All posts by Guest Author

Guest Author

መከላከያ ሰራዊትን እንደተዋጊም እንደ ፖሊስም የመጠቀም አደገኛ ዝንባሌ

(አስጨናቂ ገ/ጻዲቅ ሺፈራዉ (ኮ/ል)) መቅድም በሀገራችን ተከስቶ በነበረዉ የጸጥታ ችግር በተያያዘ የህዝቡን ደህንነት ለመጠበቅ  ተሰማርቶ የነበረዉ መከላከያ ሰራዊታችን ከሌሎች የጸጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን አኩሪና አስመስጋኝ ተግባር ማከናወኑ ይታወቃል፡፡ መከላከያ የዜጎችን ይህንነት ለማስከበር ሃላፊነቱን በሚወጣበት ወቅት በዜጎች ላይ አላስፈላጊ የመብት ጥሰት  እንዳይደርስ  ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረጉም የሚያስመሰግነዉ ነዉ፡፡ መከላከያ ሰራዊቱ በዚህ ተግባር ባይሳተፍ ኖሮ በዜጎች ህይወትና ንብረት … Continue reading መከላከያ ሰራዊትን እንደተዋጊም እንደ ፖሊስም የመጠቀም አደገኛ ዝንባሌ

መንግስትን በእጅጉ የፈተነዉ ቀዉስና የተስተናገደበት አግባብ ሲፈተሽ

(አስጨናቂ ገ/ጻዲቅ ሺፈራዉ (ኮ/ል)) መግቢያ በሀገራችን ከጥቂት ወራት በፊት ተከስቶ ለነበረዉ ሁከት ዋነኛ መነሻ ምክንያት ህዝባዊ ቅሬታዎችን በአግባቡ ማስተናገድ አለመቻላችን እንደደሆነ ይታወቃል፡፡ የህዝቡን ብሶት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ህዝባዊ ቅሬታዉን ወደ አጠቃላይ ቀዉስ በመቀየር ረገድ ጸረ -ሰላም ኃይሎች የተጫወቱት አፍራሽ ሚና ክፍተኛ እንደነበርም የሚዘነጋ አይደለም፡፡ ተቃዉሞን በሰላማዊ መንገድ ማሰማት የዜጎች መብት ሆኖ እያለ መንግስት ይህን … Continue reading መንግስትን በእጅጉ የፈተነዉ ቀዉስና የተስተናገደበት አግባብ ሲፈተሽ

ጊዜው ያለፈበትና የከሸፈ የትግል ስልት (ታጋይ ካሕሳይ ቃሉ)

(ታጋይ ካሕሳይ ቃሉ) ከያዝነው ዓመት መጀመሪያ ጀምሮ በተከታታይ በአቶ እውነቱ ዘለቀ የተባሉ ፀሃፊ (የብአዴን ከፍተኛ አመራር እንደሆኑ እራሳቸው ያስተዋወቁ) በትግራይ ተወላጆችና መሪ ድርጅታቸው ህወሓት ላይ ያነጣጠሩ ፅሁፎች በተለያዩ ድረገፆች አውጥተዋል ብዙ ሰውም እንደሚያነባቸውና የተለያዩ ሃሳብ እንደሚያነሳ የታወቀ ነው፡፡ አንዳንዱ የተለመደ የትምክህት ሃይሎች የፈጠራ ወሬ ነው በማለት ችላ ብሎ የሚያልፈው፤ ሌላው ደግሞ ብአዴን እንደድርጅት ምን ነካው … Continue reading ጊዜው ያለፈበትና የከሸፈ የትግል ስልት (ታጋይ ካሕሳይ ቃሉ)

ቁርጠኛ የሆነ አመራርና ነጻ ሚዲያ በሌለበት ሙስናን መታገል ከቶ አይቻልም

(አስጨናቂ ገ/ጻዲቅ ሺፈራዉ (ኮ/ል)) በሀገራችን በየጊዘዉ ለሚከሰቱ ችግሮች ሁሉ በቀላሉ ተጋላጭ ለመሆን የተገደድነዉ ተአማኒነት ያለዉ አማራጭ ነጻ መረጃ ምንጭ እጦትና ቁርጠኛ የሆነ አመራር አለመኖር ነዉ፡፡ ዋስትናዉ የተጠበቀ የመረጃ ተደራሽነት መኖር ለአንድ ህዝብ እጅግ ጠቃሚ ነዉ፡፡ ዜጎች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ በነጻነት የመወያየት፤ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ፤ ነጻ በሆኑ ሚዲያዎችን ተጠቅመዉ ያለመሸማቀቅ መንግስትን የመተቸትና አስፈላጊ ሆኖ ባገኙ … Continue reading ቁርጠኛ የሆነ አመራርና ነጻ ሚዲያ በሌለበት ሙስናን መታገል ከቶ አይቻልም

ዶናልድ ትራምፕ አፍሪካን ወደ ዳር ሊተዏት ይችላሉ?

(ስንታየሁ ግርማ) የተጋነነ ቢመስልም ፖለቲከኞች በየትኛውም ዓለም ተመሳሳይ ናቸው የሚል አባባል አለ፡፡ በተለይ በምርጫ ወቅት “ወንዝ በሌለበት ድልድይ” ለመገንባት ቃል ይገባሉ፡፡ ዶናልድ ትራምፕ በምርጫ ወቅት አስገራሚ እና አነጋጋሪ ንግግሮች አድርገዋል፡፡ እንደመገናኛ ብዙሃን ዘገባ ከሆነ በመጀመሪያ ተናግረዋቸዋል የተባሉት ንግግሮች መካከል አንዳንዶቹ በአግባቡ እንዳልቀረቡ እራሳቸው ትራምፕ ተናግረዋል፡፡ በምርጫ ወቅት ተናገሯቸው የተባሉት ንግግሮች ደግሞ ሙሉ በሙሉ ይተገበራሉ ማለት … Continue reading ዶናልድ ትራምፕ አፍሪካን ወደ ዳር ሊተዏት ይችላሉ?

የህዝብ አመኔታን እያተረፈለት የመጣዉ የኢህአዴግ ጥልቅ ተሃድሶ

(አስጨናቂ ገ/ጻዲቅ ሺፈራዉ (ኮ/ል)) ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በሀገራችን እጅግ አስፈሪ በሆነ ሁኔታ ከዳር አስከ ዳር አዳርሶ ከነበረዉ ቀዉስ በመንግስት ትእግስት የተሞላበት አመራር ሰጭነት ወደ ቀልባችን ከተመለስን በኋላ ገዥዉ ፓርቲና መንግስት “ጥልቅ መታደስ ” በሚል የለዉጥና የመታደስ ሂዴት ዉስጥ እንገኛለን፡፡ በከፍተኛ መነሳሳትና የቁጭት ስሜት የተጀመረዉ ይህ የለዉጥና የመታደስ እርምጃ ለዉጤት እንደሚበቃ ቅንጣት ጥርጣሬ የለኝም፡፡ ለዉጡ በመንግስትና … Continue reading የህዝብ አመኔታን እያተረፈለት የመጣዉ የኢህአዴግ ጥልቅ ተሃድሶ

የትግራይ ህዝብና መሪ ድርጅቱ ህወሓት ላይ ያነጣጠረ መሰረተ ቢስ ውንጀላ እስከ መቸ?

(ታጋይ ካሕሳይ ቃሉ) በዚሁ ወር መጀመሪያ ሳምንት በትግራይ ኦንሊይን (Tigray online) ድረ-ገፅ ላይ በአቶ እውነቱ ዘለቀ የተባሉ ፀሃፊ “ያን ያህል ወጥ መርገጥ ምን የሚሉት ድፍረት ነው”[PDF] በሚል ርእስና ቀደም ብሎ በእንግሊዝኛ ቋንቋ “Gedu Andargachew; A fifth column on the loose” በሚል ርእስ በአቶ ብርሀነ ካሕሳይ ተፅፎ ለተዘረጋው ፅሁፍ መልስ ለመስጠት ታስቦ የወጣውን ፅሁፍ ተመለከትኩ፡፡ የፅሁፉ መነሻ … Continue reading የትግራይ ህዝብና መሪ ድርጅቱ ህወሓት ላይ ያነጣጠረ መሰረተ ቢስ ውንጀላ እስከ መቸ?

በኤርትራ ላይ የተጣለው የጦር መሳሪያ ማዕቀብ መራዘም እና ለቀጠናው ያለው የሰላም አንድምታ

(Yohannes Gebeyehu) እ.ኤ.አ. ሜይ 2009 የምስራቅ አፍሪካ በይነ-መንግስታት (ኢጋድ) በኤርትራ የጣለውን የጦር መሳሪያ ማዕቀብ ተከትሎ በተመድ የጸጥታው ምክር ቤት በዛው ዓመት ዲሴምበር 23 ቀን በውሳኔ ቁጥር 1907 አማካይነት የጦር መሳሪያ ማዕቀብ በኤርትራ ላይ ጣለ። ማዕቀቡ ወደ ኤርትራ የሚገቡ እና ከኤርትራ የሚወጡ የጦር መሳሪያዎችን እና ከጦር መሳሪያ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ቁሳቁሶችን የሚያግድ ውሳኔ ነው። ውሳኔው በተመድ … Continue reading በኤርትራ ላይ የተጣለው የጦር መሳሪያ ማዕቀብ መራዘም እና ለቀጠናው ያለው የሰላም አንድምታ

በመከላከያ ሰራዊታችን የፖርቲ ፖለቲካ ገለልተኝነትና ተያያዥ ጉዳዮች [ክፍል 2]

(ኮ/ል አስጨናቂ ገ/ጻዲቅ ሽፈራው) (የዚህን ጽሑፍ የመጀመሪያ ክፍል ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ) 9/ በሰራዊቱ ዉስጥ ገለልተኝነትን የሚሸረሽርና ለኢህአዴግ የወገነ አሰራር አልነበረም፡፡ የመከላከያ ሰራዊት ግንባታ ሰነዱ የሰራዊቱን ገለልተኝነት የሚሸረሽር ስለመሆኑ በሰራዊት ግንባታ ሰነዱ ላይ ዉይይት በተደረገባቸዉ ጊዜያትም ሆነ  ከዚያ  በኋላ በሰራዊቱ ዉስጥ አንድም ጊዜ ቅሬታ ሲቀርብ  አልሰማሁም፡፡ በሰራዊቱ ዉስጥ በነበርኩበት ወቅት በመመሪያዉ ላይም ሆነ በአፈጻጸም ረገድ … Continue reading በመከላከያ ሰራዊታችን የፖርቲ ፖለቲካ ገለልተኝነትና ተያያዥ ጉዳዮች [ክፍል 2]

ሃገር ሲታመም ትውልድ ምን ያደርጋል?

(ዳግማዊ ተስፋዬ) የኤርትራው ኢሳያስ አፈወርቂ ኤርትራን ለቀው በገፍ ስለሚወጡት/ስለሚሰደዱት ወጣት ኤርትራውያን ሲጠየቁ እንዲህ ብለው መለሱ : “እነዚህ ወጣቶች በተለያዩ ሃይሎች ና በምእራባዊያን ብልጭልጭ ተታለው የሚሰደዱ ቢሆኑም የትም ሆነው ኤርትራን የሚወዱና የሚረዱ ናቸውና ችግር የለዉም”! ወዲ አፎም ይህን ባሉ ከጥቂት አመታት በህዋላ ከወደ አዲሳባ አንድ ግምገማ ስለ እኔ ትውልድ ተሰነዘረ: ይህ ትውልድ ሃገር ወዳድ አይደለም የሚል! … Continue reading ሃገር ሲታመም ትውልድ ምን ያደርጋል?