የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች በጅግጅጋ ከተማ በደማቅ ሁኔታ አቀባበል ተደረገላቸው

​(አብዲረዛቅ ኢልሚ ሸሪፍና አብዱረዛቅ ካፊ)

(ጅግጅጋ – ጥቅምት 01, 2010) ከ9ኙ የኢ.ፈ.ዴ.ሪ. ክልሎችና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮችን የተወጣጡ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች በኢ.ሶ.ክ.መ. ርዕስ መዲና በጅግጅጋ ከተማ በደማቅ ሁኔታ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

የጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር አመራር አባላት፣ የጅግጅጋ ከተማ አገር ሽማግሌዎችና የእምነት አባቶች እንዲሁም የጅግጅጋ ከተማ ህዝብና የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ሁለቱ ም/ፕሬዝደንቶችና የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራር የክረምት እረፍታቸው ያጠናቀቁ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎችን በጅግጅጋ ከተማ መግቢያ ላይ በደማቅ ሁኔታ የቅብብል ሥነ-ስርዓት አደረጉላቸው።

በአቀባበል ሥነ-ስርዓቱ ላይ ንግግር  ያደረጉት በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምር  ም/ፕሬዝደንት አቶ ኤልያስ ኡመር የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ  ነባር ተማሪዎች ለሁለት ወራት ያህል የክረምት ግዜያቸውን ጨርሰው በሰላም መምጣታቸው ተላቅ ደስታ የተሰማቸው ከመሆኑ ባሻገር መላው የሀገሪቱ ዩኒቬርሲቲዎች በ2010 የትምህርት ዘመናቸው መጀመሩ ተከትሎ ተማሪዎቹ በግዜ መግባታቸውን አመስግኗል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ ተማሪዎችሁ የነጌ አገር ተረካቢ መሆናቸው አስታውሶ ትምህረታቸውን ያለ ምንም ስጋት እንድከታተሉና ለትምህርታቸው ብቻ ትክረት እንደሰጡም አሳስቧል  ም/ፕሬዝደንቱ፡፡

በተመሳሳይም  በጅግጅጋ ከተማ የሚገኙ የእምነት አባቶች በበኩላቸው ለተማሪዎችሁ የተደረገለት የአቀባበል ሥነ-ስርዓት በጣም የተደሰቱበት ከመሆኑ ባለፈ ተማሪዎችሁ በሀገራችን የተጀመረው የልማት ጉዞ በእውቀታቸው የላቀ ደረጃ ለማድረስ የበኩላቸው ኃላፊነት እንዲወጡና ለትምህርታቸው ትክረት እንደሰጡ ጥሪ አቀረቡ፡፡

የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በበኩላቸው የተደረገለት የቅብብል ሥርዓቱ እጅግ ያስደሰታቸው መሆኑና ለዩኒቬርሲቲው የመማር ማስተማር ሂደትም አበረታች መሆኑን ገልጧል፡፡

በመጨረሻም በዘንደሮ አመት በዩኒቨርሲቲው ከ8ሺ በላይ አዳዲስ ተማሪዎች እንደሚመደቡብየጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምር  ም/ፕሬዝደንት አቶ ኤልያስ ኡመር ገልፀዋል፡፡

*********

Guest Author

Guest Author

Recent Posts

ኪዳነ ኣመነ – እንደህዝብ አንድ ሆነናል ያስቸገረን የህወሓት አስተሳሰብ ነው

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 2 - ለውጥ…

5 years ago

ኪዳነ አመነ – ለትግራይ ታላቅነት ሼምለስ ሆነን እንሰራለን

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 1 - ለትግራይ…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ትዴት ኢትዮጲያዊ ማንነት ብቻ እንዳለ ነው የሚያምነው (video)

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ (ክፍል 2)- ስለትዴት…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ኢሳት የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ ነው የሰራው (Video)u

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ (ክፍል 1) -…

5 years ago

የበረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ መታሰር -ሕጋዊ ወይስ ፖለቲካዊ እርምጃ?

(የማነ ካሣ) እንደሚታወቀው አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከጥረት ኮርፖሬሽን ጋር በተያያዘ…

5 years ago

ኣስተያየት በ’ኣብራክ’ ልብወለድ ድርሰት ላይ

(መርስዔ ኪዳን - ሚኔሶታ) ኣብራክ የተባለውን የሙሉጌታ ኣረጋዊ መጽሓፍ ኣነበብኩት። ኣገራችን ከሊቅ አስከደቂቅ በዘውጌ ብሄርተኝነት…

5 years ago