጋር