All posts by Addisu Chekol

አዲስ ከድሬዳዋ - Frm. journalist; currently communicator

የኦሮሚያ ጉዳይ ያሳስበናል!

ሰሞኑን በኦሮሚያ ከተሞች የተካሔዱ ተቃውሞዎች ብዙ ነገሮችን እንድናስብ ያደረጉ ነበሩ፡፡ እንቅስቃሴው የብዙ እናቶችን ቅስም የሰበረ እና እንባ ያራጨ፣ ከምርጫ 97 ወዲህ (በላይ) ለመጀመሪያ ጊዜ መንግስትን ያስደነገጠ፣ በሽኩቻ ይታወቁ የነበሩት የአማራና ኦሮሞ ኤሊቶች ተስማምተው የታዩበት፣ . . . . .ወዘተ ነበር፡፡ ይህ በብዙዎቻችን አዕምሮ ውስጥ በርካታ ሐሳቦችን ያመላለሰው ክስተት እኔ ከምንም በላይ ያየሁት መንግስትም ሆነ ተቃዋሚ … Continue reading የኦሮሚያ ጉዳይ ያሳስበናል!

ሚዲያዎቻችን በህዝብ ዘንድ መታመንን ያስቀድሙ – ሌላው ይከተላል!!

እዚህ ድሬዳዋ በአቶ ሬድዋን ሁሴን እና አቶ ሽመልስ ከማል መሪነት እየተካሄደ ባለው ሀገር አቀፍ የኮሚዩኒኬሽን ፎረም የመጀመሪያ ቀን ከሰዓት ላይ ለተወሰኑ ሰዓታት የመሳተፍ እድል አግኝቼ ነበር፡፡ ውይይታቸው በጣም ደስ የሚል እና ላወቀበት ብዙ ግብዓት የሚገኝበት ነበር፡፡ ዓላማዬ ስለፎረሙ ሪፖርት ማቅረብ ስላልሆነ በዚህ ዙሪያ የምለው ነገር አይኖረኝም፡፡ እኔ በራሴ ግን ቀድሞውንም በዚሁ ዙሪያ ሳብላላቸው የነበሩ ሀሳቦችን … Continue reading ሚዲያዎቻችን በህዝብ ዘንድ መታመንን ያስቀድሙ – ሌላው ይከተላል!!

ለውጥ ከብሔራዊ ድርጅቶች ሳይሆን ከኢህአዴግ (ከፌደራል) ብንጠብቅ ይሻላል

የኢህአዴግ ጉባዔ ከዚህ በፊት ተደርጎ የማያውቅ እስከሚመስል ድረስ በርካቶች በጉጉት የሚጠብቁት ሆኗል፡፡ ለመሆኑ ከጉባዔው ህዝቡ ምን ፈልጎ ነው እንደዚህ የሚጠብቀው የሚለውን እንይ እስኪ፡፡ በርግጥ በአሁኑ ሰዓት አንድ አፍጥጦ የወጣ ሀቅ አለ፤ አብዛኞቹ ከኢህአዴግ የሚጠበቁ ጥያቄዎች የራስን ክልል/ ብሔር እንጂ ሐገሪቱን የማይመለከቱ መሆናቸውን እያስተዋልን ነው፡፡ የትግራይ ብሔር ተወላጆች አብዛኞቹ ጥያቄዎቻቸው የትግራይ ክልልን የሚመለከቱ ናቸው፤ የኦሮሚም፣ የአማራም … Continue reading ለውጥ ከብሔራዊ ድርጅቶች ሳይሆን ከኢህአዴግ (ከፌደራል) ብንጠብቅ ይሻላል

ሐበሻ ማን ነው?

በጥንት ዘመን ምናልባት BBC በ DNA ጥናት አረጋግጨዋለሁ እንዳለው የዛሬ 3 ሺ አመት ገደማ ከአሁኗ ሌባንት/ሶሪያ አካባቢ(የመን አይደለም) ወደ ኢትዮጵያ የተደረገ ፍልሰት ነበረ፡፡ በሌሎች ሰነዶች መሰረት በዚህ ወቅት ባህር ተሻግረው ከአሁኗ ኢትዮጵያ ወይም ኤርትራ የሰፈሩት ነገዶች ስም ሀበሣትና አግዓዚያን ይባሉ ነበር፡፡ (ሸ ፊደል በጥንታዊ የኢትዮጵያ ሴሜቲክ ቋንቋዎች አልነበረም፡፡ ሀበሻ መባል የተጀመረው ሸ፣ቸ፣ጨ፣ኘ፣ . . . … Continue reading ሐበሻ ማን ነው?

የኢኮኖሚ እድገታችን እዳ ከፋዮች

(አዲስ ከድሬዳዋ) መንግስት ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ በማድረግና በሚፈለገው ደረጃ ባይሆንም ኢንቨስትመንቶችን በማስተናገድ ኢኮኖሚው እያደገ ነው፡፡ ዋነኛው የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽና የስራ እድል ፈጣሪ መንግስት በሆነበት ሁኔታ በመንግስት ሜጋ እና ትናንሽ ፕሮጄክቶች አማካኝነት ወደገበያው እየተለቀቀ ያለው ገንዘብና ከገበያው የሚሰበሰበው የገንዘብ መጠን ልዩነቱ ሰፊ በመሆኑ የግሽበት ተጋላጭነታችን ከፍተኛ ነው፡፡ ባንድ ወቅት ከ40 ፐርሰንት በላይ ደርሶ የነበረው የሀገራችን የዋጋ ግሽበት … Continue reading የኢኮኖሚ እድገታችን እዳ ከፋዮች

ኦሮምኛ ለፌደራል መንግስት – እንዴት?

(አዲስ ከድሬዳዋ) በሶሻል ሚዲያ(በተለይ በፌስቡክ) ብዙ ጊዜ አስተማሪና ምክንያታዊ የሆኑ ፅሑፎችን በመፃፍ የሚታወቀው ዶክተር ብርሀነ መስቀል አበበ ሰኚ ሰሞኑን ከአማርኛ ጎን ለጎን ኦሮምኛም የፌደራል መንግስት፣ እንዲሁም የድሬዳዋ እና የአዲስአበባ አስተዳደሮች የስራ ቋንቋ እንዲሆን የሚጠይቁ ፅሑፎችን በተከታታይ እያወጣ ሰፊ ውይይትም እየተደረገ ነው፡፡ ሀሳቡንም በግሌ እደግፈዋለሁ፡፡ነገር ግን በምን መልኩ ነው የስራ ቋንቋ የሚሆነው , እንዲሁም በአተገባበር ሒደት … Continue reading ኦሮምኛ ለፌደራል መንግስት – እንዴት?

የአዲስ አበባ – ፊንፊኔ ዙሪያ እቅድን መቃወም ለምን?

(አዲስ – ከድሬዳዋ) ድሮ ድሮ የአዲስአበባ ዙሪያ ገበሬዎች ራሳቸው መሬታቸውን እየሸጡ ነበር ከተማ የሚስፋፋው፡፡ ከ15 አመት ወዲህ ደግሞ መንግስት ካሳ እየከፈለ መሬታቸውን በሊዝ ለባለሀብት(ቤተሰሪ) ይሰጥ ነበር፡፡ በመጀመሪያዎቹ አመታት ታዲያ ለመሬቱ የሚከፈለው ክፍያ እዚህ ግባ የማይባል ስለነበር የብዙዎችን ህይወት ያበላሸ ነበር፡፡ በ1990ዎቹ አጋማሽ ካዛንቺስ ቶታል አካባቢ እዚህ ግበ የማይባል ካሳ ተሰትቶት የንግድ ተቋሙን የተነጠቀ ሰው ራሱን … Continue reading የአዲስ አበባ – ፊንፊኔ ዙሪያ እቅድን መቃወም ለምን?

የማንነት መገለጫ ዓይነቶች- በዓለም እና በኢትዮጵያ

(አዲስ ከድሬዳዋ) የቀድሞ ዩጎዝላቪያ አካል የነበሩት ክሮሺያና ሰርቢያ (የቦስኒያ ሙስሊሞችን እና ሞንቴኔግሮዎችን ጨምሮ) ሶሻሊዝም ሲንኮታኮት ከተበታተኑት የዩጎዝላቪያ ሪፑብሊኮችና ራስገዝ አስተዳደሮች መካከል ናቸው፡፡ እነኚህን ሪፑብሊኮች ቀድሞዉኑ ምን አንድ አደረጋቸው፣ በኋላስ ለምን መለያየት ፈለጉ የሚለው ትንሽ ግራ ያልተለመደ የሚመስል ነገር አለው፡፡ ከዩጎዝላቭ ሪፑብሊኮች በህዝብ ብዛትና ተፅዕኖ የመፍጠር አቅም ቀዳሚ የነበሩት ሰርቦች እና ክሮአቶች ቋንቋቸው የዲያሌክትን(ቀበሌኛን) ያህል እንኳ … Continue reading የማንነት መገለጫ ዓይነቶች- በዓለም እና በኢትዮጵያ

የሰለጠነ ውይይት እንጂ መነቋቆር ምን ሊረባን?

(አዲስ – ከድሬዳዋ ከተማ) ባለፈው ‹‹በከተሞች ፎረም ያወዛገበው ‘ትግሬ’›› በሚል የፃፍኩትን አስተያየት ተከትሎ በርካቶች ብዙ አይነት መልሶችን ሰጥተውኛል፡፡ እውነት ለመናገር እኔ የጠበቅኩትና ያገኘሁት የተለያየ ነበር፡፡ አንዳንዴ እንደአክቲቪስት/ፕሮሞተር ስታወራ በማንኛውም መንገድ ቢሆን ያንተ ሐሳብ አሸናፊ የሚሆንበትን መንገድ ላይ ብቻ ታተኩራለህ፤ ይህ ደግሞ ምናልባት ሰከን ብለህ ስታስበው አሸናፊ እንዲሆን የምትታገልለት ሐሳብ ክፍተቶች ካሉት እነኛን ክፍተቶች ለማስተካከል ጥረት … Continue reading የሰለጠነ ውይይት እንጂ መነቋቆር ምን ሊረባን?

በከተሞች ፎረም ያወዛገበው “ትግሬ”

(አዲስ – ከድሬዳዋ ከተማ) በድሬዳዋ በመካሄድ ላይ ያለው ስድስተኛው ሀገር-አቀፍ የከተሞች ፎረም መማር ለሚፈልግ አስተማሪ፣ መዝናናት ለሚፈልግ አዝናኝ ሁነቶችን እያስተናገደ በዓሉ እየቀጠለ ነው፡፡ በዚህ ሂደት በተለይ ከ20 በላይ የውጭና የሐገር ውስጥ ምሑራን ያዘጋጇቸው ጥናታዊ ፅሑፎች የሚቀርቡባቸው የፓናል ውይይቶች – የተመደበላቸው ጊዜ ባያንስና ከየከተሞቹ የሚመለከታቸው አመራሮችና ከፍተና ባለሙያዎች እንዲሳተፉባቸው ቢደረግ/እየተሳተፉ መሆኑ ቢረጋገጥ – እጅግ አስተማሪዎች ነበሩ፡፡ስለ … Continue reading በከተሞች ፎረም ያወዛገበው “ትግሬ”