All posts by Guest Author

Guest Author

አገራችን ኢትዮጵያ ያጠላባት አደጋና ስለ መውጫዋ አቅጣጫዎች

(በላይ ደርሸም) አጠቃላይ አገራችን ኢትዮጵያ ግዙፍ ፈተና ተደቅኖባታል፤ ዜጎችዋ ግዙፍ ፈተና ተደቅኖብናል፡፡ ከዚህ ፈተና ልንወጣ የምንችለው በራሳችን ጥረትና ብልህነት ብቻ ነው፡፡ እንባችንን ልናደርቅ የምንችለው እርስ በርሳችን ተመካክረን በምንደርስበት አግባቢ መንገድ ብቻ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ሁሉም በየራሱ ጉዳይ ተጠምዷል ወይም ቅድምያ የሚሰጣቸው ብሄራዊ ጥቅሞች አሉት፡፡ አጋር የሚባሉት ከጎናችን ይቆማሉ ወይም መፍትሄ እንዲመጣ ያደርጋሉ በሚል ተስፋና ስሌት … Continue reading አገራችን ኢትዮጵያ ያጠላባት አደጋና ስለ መውጫዋ አቅጣጫዎች

የህዳሴው ግድብ እና አለም አቀፍ ህግ

(በስንታየሁ ግርማ)  የአሜሪካው ሁቨር ግድብ እ.ኤ.አ በ1929 እና በ1930ዎቹ በአሜሪካ ተከስቶ የነበረው የኢኮኖሚ ድቀት ወቅት የተገነባ ግድብ ነው፡፡ ግድቡን ለመገንባት በ10000ዎች የሚቆጠሩ አሜሪካኖች የተሳተፉ ሲሆን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተሰውተዋል፡፡ ግድቡ ለኔቨዳ ለአርዞንያ እና ለካርፎርኒያ ወዘተ ምእራብ ግዛቶች ዋነኛ የሀይል እና የብልፅግና ምንጭ ሲሆን በየዓመቱ በሚሊዬን የሚቆጠሩ ቱሪስቶች መናኽሪያ በመሆን በአሜሪካ ብልፅግናም ከፍተኛ አስተዋፆኦ አድርጓል፡፡ በተለይም … Continue reading የህዳሴው ግድብ እና አለም አቀፍ ህግ

የኢትዮጵያ ልማት በዓለም አቀፍ ሚዲያ

(ስንታየሁ ግርማ) “የኢቫንካ ትራምፕ ጫማዎች ከቻይና ሥሪት ወደ ኢትዮጵያ ሥሪት እየተቀየሩ ነው ” – ኳርትዝ የተባለ ድረ-ገፅ፡፡ ኢቫንካ ትራምፕ የአሜሪካው ዕጩ ፕሬዚዳንት ተወዳዳሪ የዶናልድ ትራምፕ ልጅ ናት፡፡ ኢቫንካ በቻይና የተሠሩ ጫማዎች መሸጫ መደብር አሏት፡፡ ይሁንና የኢቫንካ ጫማ አቅራቢ ድርጅት የሆነው የቻይናው ሁጃን ፋብሪካ በዚህ ሣምንት ፋብሪካው መሠረቱን ከቻይና ጉልበት ርካሽ ወደ ሆነበት ኢትዮጵያ ለማድረግ መወሰኑን የፋብሪካው … Continue reading የኢትዮጵያ ልማት በዓለም አቀፍ ሚዲያ

ኒዬሊበራሊዝም ሊክደው ያልቻለ ልማት

(ስንታየሁ ግርማ) “እ.ኤ.አ በ2016 የአፍሪካ ኢኮኖሚ 3.7% ያድጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ምስራቅ አፍሪካ ከአህጉሩ ከፍተኛው እድገት ታስመዘግባለች፡፡ በተለይም ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ ከ2005 ጀምሮ ባለሁለት አሀዝ እድገት እያስመዘገበች ሲሆን በ2016 ዓ.ም እድገቱ ይቀጥላል፡፡ የእድገቱ ዋንኛ መሠረት ደግሞ ሰፊ የመንግስት ኢንቨስትመንት ነው፡፡ ምዕራብ አፍሪካም በበኩሏ የኢቦላማብቃት ይረዳታል፡፡ ነዳጅ ላኪ ሀገሮች ግን እድገታቸው ይገታል፡፡ ደ/አፍሪካ በድርቅ እና በሃይል እጥረት ምክንያት … Continue reading ኒዬሊበራሊዝም ሊክደው ያልቻለ ልማት

የኮንሶ ህዝብ ጥያቄ ተገቢዉን ምላሽ ይሻል !

(ኮሎኔል አስጨናቂ ገ/ጻዲቅ ሺፈራዉ) በቅድሚያ በኮንሶ ህዝብ ላይ እየደረሰ ሲላለዉ በደል አንዳችም ትርፍ  ነገር ሳይጨምር ሳይቀንስና ሳይደባብቅ ሃቁን ለህዝብና ለሚመለከታቸዉ የመንግስት ባለስልጣና አካላት ሁሉ እንዲደርስ ባደረገዉ በአቶ ናሁሰናይ በላይ የተሰማኝን ኩራትና አድናቆት ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡ ናሁሰናይ አስታዋሽ ያጣዉና ትኩረት የተነፈገዉ  የኮንሶ ህዝብ  ብቻ  ሳይሆን  ጭቆናንና በደልን የሚጸየፉ የመላዉ የሀገራችን ህዝቦች ሁሉ እንደሚያሰግኑህ ቅንጣት ጥርጥር የለኝም፡፡ ሆርን … Continue reading የኮንሶ ህዝብ ጥያቄ ተገቢዉን ምላሽ ይሻል !

የትግራይ ህዝብ የለውጡ አጋር እንጂ ተጠቂ ሊሆን ኣይገባም

(መርስዔ ኪዳን) ([email protected] – ሜኔሶታ፤ ሃገረ ኣሜሪካ) ሰሞኑን በሃገራችን ውስጥ እየተካሄደ ባለው ህዝባዊ አመፅ ምክኒያት ብዙ የሰው ህይወት፣ የአካል ጉዳትና የንብረት ውድመት እየደረሰ ነው። ይህ ሁኔታ እንዲፈጠር ያበቁ ብዙ ምክኒያቶች ቢኖሩትም አንዱና ዋነኛው ምክኒያት በሃገሪቱ ውስጥ ፍትሃዊ የሆነ የፖለቲካ ስርዓት አለመኖሩ ነው። ኢትዮጵያ ብዙ ብሄሮች ብቻ ሳይሆን ብዙ ፖለቲካዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አመለካከት ያለው ህዝብ የሚኖርባት አገር … Continue reading የትግራይ ህዝብ የለውጡ አጋር እንጂ ተጠቂ ሊሆን ኣይገባም

ለሀገሪቱም ለኢህአዴግም የሚበጀዉ ሀገር ወዳድ ምሁራንን ማዳመጡ ነዉ!

(ኮሎኔል አስጨናቂ ገ/ጻዲቅ ሺፈራዉ) መግቢያ በሃገራችን የተከሰተዉን አደገኛ ሁኔታ ስጋት የገባቸዉ ቅን የሆኑ ኢትዮጵያዉያን አገሪቱን ከአደጋ መታደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የበኩላቸዉን ምክረ ሃሳብ እያቀረቡ ባለበት ሰዓት አንዳችም ኃላፊነት የማይሰማቸዉ አንዳንድ ወገኖች ደግሞ አሁን ያለዉ ቀዉስ ተባብሶ  የበለጠ ምስቅልቅል ሁኔታ እንዲፈጠር ሆን ብለዉ መርዘኛ የሆነ ቀስቀሳ ከማድረግ አልተቆጠቡም:: መንግስት በሀገሪቱ የተከሰተዉ ሁኔታ አሳስቦት ራሱን በግልጽ ፈትሾና … Continue reading ለሀገሪቱም ለኢህአዴግም የሚበጀዉ ሀገር ወዳድ ምሁራንን ማዳመጡ ነዉ!

“አወቅሽ አወቅሽ ሲሏት…” (ለሜ/ጄኔራል አበበ ተ/ሃይማኖት ጽሑፍ የተሰጠ ምላሽ) (ክፍል 2)

(መሓሪ [email protected]) (ክፍል ሁለትና የመጨረሻው) ውድ አንባቢያን በክፍል አንድ ፅሑፌ ላይ “ጆቤ” በሰራዊቱ ግንባታ ሰነድ ላይ ያነሷቸውን ሃሳቦች ከተጨባጭ ሰነዱ ጋር በማመሳከር ነጥቦቹ ትክክል አለመሆናቸውን ለማሳየት ሞክሬያለሁ። ሰውዬው ለማንሳት የሞከሯቸው ሌሎች ጉዳዩችንም እንዲህ ተመልክቻቸዋለሁ። መልካም ንባብ።… ጡረተኛው ሜ/ጄኔራል ሰነዱን አስመልክተው ያነሷቸው ሃሳቦች ለእርሳቸው ፍጆታ በሚውል መልኩ ቀነጫጭበውና እውነት አስመስለው ለማቅረብ ሞክረዋል። ለዚህም “በእኛ ተጨባጭ ሁኔታ … Continue reading “አወቅሽ አወቅሽ ሲሏት…” (ለሜ/ጄኔራል አበበ ተ/ሃይማኖት ጽሑፍ የተሰጠ ምላሽ) (ክፍል 2)

“አወቅሽ አወቅሽ ሲሏት…” (ለሜ/ጄኔራል አበበ ተ/ሃይማኖት ጽሑፍ የተሰጠ ምላሽ)

(መሓሪ [email protected])  (ክፍል አንድ) የቀድሞው የአየር ኃይል አዛዥ የነበሩትና የዛሬ 15 ዓመት ገደማ ህወሓት (ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ) ውስጥ በአንድ በኩል በልማታዊ ዴሞክራሲ ኃይሎች፤ በሌላ በኩል ደግሞ በትምክህት፣ በጥበትና በኪራይ ሰብሳቢነት ጎራ መካከል በተካሄደው የሃሳብ ፍትጊያ ኪራይ ሰብሳቢነትን ከሚያቀነቅነው “አንጃ” ጋር ተሰልፈውና እንደ ሰራዊት አባል ለህገ-መንግስቱ ታማኝ ባለመሆናቸው ምክንያት ከስራቸው የተሰናበቱትን ግለሰብ አንድ ፅሑፍ እንደ … Continue reading “አወቅሽ አወቅሽ ሲሏት…” (ለሜ/ጄኔራል አበበ ተ/ሃይማኖት ጽሑፍ የተሰጠ ምላሽ)

ነጋድራስ ገብረሕይወት ባይከዳኝ ስለኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታዎች አሁንስ ምን ይሉ ነበር ይሆን?

(ሕሉፍ ሓጎስ [email protected]) መግቢያ ‹‹ታሪክን መማር ለሁሉ ሰው ይበጃል፤ ለቤተ መንግስት መኰንን ግን የግድ ያስፈለጋል››– ነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ በመጀመርያ የነጋድራስ ገብረ ሕወይት ባይከዳኝን ሥራዎች ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ጥረት ላደረጉ ለልጅ ልጃቸው ለወ/ሮ ዓይናለም አሸብር ገብረሕይወትና የሀገራችን ምሁራን በተለይም የታሪክ ምሁር ኤሜሪተስ ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ እና የስነ-ምጣኔ ምሁር ለኢኮኖሚስቱ ዶ/ር ዓለማየሁ ገዳ ታላቅ ምስጋናዮንና … Continue reading ነጋድራስ ገብረሕይወት ባይከዳኝ ስለኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታዎች አሁንስ ምን ይሉ ነበር ይሆን?