Feb 14 2017

ወገን ተከበናል?

የኦባማ ቅልስልስ አስተዳደር ከኢራን ጋር ያደረገው ስምምነት የብዙ አረብ አገራትን ቀልብ የገፈፈ ነበር። በዚህም የተነሳ ረስተውት የቆዩትን ጦራቸውን ማጠናከር እና በጓደኛ ብዛት መፎካከሩን ተያይዘውታል።

ብዙዎቹ (ሚጢጢዎቹ) ሀገራት ሳይቀሩ ጦራቸውን አፍሪካ ላይ ማስፈር አሜሪካ አሜሪካ መጫወት ጀምረዋል። ለዚህ ደግሞ ዋናው የትርኢቱ መድረክ ለመካከለኛው ምስራቅ ስትራቴጂካዊ ትርጉም ያለው ምስራቅ አፍሪካ ነው።

ጅቡቲ

ከፈረንሳይ ነፃ ወጥታ የማታውቀው ጅቡቲ አሁን ጦር ያለውን አገር ሁሉ ታስተናግዳለች። አገሪቷ ዋና የኢኮኖሚ መሰረቷ ኢትዮጲያ የሆነች የተለየ የአይዲዮሎጂ ዝንባሌ የሌላት ሰላም ፈላጊ ጥገኛ ነች። በዚያ ላይ አሜሪካም ቻይናም ሁሉም አሉባትና የተለየ ስጋት አታጭርም።

ኤርትራ

ኤርትራ ያው ኤርትራ ነች። እሺ ካሏት ለእኛ ጥፋት የማትሆነው የለም። እዛ የሰፈረው የቃጣር እና ሳውዲ ጦር ለግዜው ዋና ትኩረቱ የመን ላይ ነው። አሜሪካን ከመጠበቅ እራሳቸው ወደ መደብደብ ያደጉት ሀገራት በአረብ ሆነ በምዕራብ ሀገራት አንድ ሰልፍ ሳይወጣባቸው የየመንን ህዝብ እየፈጁት ነው። ሲጨርሱ ኤርትራን ለቀው ወደ ቀጠናቸው ይመለሱልናል ወይስ እዚሁ ተወዝፈው ስራ ይሰጡናል የሚለውን በሂደት የምናየው ይሆናል።

ኢትዮጲያ ወደፊት ኤርትራ ላይ ልትወስደው በምትችለው ወታደራዊ እርምጃ ላይ እንቅፋት የመሆናቸው እድልም ቀላል አይደለም። 

ሱዳን

ሱዳን ላይ የሰፈረ ጦር አለ ከተባለ ያው የእኛው ነው። ወደ 6000 የሚሆኑ የኢትዮጵያ ወታደሮች በሱዳን በሰላም ማስከበር ላይ ይገኛሉ። ያው የሄዱት ጠበንጃና ወኔያቸውን ይዘው ነውና የግራ ጎናችንን በሚገባ ሸፍነውልናል።

ሱዳን ከግብፅ ጋር ያላት ግንኙነት ከእኛ ቢብስ እንጂ አይሻልም። የግብፅ በምስራቅ አፍሪካ እግር ማብዛት ጨርሶ ደብሯታል። እናም ግራ ጎናችን በዚህ ረገድ ሴፍ የሚባል ነው።

ነገር ግን ከግብፅ ጋር ያላት ፀብ ወደ ሳውዲ እየገፋት ይመስላል። ይህ የተጠናከረው ወዳጅነት የሳውዲን ጦር ወደ ማስፈር እንዳያመራ መስራት ያስፈልጋል። ካስፈለገ የወታደራዊ ስምምነት ልንፈራረምና ሱዳን ከግብፅ በሚመጣባት ነገር ብቻዋን እንደማትሆን ልናሳምናት ይገባል።

ሀገራቸው ላይ ጦር ማስፈር የማይወዱት ሱዳናውያን ያመኑት ጦራችንን እንዲተማመኑበት ማድረግ ጠቃሚ ይመስለኛል።

ደቡብ ሱዳን

ደቡብ ሱዳን አዲሷ ጆከር ነች። ትርምስምሷ የወጣው ሀገር የማንም መፈንጫ ለመሆን የምትመች ሆናለች። ለዚህም ነው ግብፅ እንደ ውሀ ቀጂ የምትመላለሰው። ይሄ ወጣ ገባ ሱዳንንም ኢትዮጲያንም ያሳሰበ ሆኗል። የኪር መንግስት አይዲዮሎጂካል ወይም የጠላትነት አጀንዳ የሌለው ስልጣኑን ለማስቀጠል ማንንም የሚያስተናግድ ጥቅም ተኮር ነው።

አያያዙ ካላማረ ኢትዮጲያ በጥቅሙ (ስልጣኑ) ልትመጣበት የምትችልባቸው ብዙ መንገዶች አሏት። ቀይ መስመሩ ከታለፈ ሀገሪቷን ወደለየለት ቀውስ መክተት እንደምንችል ለኪርም ለሚያሳስባቸው የቀጠናውና የአለም ሃገራት ግልፅ ማድረግ ይበጃል።

ሶማልያ

የሶማልያ መንግስት ህልውና የተመሰረተው ኢትዮጲያ ባሰፈረችው ጦር ላይ እንደሆነ በተደጋጋሚ ታይቷል። የሶማልያን መንግስት ለመጣል እንደው ከተፈለገ የኢትዮጵያን ጦር ከካምፑ እንዳይወጣ ማዘዝ ይበቃል። ይህ ማለት ኢትዮጵያ ሶማልያ ላይ ትልቅ leverage አላት ማለት ነው።

ለዚህ ነው አዲስ የተመሰረተው መንግስትም የኢትዮጵያ ወዳጅ ከመሆን ሌላ አማራጭ የማይኖረው። የቀደመው ፕሬዘዳንት ከግብፅ የቀረበለትን የጦር ማስፈር ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ለዛም በምርጫው የኢትዮጵያን ድጋፍ ማግኘቱ ይታወሳል። አዲሱ አሜሪካዊው የሶማልያ ፕሬዘዳንትም ከኢትዮጵያ ጋር ጋር ያለውን ወዳጅነት መጠበቅ ግድ ይለዋል። አለዚያ አልሸባብ ወደ ቡፋሎ (buffalo) ይመልሰዋል። ይህንን እንዳይረሳው ማስታወስ አይጎዳም።

ሶማሊላንድ

ሶማሊላንድ ሀገር አይደለችም። ከእኛ ውጪ ለኢኮኖሚያዊ ትዳር የሚያስባትም የለም። የሶማሊላንድ ገዢ ፓርቲ ግን ያን የዘነጋ ይመስላል የሶማሊላንድ ነፃነትን የምትቃወመዋን አረብ ኢሚሬት ጦር ለማስፈር ተስማምቷል።

ነገ አረብ ኢሚሬትስ ከሞቃዲሾ መንግስት ጋር ተዋውላ አልለቅም ብትል የሚያስለቅቅበት የህግ መሰረት የሌለው እውቅና አልባ መንግስት በሶማሊላንድ ነፃነት ላይ ትልቁን ቁማር ተጫውቷል። ጠበቆቻቸውን ሳያማክሩ በምርቃና የወሰኑት ይመስላል።

ምንአልባትም አይዟችሁ ያላቸው ሌላ ሀገር ይኖራል። ኢትዮጲያ ይህንን ስምምነት ለማሰረዝ ከበቂ በላይ አቅም አላት። ከሶማሊላንድ ጋር ያላትን የኢኮኖሚ ትብብር ለማቆም ማስጠንቀቂያ መስጠት ብቻውን የዛን መንግስት ምርቃና ይሰብራል። ካላደረግን ምክንያቱ እንቅልፍ ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው።

ኬንያ

ኬንያ እናቷ – ካሰፈረችም የእኛን ስደተኞች ነው የምታሰፍረው። ከእሷ የሚመጣ ስጋት ኖሮም አያውቅም ወደፊትም እንደማይኖር መገመት ይቻላል።

ማጠቃለያ

ለግዜው ተከበናል ማለት ይከብዳል። በሁለቱ ጎረቤቶች (Eritrea & Somaliland) የአረብ ሀገራት ጦር ለመስፈር እድል ቢያገኝም በሁለቱ (Sudan & Somalia) ደግሞ የእኛ ጦር ሰፍሯል። የደቡብ ሱዳን ገና አልለየም። ቀሪዎቹ ሁለቱ (Djibouti & Kenya) ሴፍ ናቸው። 

በንፅፅር ግን እንግዳ ሀይሎች በቀጠናችን የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ጨምሯል። በተለይ የግብፅ መቍነጥነጥ ትኩረት ሊሰጠው እና የውጭ ጉዳይ እርምጃዎቻችን ክስተቶችን የሚቀድሙ (preemptive) ሆነው መቃኘት ይኖርባቸዋል። ሰርፕራይዝ የሚያምረው ለቫለንታይን ብቻ ነው።

********

Source: HornAffairs.com
ይህን ጽሑፍ ወስደው ሊያትሙ ቢሹ፤ የሆርን አፌይርስን እና የፀሐፊውን ስም በግልጽ መጥቀስ እና የዚህን ፖስት Link ማስቀመጥ ይገባል፡፡

7 Comments
 1. aschenaki

  ፍፁም በቀልድ አዋዝተህ ያነሳሄዉ ጉዲይ እነንም ዘወትር የሚያሳስበኝ ነዉ::ነገሪዬዉ በአደባባይ የምትወያይበት ሰለ አልሆነ እንጂ ምቾት የማይሰጡ ብዙ ሁኔታዎች አሉ::መከላከያችንን ለማሻሻል አየተሰራ ያለዉ ስራ ከሀገራችን ፈጣን እድገት ጋር የሚመጣጠን ይመስልሃል? ለመስዋእትነት ዝግጁ የሆነ ጀግና ሰራዊት ባለቤት መሆናችን ባይካድም በዘመናዊ ትጥቅ ካላጠናከርነዉ ደህነታችን ከስጋት ዉጪ አይሆንም::ስለዚህ የመከላከያችንን ሁለንተናዊ አቅም ልናሳድግ ይገባናል::

 2. Dendir

  Let analysts write the geopolitic analysis.what the hell do you mean “tekebenal lemalet yikebdal” ? UAE already got base in somaliland.Somalia hosting Turkey and became ally with saudi, eritrea already have UAE and Saudi arabian bases.Kiir’s Sudan befriended egypt due to trust issues. Ethiopia, well, Ethiopia became a country with no economic and geopolitics importance in the horn.Adios!

 3. dergu temelese

  የወቅቱ ኢትዮጵዊ የትውልድ ሁለት አማራጭ
  ብሔራዊ ስሜት የነበረው የኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም መንግሥት ቀይ ባህርን የዓረብ ባህር ለማድረግ እና ኤርትራንም ከእናት አገሯ ለመገንጠል ሻዕብያ እና ወያኔ በአረብ ፔትሮ ዶላር ሰክረው አገራቸውን ለመሸጥ እና ለማፍረስ እየሰሩ ነው፤ ሻዕብያ እና ወያኔ ከዘበኛ እስከ ምሁር በዘር ተደራጅተው ኢትዮጵያን ለማጥፋት ሲሰሩ ቁጭ ብለን መመልከት የለብንም፤ አብዮታዊት እናት ሀገር ወይም ሞት ብለው ለአሥራ ሰባት ዓመታት ሀቀኛ ኢትዮጵያውያንን አስተባብረው ተዋግተዋል፤ በርካታ ጀግኞችም ቀይ ባህር ላይ ደማቸውን አፍሰዋል፡፡ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ምንም እንኳ በመጨረሻ ሞትን ፈርተው እንደ ሸሹ ቢነገርላቸውም ያሉትም አልቀረ ዛሬ ቀይ ባህር ወደ ዓረብ ባህርነት ስለመቀየሩ የሳውዲ ዓረቢያ፤ ኳታር እና ዐረብ ኤምሬትስ በአሰብ ወደብ እና በሶማሊያ መስፈር እንዲሁም ታሪካዊ ጠላታችን ቱርክ በአፍሪካ ታላቅ የሆነውን ጦር ሰፈር በሶማሊያ ለመገንባት ጫፍ ላይ መድረሷ ትልቅ ምስክሮች ናቸው፡፡
  ስልጣናቸውን ለሻዕብያ እና ወያኔ አምበሎች አስረክበውና ለሀገሪቱ አንድነት የታገሉትን ኢትዮጵውንን አመስግነው ወደ ሙጋቤ የተጠጉት የቀድሞው መሪ ከተናገሩት የቀረ ነገር ያለ አይመስልም፡፡ ሻዕብያ እና ወያኔ ባላቸው ስምምነት መሠረት ኤርትራ ስትገነጠል ኢትዮጵያን የሚበታትን ህገ መንግሥት (አንቀጽ 39) በወያኔ ተቀርጾና ዝርዝር አፈጻጸሙ ተቀምሮ ላለፉት 26 ዓመታት የትግራ ኢኮኖሚ እስኪገነባና ታላቋ ዓባይ ትግራይ እስክትመሰረት እንዲሁም ቀሪዋ ኢትዮጵያ በጎሳ እስክትበታተን ድረስ ጥቂት ዓመታትን መጠበቅ ሊኖርብን ይችላል፡፡ ኤርትራ የምትባል ሉዓላዊት አገር ትኖራለች ኢትዮጵያ የምትባል ሉዓላዊት አገር ግን አትኖርም በማለት ኢሳያስ አፈወርቂ የተናገሩትንም ለማየት የቀረን ጊዜ በጥቂት ዓመታት የሚቆጠር ነው፡፡
  ለዘህ ማስረጃው የኦሮሚያን እና አማራን ክልል ከሱዳን የሚያዋስኑትን ቦታዎች ወደ ቤኒሻንጉል ጉምዝ እና ወደ ትግራይ በማካለል ጋምቤላን፣ የዓባይ ግድብ ያለበትን ቦታ ጨምሮ ቤኒሻንጉል ጉምዝን፣ ወልቃይት እና ሁመራን እንዲሁም የአፋርን እና የአሰብ ወደብን በማጠቃለል 100 ሺ ካሬ ኪሎሜትር ስፋት ያላት ታላቋ ትግራይ እንደምትመሠረት ህወሀት ያወጣው ካርታ ይፋ መሆን እና ራስ ዳሸን እና ዋልያ ትግራይ ውስጥ ይገኛሉ በማለት በትግራይ ትምህርት ቤቶች መማሪያ መጻህፍት ከአሥር ዓመት በላይ ሲሰጥ የቆየው ትምህርት በመጨረሻም ትምህርት ሚኒስትር በኢቢሲ ይቅርታ የጠየቀበት በትግራይ ትምህርት ቢሮ ተፈጸመ የተባለው ስህተት ምስክሮች ናቸው፡፡
  ዛሬ ትግራይ በመሠረተ ልማት፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በኢንዱስትሪ እና በቢዝነስ ከኢትዮጵያ ግንባር ቀደም መሆኗን በመስማት ሳይሆን አይቶ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ትግራይ ውስጥ ያልተገነባ ፋብሪካ የለም፡፡ ወጣቱ ትግራይን ለመገንባት የሚያስችለውን ገንዘብ እንዲያመጣ በመላው ኢትዮጵያ ተሰማርቷል፡፡ ትግራይ ውስጥ ያሉ አዛወንት እና መከላከያ ሠራዊት ብቻ ናቸው፡፡ ኤፈርት የተባለው የህወሀት የኢኮኖሚ ድርጅት ሀብት በአፍሪካ ተወዳዳሪ እንደሌለው እንደ ታቦት የሚታዩት ታጋይ አቦይ ስብሀት በአሜሪካ ድምጽ ቀርበው መስክረዋል፡፡ አሁን ያለማጋነን በኢትዮጵ የትግራይ ሀብት ድርሻ ከ50 ፐርሰንት በላይ ነው ምንም እንኳ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ከትግራይ የምናገኘው ገቢ ለጠመኔ መግዣም አይበቃም ብለው የነበረ ቢሆንም፡፡ በእርግጥ የኤፍርት ሀብት ምንጭ ኢትዮጵያ ናት ትግራይ አይደለችም፡፡
  አሁን ሀገሬ ወደ ማይቀረው መበታተን እያመራች ነው፡፡ ምናልባት ፈጣሪ በረቂቅ ስልጣኑ ካልታደጋት በስተቀር፡፡ እርግጥ ነው ኢትዮጵዊ የሆነ ወገን አሁንም አልሞት ባይ ተጋዳይ ሆኖ ከወያኔ እና ሻዕብያ ጋር እየተዋጋ እና ከአገሬ በፊት እኔ ልሙት ብሎ እየሞተ ነው፡፡ ክፋቱ ትግሉ የሚደረገው የኢትዮጵያን ሀብት ሙሉ በሙሉ ከተቆጣጠረው እና ዙሪያውን አይዞህ የሚል የአረብ፣ የሲ አይ ኤ የእንግሊዝ የስላለ ሃይል ( ኤም ኤ 6 ) ድጋፍ ካለው ወያኔ ውስጥ ተከቦ መሆኑ ውስብስብ አደገኛና ተስፋ አስቆራጭ ቢሆንም፡፡ አሁን አትዮጵያን ለማዳን የትግል ስልቱ እጅግ ረቂቅ እና በመንፈስ የሚመራ ሊሆን ይገባል፡፡ ወያኔ ካለው ሰፊ ሀብት በተጨማሪ የምስጢር ማህበራት (ሰይታን አምላኪዎች) የሆኑ እነ ቢል ጌትስ፣ ጎርጅ ደብሊው ቡሽ እና አንጌላ ሜርክልን የመሳሰሉ ይረዱታል፡፡ እነዚህ ማህበራት ደግሞ ኢትዮጵያን ማዕከል አድርገው ዓለም አቀፋዊ የግጭት ዕቅድ እንዳላቸው በርካታ መረጃዎች አሉ፡፡
  ሆኖም ሊያስማማን የሚገባ ነገር ወቅቱ ፈጠረልን የወቅቱ ኢትዮጵዊ የትውልድ ሁለት አማራጭ ውስጥ ያለ መሆኑን ነው፡፡ አንድም የወያኔ እና ተባባሪዎቹ የሰይጣን ማህበራት ለሀገራችን የሸረበትን ጥፋት በጸሎት፣ በጀግንነት እና በመሰዋትነት መመከት አልያም ለሰይጣን ማህበራት ዳረጎት እና ወያኔ አገልጋይ በመሆን ለሆድ ብቻ መኖር ነው፡፡ እግዚአብሔር በጸሎት፣ በጀግንነት እና በመሰዋትነት አምነን የምንኖር ያድርገን፡፡