በኦሮሚያ – በአምቦ፤ ዶዶላ እና ሻሸመኔ ተቃውሞ ተደረገ

(እሸቴ በቀለና ሸዋዬ ለገሠ – ጀርመን ራዲዮ)

በአምቦ፤ ዶዶላ እና ሻሸመኔ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች ተደረጉ። የዓይን እማኞች “በሰላም ተጠናቋል” ባሉት የአምቦ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ የኢትዮጵያ መንግሥት የሰላ ትችት ተሰንዝሮበታል።

በዶዶላ ከተማ በተደረገ ተመሳሳይ የተቃውሞ ሰልፍ የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተሞች የባለቤትነት ጥያቄ መነሳቱን የከተማዋ ነዋሪ ተናግረዋል።

ከአዲስ አበባ በ126 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው የአምቦ ከተማ ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ነዋሪዎች የኢትዮጵያ መንግሥትን ተችተዋል።

የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፤ የመንግሥት ሠራተኞች እና የከተማዋ ነዋሪዎች ተቃውሞው ትልቅ ነበር ሲሉ ለዶይቸ ቬለ አረጋግጠዋል።

Photo – Ethiopia, Ambo city protest – Oct 11, 2017

የዓይን እማኞች እንደሚሉት ዛሬ ጠዋት 4 ሰዓት አካባቢ የጀመረው ተቃውሞ እስከ ስድስት ሰዓት ዘልቋል።

በተቃውሞ ሰልፉ ላይ ኦሮሞ ሊዋሐድ ይገባል የሚሉ ጥሪዎች ተደምጠዋል የሚሉት የከተማዋ ነዋሪ መንግሥት ይውረድ የሚል መፈክርም ተደምጧል ብለዋል። 

“በቃ ሕብረተሰቡ በሙሉ ማለት እንችላለን ከተማው አልቀረም ጫፍ እስከ ጫፍ ብዙ ነበረ። ደስ የሚል ነበረ። በሰላም ነው የተጠናቀቀው። መፈክሮች ወያኔ ይጥፋ፤ ወያኔ ይብቃን ካሁን በኋላ ኢሕአዴግ አይግዛን ኦሮሞ ራሳችንን እናስተዳድራለን ነው።”

የተቃውሞ ሰልፉ እንደ ከዚህ ቀደሙ በወጣቶች ብቻ ሳይሆን መላ የከተማዋን ነዋሪዎች አካቷል የሚሉት ሌላኛዉ የአምቦ ነዋሪ ለሁለት ሰዓት መካሔዱን ተናግረዋል። የተቃውሞ ሰልፈኞች የመብት ጥያቄዎችን ጠይቀዋል የሚሉት የዓይን እማኙ በአካባቢው የነበሩት አድማ በታኝ ፖሊሶች ምንም ዓይነት እርምጃ አለመውሰዳቸውን ተናግረዋል። በአምቦው ተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፈኞች ፋብሪካ መነቀል የለበትም፤ ዜጎች ከሶማሌ ክልል ሊፈናቀሉ አይገባም የሚሉ መፈክሮች ማሰማታቸውን የከተማዋ ነዋሪ ነኝ ያሉ ግለሰብ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። 

የዛሬው የተቃውሞ ሰልፍ ከአምቦ ባሻገር ሻሸመኔ እና ዶዶላን በመሳሰሉ አካባቢዎችም ተደርጓል። የዶዶላው ነዋሪ አቶ አህመድ መሐመድ እንደታዘቡት ከቀኑ ሰባት ሰዓት ገደማ የተጀመረው የተቃውሞ ሰልፍ ከወትሮው በተለየ አመራሮች እና የጸጥታ ኃይሎች ጭምር የተሳተፉበት ወጥነትም የነበረው ነው።  

በዶዶላው ተቃውሞ በእስር ላይ የሚገኙት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አመራሮች ይፈቱ ከሚለው ጥያቄ ባሻገር የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ የባለቤትነት ጥያቄ ተነስቷል ሲሉ የዓይን እማኙ አክለዉ ነግረውናል።
በሻሸመኔ ከተማ በተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ አንድ የተመታ ሰው አለ የሚል መረጃ ቢኖርም ለማረጋገጥ ሳንችል ቀርተናል። የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኃላፊዎችም በተደጋጋሚ ያደረግናቸዉን የስልክ ጥሪዎች አልመልሱም።

********

Curated Content

Content gathered and compiled from online and offline media by Hornaffairs staff based on relevance and interest to the Horn of Africa.

Recent Posts

ኪዳነ ኣመነ – እንደህዝብ አንድ ሆነናል ያስቸገረን የህወሓት አስተሳሰብ ነው

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 2 - ለውጥ…

5 years ago

ኪዳነ አመነ – ለትግራይ ታላቅነት ሼምለስ ሆነን እንሰራለን

ከብሔራዊ ባይቶ ኣባይ ትግራይ (ባይቶና) አመራር ኪዳነ አመነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ክፍል 1 - ለትግራይ…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ትዴት ኢትዮጲያዊ ማንነት ብቻ እንዳለ ነው የሚያምነው (video)

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ (ክፍል 2)- ስለትዴት…

5 years ago

መኮንን ዘለለው – ኢሳት የትግራይ ህዝብ እንዲጠፋ ነው የሰራው (Video)u

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) አመራር መኮንን ዘለለው ከሆርን አፌይርስ ጋር ያደረጉት ቃለ-ምልልስ (ክፍል 1) -…

5 years ago

የበረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ መታሰር -ሕጋዊ ወይስ ፖለቲካዊ እርምጃ?

(የማነ ካሣ) እንደሚታወቀው አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) ከጥረት ኮርፖሬሽን ጋር በተያያዘ…

5 years ago

ኣስተያየት በ’ኣብራክ’ ልብወለድ ድርሰት ላይ

(መርስዔ ኪዳን - ሚኔሶታ) ኣብራክ የተባለውን የሙሉጌታ ኣረጋዊ መጽሓፍ ኣነበብኩት። ኣገራችን ከሊቅ አስከደቂቅ በዘውጌ ብሄርተኝነት…

5 years ago