በግሎባላይዜሽን ማደግ እንችላለን?

(ስንታየሁ ግርማ)

አሁን ያለንበት ዘመን የግሎባላይዜሽን ዘመን ይሉታል፡፡ በአጭሩ ግሎባላይዜሽን ማለት በምርት እና በገበያ በጥቅሉ የተሳሳረች አለም ለማለት ነው፡፡ ግሎባላይዜሽን ብሔራዊ ኢኮኖሚን ወደ ተያያዙ እና ተደጋጋፊ (ተመጋጋቢ) ወደ ሆነች አለም ኢኮኖሚ መቀየር ማለት ነው፡፡

በሌላ በኩል ግሎባላይዜሽን ማለት አሜሪካናይዜሽን ማለት ነው የሚሉት አሉ፡፡ አባባሉ አዲሱ የአለም ሰርአት ወይንም የአሜሪካ ስርአት ማለት ነው ይሉታል፡፡ ይሁንና በዚሁ ስርአት አሜሪካ ብቸኛ ተጠቃሚ ናት ብሎ መደምደም አስቸጋሪ ነው፡፡ ምክንያቱም ከምንም ተነስታ በአለም ቁጥር 2 ኢኮኖሚ የሆነችው ቻይና በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ዜጐችን ከድህነት ያወጣችው ቻይናምን የግሎባለይዜሽን ውጤት ናትና፡፡

ግሎባል ገበያ

ግሎባላይዜሽን 2 ዋና ዋና ክፍሎች አሉት፡፡ እነሱም ግሎባል ገበያ እና ግሎባል ምርት የሚባሉት ናቸው፡፡ ግሎባል ገበያ ማለት በታሪክ የተለያዩ እና በተነጣጠሉ ገበያዎች ወደ አንድ ትልቅ ገበያ የተለወጡበት ማለት ነው፡፡ በአለም ላይ ሸማቾች የምርት ፍላጐታቸው እና ምርጫቸው እጅግ ሁሉ የተቀራረበ በመምጣቱ ግሎባል ምርት እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል፡፡ ይህ ደግሞ ግሎባል ገበያ እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል፡፡ በግሎባል ገበያ ተቀባይነት ያገኙ ምርቶች መካከል ኰካኮላ፣ ማክዶናልድ፣ ሊቫይ ጀንስ፣ እና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡

መረጃዎች እንደሚያሳዩት በአሜሪካ ኤክስፖርት ከሚያደርጉት ኩባንያዎች መካከል 97 በመቶ ተናንሾች ናቸው፡፡ በ1987 እና በ1997 (አ.ኤ.አ) በአሜሪካ ከ100 በታች ሠራተኞች ያላቸው ኩባንያዎች በእጥፍ አድረገው ነበር፡፡ ይህ ደግሞ በዘመነ ግሎባላይዜሽን በትልልቅ ብቻ ሳይሆን በትናንሽ ድርጅቶችም መወዳደር እንደሚቻል ነው የሚያሳዩት፡፡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት አነስተኛ እና ጥቃቅን ኩባንያዎች ወደ ቻይና ሆንግ ኰንግ ኤክስፖርት ባደረጉት መካከል 40 በመቶ ይሸፍናሉ፡፡

ብሔራዊ ገበያዎች ለግሎባል ገበያ ቦታቸውን እየሠጡ ናቸው፡፡ በብሔራዊ ገበያ አሁንም የተጠቃሚዎች ምርጫ፣ መለያየት፣ የዚህ ስርጭት ሁኔታ፣ በባህል ላይ የተመሠረተ የእሴት ልዩነቶች፣ እና ብሔራዊ ገቢዎች ለግሎባል ገበያ ቦታቸውን እየሰጡ ናቸው፡፡ በብሔራዊ ገበያ አሁንም የተጠቃሚዎች ምርጫ፣ መለያየት የዚህ ሁኔታ፣ በባህል ላይ የተመሠረተ የእሴት ልዩነቶች፣ እና የመሳሰሉት ይታያሉ፡፡ ሆኖም ግን በእስትራቴጂክ ማርኪቲንግ እቅዳቸው እነዚህን ማጣጣም ችለዋል፡፡ ለምሳሌ የመኪና ፋብሪካዎች የተለያዩ ሞዴሎች ለተለያዩ ሀገሮች እንደየአካባቢው የነዳጅ ዋጋ የገበያ መጠን፣ የትራፊክ ሁኔታ እና የባህል እሴቶች ግምት ውስጥ በማስገባት ያቀርባሉ፡፡ ቻይና ለእፍሪካ እና ለአሜሪካ የምታቀርባቸው ምርቶች በሸማች የመግዛት አቅም ላይ ተንተርሰው እጅግ የተለያዩ ናቸው፡፡

በግሎባላይዜሽን ከፍተኛ እና የማይታመን ውድድር በመኖሩ ሸማቾች ተጠቃሚ እየሆኑ ነው፡፡ የሸማቾች ምርቶች የኢንዱስትሪ እቃዎች እና የፋይናንስ አገልግሎት ዋነኛው ገፅታቸው ከሀገር ሀገር ከፍተኛ ውድድር ማጋጠሙ ነው፡፡ ኰካኮላ ከፔፕሲ፣ ፎርድ ከቶዮታ፣ ቦይንግ ከኤየርባስ፣ ወዘተ በሞት ሽረት ወድድር ላይ ናቸው፡፡ ለብዙ ኩባንያዎች የአሜሪካ የቻይና የእንግሊዝ ገበያ ማለት ትርጉም የለሽ እየሆነ ነው፡፡ ምክንያቱም በግሎባል ገበያ እየተቀየሩ ስለሆነ ነው፡፡

ግሎባል ምርት

ግሎባል ምርት ማለት ምርትና አገልግለትን የተለየዩ ሀገሮች ከብሔራዊ አዋጭነት አኳያ ሲያመርቱ ነው፡፡ አዋጭነቱ በዋናነኝነት በዋጋና በጥራት በዋነኝነት የተመሠተ ነው፡፡ አንዱ ሀገር የአንድን ምርት የተወሰነ ክፍል በማምረት በዋጋ አዋጭ ሊሆን ይችላል፡፡ ሌላኛው ሀገር ተመሳሳይ ምርትን ሌሎች ክፍል በማምረት ተወዳዳሪ ሊሆን ይችላል፡፡ ኩባንያዎች ይህንን በማድረጋቸው አጠቃላይ ወጪያቸውን በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሱ ነው፡፡ የምርት አቅርቦታቸውንና ጥራታቸውንም ለማሻሻል እየረዱ ናቸው፡፡ ከዚያም በተቀናቃኛቸው የተሻለ አቅም እንዲኖራቸው ያስችላቸዋል፡፡ ቦይንግ 777 ለምሳሌ ብንወስድ 132500 የምርት ክፍሎች አሉት፡፡ በ545 አቅራቢዎች ይመረታል፡፡ የተለያዩ ክፍሎች በተለያዩ ሀገራት የሚሠሩበት ምክንያት እነዚህ አቅራቢዎች የተለያዩ ክፍሎችን በማምረት በጣም የተሻሉ ስለሆኑ እና አዋጭ ስለሆነ ነው፡፡ ስምንት የጃፓን አቅራቢዎች የቦይንግ የበርና ክንፍን ሲያመርቱ 3 የጣሊያን አቅራቢዎች የቦይንግ ክንፍ ሊፍት ያመርታሉ፡፡ በሲንጋፖርም የሚመረት ክፍል አለ፡፡ ስለዚህ ምንም እንኳን ብራንዱ የአሜሪካ ቢሆንም ቦንግ የአሜሪካ ምርት ሳይሆን የአለም ምርት እየሆነ ነው ማለት ነው፡፡

የተለያዩ ምርቶችን በተለያዩ ሀገራት ማምረት በትላላቅ ምርቶች ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ የአነስተኞቹም ጭምር እንጂ ለምሳሌ ሰዋን ኦፕቲካል የአይን መነፅር አምራች ድርጅት ነው፡፡ መሠረቱ አሜሪካ ነው፡፡ አመታዊ ሽያጩ ከ20-30 ሚሊዮን እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ የስዋን መነፅሮች የተለያዩ ክፍሎች በሆንግኮንግ በቻይና በጃፓን፣ በፈረንሳይ፣ በጣሊያን ይመረታሉ፡፡ ይህንን በማድረጉ ስዋን በአለም ገበያ ተወዳዳሪ መሆን ችሏል፡፡ በአጠቃላይ በሰዋንም ሆነ የቦይንግ 777 ልምድ የሚያሳዩን ስለአሜሪካ ምርት ሳይሆን ስለአለም ምርት መሆኑ ነው፡፡

ምንም እንኳን አለም በምርቶች እና በገበያዎች በጥብቅ እየተሳሰረች ቢሆንም አሁንም የሚያገጥሙ ፈተናዎች እና ተግዳሮች አሉ፡፡ መደበኛ የሆኑና ያልሆኑ የንግድ መሰናክሎች አሁንም በሀገራት መካከል ይታያሉ፡፡ የትራንስፖርት ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መዋዥቅ፣ የአለም ኢኮኖሚው ቀውስ መሠረታዊ ምክንያቶች አለመፈታት ከፖለቲካ ጋር የተያያዙ ስጋቶች እንደ ትራምፕ ዓይነት መሪዎች በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት የቀኝ እና የግራ ክንፍ ፓርቲዎች በፓርላማ የበላይነት ማግኘታቸው፣ በበለፁጉት ሀገራት እና በድሃ ሃገራት መካከል ያለው የገቢ ልዩነት እንደታሰበው እየጠበበ አለመምጣት፣ በምዕራቡ አለም ያለው በድሆች እና በሀብታሞች መካከል ያለው የገቢ ልዩነት እየሠፋ መሄድ የሚሉት ይገኙበታል፡፡

የግሎባላይዜሽን መንስኤዎች

ለግሎባላይዜሽን ማደግ እና መስፋፋት የተለያዩ ምሁራን የተለያዩ ትንታኔዎች ይሰጣሉ፡፡ በአብዛኛው ግን ስምምነት የተደረሰባቸው ምክንያቶች ሁለት ናቸው፡፡ አንዳቸው ከ2ኛው የአለም ጦርነት በኋላ በምርቶች እና በአገልግሎቶች ላይ ተጥሎ የነበረው ቀረጥ ኰታ እና የመሳሰሉት የንግድ መሰናክሎች በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሱ መምጣቱ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ደግሞ የቴክኖሎጂ እድገት በተለይም የኮሚኒኬሽን በኢንሞርሜሽን ፕሮሰሲንግ እና በትራንስፖርት የታየው የቴክኖሎጂ ለውጥ ነው፡፡

እ.ኤ.አ በ1920ዎቹ እና በ1930ዎች ብዙ ሀገራት በአለም ንግድ እና ኢንቨስትመንት ላይ ከባድ መሠናክሎችን ጥለው ነበር፡፡ መሰናክሎችም በከፍተኛ ቀረጥ እና በኰታ መልክ የሚገለፁ ነበሩ፡፡ አለማው የሀገር ውስጥ ምርትን ከውድድር ለመከላከል ነበር፡፡ ይህ ደገሞ ሀገራትን ከፈተኛ ቀረጥ ወደ መጣል ውድድር ውስጥ አስገብቷቸው ነበር፡፡ ይህ ደግሞ በአለም ላይ ከፍተኛ የፍላጐት መቀነስን አስገብቶ በአለም ላይ የ1930ዎቹን የኢኮኖሚ ውድቀት አስከትሎ ነበር፡፡

ከዚህ የኢኮኖሚ ድቀት በመማር በአሜሪካ መሪነት በሀገራት የንግድና የኢንቨስትመንት እንቅፋቶች በሂደት ለመቀነስ ተስማሙ፡፡ እ.ኤ.አ በ1993 በኡራጋይ የአለም የንግድ ድርጅትን አቋቁመ፡፡ ድርጅቱ የአለም ንግድ በተመለተ ፖሊሲዎትን ያወጣል በ125 ሀገሮችም ድርጅቱን ለመቀላቀል ተስማምተዋል፡፡ በሀገራት መካከልም ያሉ የንግድ አለመግባባቶችንም ይፈታል፡፡ በተለያዩ ወቅቶች በተለያዩ ሀገራት መካከል ንግድና ኢንቨስትመንትን የሚገድቡ ተግባራትን ለመቀነስ/ለማስወገድ/ ስምምነት አድርገዋል፡፡ እነዚህ ድርጊቶች ደግሞ የአለም ምርቶችን የአለም ገበያን ማደግ አፍጥነውታል፡፡ የአለም ገበያ እና ምርት መስፋፋት የአለመ ንግድንና ምርትን በከፍተኛ መጠን እንዲያድግ አስተዋጽኦ እያደረጉ ነው፡፡ ግሎባላይዜሽን ሀገራትን በጥብቅ እያስተሳሰረ ነው፡፡

ግሎባላይዜሽን ምርትንና አገልግሎትን በከፍተኛ ሁኔታ እያሳደገ ቢሆንም አሁንም በጥርጣሬ የሚያዩት አሉ፡፡ ግሎባላይዜሽን ማለት አዲሱ የአለም ስርአት ነው፡፡ ይህ ሰርአትም በአሜሪካ የሚመራ ነው፡፡ ስርአትም ሳይሆን ስርአት አልበኝነትም ጭምር ነው፡፡ ለምሳሌ አሜሪካ በኢራቅ ያደረገችውን ጣልቃ ገብነትን ማስታወስ (ያለ ተመድ እውቅና መሆኑ) ልብ ይሏል፡፡

ያም ሆነ ይህ ግሎባልይዜሽን የአለማችን እውነታ እየሆነ ነው፡፡ ታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ እንዳሉት የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን የስርአት ጉዳይ ነው፡፡ እንደ ቻይና ያሉ ዝሆኖችን ያሳደገ ስርአት ኢትዮጵያን የሚያሳድግበት ምክንያት አይኖርም፡፡ እርሳቸው እንደሚሉት ከግሎባልይዜሽን ስርአት ውጭ መሆን ከእግር ኳስ ሜዳ ቀርቶ በፎርፌ መሸነፉ ነው፡፡ ከግሎባለይዜሽን ውጭ መሆን እንደ ሰሜን ኮሪያ ተመጽዋች መሆን ነው፡፡ ሰሜን ኮሪያ ያላትን የኒኮለር ሃይል በማስፋፋያነት በመጠቀም በአመት በነፋስወከፍ ከደቡብ ኮሪያ ከ3000 ዶላር በላይ እርዳታ ታገኛለች፡፡

ታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ በግሎባይዜሽን ማደግ እንደሚቻል ቻይና በተግባር ስላሰየች ከእንግዲህ ስለ ጉዳዩ ውይይት የትወራ እንጂ የትግበራ አይደለም፡፡ ስለዚህ በግላሎባይዜሽን አዋጭነታችን በመለየት በጥብቅ መሳተፍ ይኖርብናል ይላሉ፡፡ የ”ኤስያ ነብሮች” ከሚባሉትም የምንማረውም ይኸው ነው፡፡ እነዚህ በአለም አስደማሚ የሆነ እድገት ያስመዘገቡ የኤስያ ሀገራት ለእድገታቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ካደረገው መካከል ኤክስፖርት መር ፖሊሲ መከተላቸው ነው፡፡ እንደ ኮሪያ የመሳሰሉት ሀገራት ለባለሀብቱ በየአመቱ የኤስክፖርት ኰታ ይሰጡት ነበር፡፡ ኮታውን ካሳካ የተለያዩ ማበረታቻዎች ይሰጡ ነበር፡፡ አንዳንዶቹ ለሀገር ወስጥ ምርቶች የተፈቀዱትን ጭምር ለኤስክስፖርት አድራጊዎች ተሰጠ፡፡ ኰታውን ካላሳካ ከፍተኛ የሆነ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ቅጣቶች ተገበሩ፡፡ ኮሪያም ስኬታማ ሆነች እና ታይዋንም እናማ ሌሎች እሷን ተከትለው አደጉ፡፡

ኢትዮጵያን ይህንን ፈለግ መከተል ትችላለች፡፡ አሰሱን ገሰሱንም ወደውጭ መላክ ሳይሆን በጥናት ላይ ተመስርቶ የአንፃራዊ ብልጫችን በመለየት መወዳደር ነው፡፡ ለምሳሌ በአለም ላይ 90% የሚሆነውን ጤፍ እናመርታለን፡፡ ጤፍ በንጥረ ነገር የበለፀገ እና የተለየዩ የጤና ጥቅሞች እንዳሉት በምዕራባውያን ተመራማሪዎች ሳይቀር እየተረጋገጠ ነው፡፡ በምዕራቡ ዓለም በሚመገቡት ምግብ ምክንያት ከልክ ያለፈ ወፍረት የጤና የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ችግር እየሆነ ነው፡፡ ሸማቹ ስኳር በበዛባቸው ምግቦች ምክንያት የእራሱ እና የልጆቹ ጤንነት አደጋ ላይ እየወደቀ ስለሆነ መንግስት በማስታወቂያ ላይ አዲስ ሕግ እንዲያወጣ እየወተወቱ ነው፡፡ ከፍተኛ ቀረጥም በእነዚህ ምርቶች ላይ እንዲጣል የመበት ተሟጋቾች እየወተወቱ ነው፡፡ አሜሪካ በዚሁ ምክንያት በየአመቱ ከ147 እስከ 210 ቢሊዮን ዶላር እያወጣች መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

እነ በክቶሪያ ቤከም የመሳሰሉትም ጤፍ ካለው ጠቀሜታ አንፃር ምርጫቸው እየሆነ ነው፡፡ (hollywood’s new favorite food revealed; Victoria beckham and gwyneth parlow are fans of teff, an iron-rich Ethiopian grain…” Daily mail, 2 Feb. 2014)

ሌሎች እንደጋርዲያን እና ኒዮርክ ታይምስም ስለጤፍ ጠቀሜታዎች እያተቱ ነው፡፡ ለምሳሌ ኒዮርክ ታይምስ ኦገስት 16፣ 2016 “is teff the new super grain?” በሚል ርዕሰ አንቀስ ስለጤፍ ጠቀሜታዎች አሰነብቧል፡፡ እነዚህን መልካም አጋጣሚዎች ልንጠቀምበት ይገባል፡፡ ይህንን ለማድረግ ደግሞ የማስተዋወቅ አቅማችን ማሳደግ ይገባል፡፡ በመጀመሪያ ግን ኢትዮጵያን በማስተዋወቅ ከሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች የተወጠጡ ባለሙያዎች ያሉበት ቡድን ማቋቋም ያስፈልጋል፡፡ ባለሙያዎቹ ኢትዮጵያ ያላትን አንፃራዊ ብልጫ በጥናት እንዲለዩ መደረግ አለበት፡፡ በመቀጠል የጥንካሬ፣ የድክመት፣ የመልካም አጋጣሚዎች እና የስጋቶች ትንተና በመካሄድ ወደስራ መግባት ይኖርበታል፡፡

የኢትዮጵያን መለያ ወይንም ብራንድ ለማስተዋወቅ የሚዋቀረው ቡድን እና የሚያከናውናቸው ተግባራት የሚከተሉት በሆኑ ይመረጣል (አሊንሳ 1999 እ.ኤ.አ)

* ከመንግስት፣ ከባለሀብቶች/ኤክስፖርት ከሚያደርጉት ተመርጠው/ ከአርት ሰዎች፣ ከትምህርት ተቋማት፣ ከሚዲያ የተሰበሰቡ

* ስለሀገራቱ ዜጐች እና በውጭ አለም እንዴት እንደሚታዩ፣ የተለያዩ የጥናት ዘዴዎችን በመጠቀም ማወቅ

* የሀገሪቱን ገፅታ ጠንካራ /ደካማ/ ጐኖች ለመለየት ተጽእኖ ፈጣሪ ከሆኑ ግለሰቦች እና ቡድኖች እና ሃገሮች ጋር አቀፍ ምክክር ማካሄድ እና ስምምነት መድረስ

* ኢትዮጵያን ለማስተዋወቅ የሚረዳ ማዕከላዊ ሃሳብ ከባለሙያዎች ጋር በመሆን መለየት ሌሎች ፕሮግራሞችም የሚመሩበት ማድረግ ዋናው ሃሳብ የኢትዮጵያ የተለየ መለያ ባህሪ የያዘ መሆን አለበት፡፡

* ዋነኛው ሃሳብ የሚተዋወቅበትን ዘዴዎች ሎጐን ጨምሮ በመለየት ማስተዋወቅ

* ቱሪስቶችን ለመሳብ፣ ኢንቨስተሮችን ለመማረክ፣ ኤክስፖርት በውጭ ገበያ ተቀባይነት እንዲያገኝ እንደ አዲያንሱ በህሪ መልዕክቶች አዘጋጅቶ እና የተቀናጅ አድርጐ ማሰራጨት የስርአቱን ቀጣይነት የሚያረጋግጥ ያገናኝ ቡድን ማቋቋም ነው መዘርጋት ነው፡፡

**********

* ስንታየሁ ግርማ የፌደራል ኤች አይ ቪ/ኤድስ መ/መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ

Guest Author

more recommended stories