[Video]ም/ጠ/ሚ ደብረጺዮን – ወቅቱ ያናግራል፣ ‘ለምን ዓላማ ተናገሩ’ ወደሚል መሄዱ አይጠቅምም

ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚሰነዘሩ ሀሳቦችን በይዘታቸው በመመዘን ጠቃሚውን መውሰድ እንጂ ለምን ተባለ ወደሚለው መሄድ አይጠቅምም፤ ብለዋል በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የኢኮኖሚና ፋይናንስ ክላስተር አስተባባሪ ደብረጺዮን ገብረሚካኤል፡፡

ዶ/ር ደብረጺዮን ይህንን የተናገሩት ባለፈው ነሐሴ 27/2008 ለኦንላይን ሚዲያዎች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነበር፡፡

የቀድሞ የህወሓት ነባር አመራሮች (እነጄ/ል ጻድቃንና ጄ/ል አበበ) ከቅርብ ግዜ ወዲህ በስፋት ትችቶችን እየሰነዘሩ ስለመሆኑ በተጠየቁበት ወቅት ነው ደብረጺዮን፤ ‹‹ወቅቱ ያናግራል››፣ ‹‹እንኳን ዜጋ የውጭ ሰውም አስተያየት ሊሰጥ ይችላል›› በማለት መልሰዋል፡፡ አክለውም ‹‹ዝም ከሚባል ሀሳቦች ቢገለጹ ይጠቅማል፤ ከሌላ አቅጣጫ የሚመጡ ሀሳቦች ሁሌም ቢመጡ ነው የሚሻለው እንድትፈትሽ [ይረዳል]›› ብለዋል፡፡ ለምን ዓላማ(motive) ተናገሩ ወደሚለው መሄዱ አይጠቅምም የሚል አስተያየት ሰንዝረዋል፡፡

ሚኒስተር ደብረጺዮን ሌሎች ጉዳዮችንም በጋዜጣዊ መግለጫው ዳስሰዋል፡፡

Photo - DPM Debretsion Gebremichael
Photo – DPM Debretsion Gebremichael

ከጋዜጣዊ መግለጫው በከፊል ‹‹ም/ጠ/ሚ ደብረጺዮን – የብሔር የበላይነት ስለሚባለውና በጎንደር ስለተከሰተው መፈናቀል [Video]›› በሚል ባለፈው አቅርበን የነበረ መሆኑ ይታወሳል፡፡

ከታች ባቀረብነው የጋዜጣዊ መግለጫው ቪዲዮ ደግሞ የተዳሰሱ ጉዳዮች፡-

* በሳቸው ስም በተከፈተ ሀሰተኛ የፌስቡክ አካውንት ጽሑፎች ስለመሰራጨታቸው

* በተሐድሶ/በክፍፍሉ ወቅት የወጡ የህወሓት ነባር አመራሮች ትችቶችን እየሰነዘሩ ስለመሆኑ

* የሞባይል ስልክ ቀፎዎች ምዝገባ የማድረግ እቅድን በተመለከተ

* በ2008 በነበሩት ተቃውሞዎችና ግርግሮች ምክንያት የህዳሴ ግድብ ተጓትቷል ወይ;

* ‹‹ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብቷ እንዳትጠቀም የሚፈልጉ ሀይሎች›› ሚና ነበራቸው ስለተባለው

* ከወቅታዊ አለመረጋጋቶች ጋር በተያያዘ ቀጣይ የፖለቲካ ስራዎችን በተመለከተ

 (ለድምጽ ጥራት ችግር ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡)

——

Watch the video

********

Daniel Berhane

more recommended stories