​የህዝብ ዓላማ፣ ባንዲራው፣ ደጋፊው ወይም አክሊሉ

(Betru Dibaba)

ግለሰብ እንደሚሮጥ ሁሉ ህዝብ ይሮጣል። የህዝብ ሩጫ ለዓላማው ነው። አንድ ህዝብ ሲሮጥ ዓላማው  ባንዲራውን መያዝ ሊሆን ይችላል። አንደኛው ህዝብ ደግሞ  የደጋፊውን ድምጽ ለመስማት ይሮጣል። ሌለኛው የህዝቡ ክፍል ደግሞ  እስከ የሩጫው የመጨረሻ መስመር ድርስ ለአክሊል  ይሮጣል።

ባንዲራውን መያዝ ዓላማው የሆነ ህዝብ ለዚሁ ዓላማ ይሮጣል። የዚህ ህዝብ ዓላማ ባንዲራውን ማግኘት ነው። ባንዲራውን ለማግኘት እስከመጨረሻ መሮጥ አይጠበቅበትም። ሩጫውን የታደሙ ባንዲራውን ባቀበሉበት ጊዜና ቦታ ባንዲራውን ይወስዳል፤ ሩጫውን ያቋርጣል። የዚህ ህዝብ ዓላማ እስከዚሁ ነው።

ከፊሉ ህዝብ ደግሞ የደጋፊውን ደምጽ መስማት የሩጫው ዓላማ ያደርጋል። ይህ ህዝብ እየሮጠ “ኦሮሞ! ኦሮሞ! ኦሮሞ! [የራሳችሁን የብሔር ስም ትጠሩ ዘንድ የተፈቀደ ነው] … ጀግናው! …” የሚል ድምጽ ከሰማ ሩጫውን ይገታል። ቆሞም የደጋፊውን የትፎዞ ድምጽ ያዳምጣል።  ሩጫው ካለቀ በሃላ ወደ መጨረሻው መስመር እየሮጠ፣ “እኔም ደርሻለሁ፤ ንገሩልኝ!” ይላል።

ሌለኛው ህዝብ ደግሞ ዓላማውን የሩጫው መጨረሻ ላይ ያደርጋል። የዚህ ህዝብ የሩጫው ዓላማ የማንነቱ፣ የአንድነቱ፣ የነፃነቱ እና የልማቱ አክሊሎች ናቸው። ይህ ህዝብ እስከመጨረሻ ይሮጣል። እየሮጠ መሃል ላይ ባንዲራውን ሊያቀብሉት ቢፈልጉ አይቀበልም። እየሮጠ የትፎዞ ድምጽ ቢበረታ ሞራሉ እስከመጨረሻ እንዲሮጥ ያስገድደዋል እንጂ የጀመረውን ሩጫ ትተው፣ ቆሞ አያዳምጥም።

እስከመጨረሻ የሮጠ ህዝብ ሁሉንም በአንድ ላይ ያገኛልና!

*********

Guest Author

more recommended stories