በኢትዮጲያ ሶማሌ ክልል የተገነቡ ስድስት ኮሌጆች ወደ ስራ ለማስገባት ዝግጅቱ ተጠናቀቋል

(አብዱረዛቅ ካፊ)

በኢትዮጲያ ሶማሌ ክልል መንግስት በመደበው 6 መቶ ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነቡ 6 የቴክኒክ ሙያና ግብርና ማሰልጠኛ ኮሌጆች ወደ ስራ ለማስገባት ዝግጅቱ ተጠናቀቋል

የክልሉ የቴክኒክ ሙያና ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ኃላፊ አቶ ናስር ሐሰን ለክልሉ ሚዲያ እንደገለጹት በተያዘው ዓመት ስራ የሚጀምሩት ኮሌጆቹ በሀዲጋላ፣ፊቅ፣ዋርዴር፣ደገህቡር፣ሞያሌናፊልቱ አካባቢዎች የተገነቡ ናቸው፡፡

1500 ተማሪዎችን ለማስተናገድ እንዲችሉ የተገነቡት እነዚህ ኮሌጆች የተማሪዎች የመኝታ፣ የመመገቢያ፣ የመማሪያና የአስተዳደር ክፍሎች ማካተታቸውን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

ኮሌጆቹ የአርብቶ አደር ወጣቶችን በመቀበል የመኝታና የምግብ አገልግሎት በመስጠት እያንዳንዱ ኮሌጅ 250 ተማሪዎች እንደሚማሩ ያመለከቱት አቶ ናስር ከ3000 ባላይ ተማሪዎች ደግሞ ከተቋሙ ውጭ ሆነው ትምህርታቸውን መከታተል እንደሚችሉ አስታውቀዋል፡፡

400 መምህራን ተመድበው ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች እየተሟላ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

Photo – New TVT colleges in Filtu and Wardere, Ethiopian-Somali region

ግንባታቸው ባለፈው በጀት ዓመት መግቢያ ተጀምሮ በእቅዳቸው መሰረት የተጠናቀቁት የኮሌጆቹ መከፈት በክልሉ በመካከለኛ ደረጃ የሚያሰለጠን የሰው ኃይል እጥረትን ለማሟላት እንደሚያስችልም ተመልክቷል፡፡

ከኮሌጆቹ መካከል የግንባታ ስራ፣ የንብ ማነብ፣ የእንጨት ውጤቶች ማምረት፣ ሳይንሳዊ የአየር ትንቢያ መረጃ መሣሪያ ንባብ፣ ዘመናዊ የእርሻ ስራና የእንስሳት እርባታ ሙያ የረጅምና የአጫጭር ጊዜ ስልጠናዎች ይሰጣሉ፡፡

በዚህም መንግስት በአርብቶ አደር አካባቢዎች የያዘውን የሰው ሀይል ልማትና የስራ ፈጠራ ክህሎት እንዲያድግ እንደሚሰሩም ተመልክተዋል፡፡

ከተገነቡት መካከል የፊቅ ቴክኒክ ሙያና ግብርና ማሰልጠኛ ኮሌጅ ተወካይ አቶ ሙሴ መሀመድ እንዳሉት ተቋሙ መንግስት ለዘርፉ ያስቀመጠውን 70 በመቶ ተግባር ተኮር 30 በመቶ ደግሞ በንድፈ ሀሳብ የተደገፈ ጥራት ያለው ትምህርት ለመስጠት መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡

የፊቅ ከተማ ነዋሪዎች ከዚህ ቀደም ኮሌጅ በአካባቢው ባለመኖሩ ልጆቻቸውን ለማስተማር ወደ ሀረርና ጅግጅጋ ከተሞች ለመላክ እየተገደዱ እንደነበረ የገለጹት ደግሞ የፊቅ ከተማ ቀበሌ 04  ነዋሪ አቶ ከደር ኢብራሂም ናቸው፡፡

በሌላ በኩል አዳዲስ ኮሌጆችን ሳይጨምር በክልሉ 14 የመንግስትና የግል ነባር የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ከ13 ሺ በላይ ነባርና አዳዲስ ተማሪዎችን ተቀብለው በተለያዩ የስልጠና መርሃ ግብር በማሰልጠን ላይ እንደሚገኙ የክልሉ የቴክኒክ ሙያና ትምህርትና ስልጠና ቢሮ የህዝቢ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይረክቶሬት ዳይረክተር አቶ አብዲ ኢብራህም አስረድቷል፡፡

እነዚህ ኮሌጆች የተቋቋመላቸው አላማ ማሳካት እንድችሉ የተለያየ የህብረተሰብ ክፍሎችና መስተዳደር አካላትም በባለቤትነት ስሜት ተሳትፎቸውን እንድያጠናክሩ ጠይቋል::

********

Guest Author

Guest Author

Recent Posts

ኪዳነ ኣመነ – እንደህዝብ አንድ ሆነናል ያስቸገረን የህወሓት አስተሳሰብ ነው

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 2 - ለውጥ…

5 years ago

ኪዳነ አመነ – ለትግራይ ታላቅነት ሼምለስ ሆነን እንሰራለን

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 1 - ለትግራይ…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ትዴት ኢትዮጲያዊ ማንነት ብቻ እንዳለ ነው የሚያምነው (video)

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ (ክፍል 2)- ስለትዴት…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ኢሳት የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ ነው የሰራው (Video)u

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ (ክፍል 1) -…

5 years ago

የበረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ መታሰር -ሕጋዊ ወይስ ፖለቲካዊ እርምጃ?

(የማነ ካሣ) እንደሚታወቀው አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከጥረት ኮርፖሬሽን ጋር በተያያዘ…

5 years ago

ኣስተያየት በ’ኣብራክ’ ልብወለድ ድርሰት ላይ

(መርስዔ ኪዳን - ሚኔሶታ) ኣብራክ የተባለውን የሙሉጌታ ኣረጋዊ መጽሓፍ ኣነበብኩት። ኣገራችን ከሊቅ አስከደቂቅ በዘውጌ ብሄርተኝነት…

5 years ago